Fana: At a Speed of Life!

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካቢኔ  በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ካቢኔ ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል። ካቢኔው ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የማረሚያ ቤቶች የታራሚዎች ቀለብ ማሻሻያ ላይ ተወያይቷል። በዚሁ ውይይት በክልሉ…

በሜክሲኮ በተከሰተ የመድረክ መደርመስ አደጋ የ9 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሜክሲኮ በተከሰተ የመድረክ መደርመስ አደጋ አንድ ህፃንን ጨምሮ ዘጠኝ ሰዎች ህወታቸው ማለፉ ተገለፀ፡፡ አደጋው የሜክሲኮ ሴንተሪሰት ሲቲዝንስ ንቅናቄ ፓርቲ መሪ ጆርጌ አልቫሬዝ ሜኔዝ በኒኦቮ ሊዮን ግዛት የምርጫ ቅስቀሳ እያደረጉ በነበረበት ወቅት…

ተማሪ ደራርቱ ለሜሳን የገደለው ግለሰብ በ18 ዓመት እስራት ተቀጣ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የነበረችውን ደራርቱ ለሜሳን በጩቤ ወግቶ የገደለው ግለሰብ በ18 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣተወሰነበት፡፡ አቶ ዮሐንስ መርጋ ኢተቻ የተባለው ግለሰቡ ግንቦት 9 ቀን 2016 ዓ.ም በግምት ከጧቱ 2 ሰዓት 45 ሰዓት አካባቢ…

ቻይና በታይዋን ዙሪያ ወታደራዊ ልምምድ ማድረግ ጀመረች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና በታይዋን ዙሪያ የባህር እና የአየር ወታደራዊ ልምምዶችን ማድረግ መጀመሯን አስታወቀች፡፡ ለሁለት ቀናት ይቆያል የተባለው ልምምዱ የታይዋን አዲሱ ፕሬዝዳንት በሹመታቸው ወቅት የታይዋን ሉዓላዊነት አስጠብቃለሁ ሲሉ ቃል መግባታቸውን ተከትሎ…

1 ሺህ 199 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳዑዲ ዓረቢያ ችግር ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 199 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡ ከተመላሾች ውስጥ 1 ሺህ 159 ወንዶች፣ 19 ሴቶች፣ 21 ጨቅላ ሕጻናት እና 12 ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡…

አቶ አሻድሊ ሀሰን ከተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ የተለያዩ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ተወያዩ። በውይይቱ ርዕሰ መስተዳድሩ÷ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ለህዝብ ሰላም እና ልማት ቅድሚያ ሰጥተው…

ያልተቆራረጠ የካንሰር የመድሃኒት አቅርቦት እንዲኖር ጥረት እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ያልተቆራረጠ የካንሰር የመድሃኒት አቅርቦት እንዲኖር ጥረት እየተደረገ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። የካንሰር መድሃኒቶችን አቅርቦት ለማሻሻል ያለመ የባለድርሻ አካላት ውይይት ተካሄዷል፡፡ የጤና ሚኒስትር ዴኤታው ዶክተር ደረጄ ድጉማ በዚህ…

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዘላቂ ሰላም ለማስፈን እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በክልሉ ዘላቂ ሰላም ለማስፈን በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ጥላሁን ከበደ ገለጹ፡፡ የክልሉ የጸጥታ ምክር ቤት 2ኛ ዙር መደበኛ ጉባዔ በወላይታ ሶዶ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡ አቶ ጥላሁን በመድረኩ ላይ…

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከጣልያን አቻቸው አድሚራል ጉሴፔ ካቮ ድራገን ጋር ተወያዩ

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከጣልያን አቻቸው አድሚራል ጁሴፔ ካቮ ድራገን ጋር ተወያዩ አዲስ አበባ፣ ግንቦት 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከጣልያን ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም አድሚራል ጁሴፔ ካቮ ድራገን ጋር ተወያይተዋል፡፡ በፊልድ…

የጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ንግግሮችና መልዕክቶችን የያዘ መጽሃፍ ለንባብ በቃ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ንግግሮችና መልዕክቶችን የያዘ እና ከ''መስከረም እስከ መስከረም'' የተሰኘ መጽሃፍ ለንባብ በቅቷል፡፡ መጽሃፉ ላይ ሙያዊ ውይይት በወዳጅነት ፓርክ መካሄዱን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መረጃ…