Fana: At a Speed of Life!

የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባኤ አካሄደ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት 3ኛ የሥራ ዘመን 2ኛ ዓመት ሁለተኛ አስቸኳይ ጉባኤ አካሂዷል፡፡ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት የመንግስት ተጠሪ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ በጉባዔው ለውይይት የሚሆን መነሻ ጽሁፍ አቅርበዋል።…

ከ558 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ558 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዛቸውን የጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ ኮሚሽኑ ከነሐሴ 5 እስከ ነሐሴ 11 ቀን 2015 ዓ.ም ባደረገው ክትትል 523 ነጥብ 1 ሚሊየን የገቢ የኮንትሮባንድ እቃዎች እና 35…

የምስራቅ ዕዝ ለጅግጅጋ የገበያ ማዕከል የእሳት አደጋ ተጎጂዎች የ2 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በመከላከያ ሠራዊት የምስራቅ ዕዝ በጅግጅጋ ከተማ አዲሱ ታይዋን የገበያ ማዕከል በተከሰተው የእሳት አደጋ ሀብት ንብረታቸው ለወደመባቸው ተጎጂዎች የ2 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ፡፡ ድጋፉን የምስራቅ ዕዝ ዋና አዣዥ ሌተናል ጄኔራል መሀመድ ተሰማ…

ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ለተሰጣት እውቅና የእንኳን ደስ ያለሽ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ በሃንጋሪ ቡዳፔስት በተካሄደው 54ኛው የዓለም አትሌቲክስ ጉባዔ ላይ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ በአትሌቲክሱ ዘርፍ ላበረከተችው አስተዋጽኦ ለተሰጣት የ”ፕላክ ኦፍ ሜሪት” እውቅና…

ዕዙ በአማራ ክልል ሰላምን ለማረጋገጥ በቀጣይ መወሰድ ያለባቸው እርምጃዎች ላይ አቅጣጫዎችን አስቀመጠ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ በአማራ ክልል ሰላምና ደኅንነትን ሙሉ በሙሉ ለማረጋገጥ በቀጣይ መወሰድ ያለባቸው እርምጃዎች ላይ አቅጣጫዎችን አስቀመጠ። ዕዙ ዛሬ ባደረገው ስብሰባ ወደ ሥራ ከገባ ጊዜ ጀምሮ ላለፉት 13 ቀናት ያከናወናቸውን…

በአማራ ክልል ፅንፈኛውና ዘሪፊው ቡድን ደቅኖት የነበረው አደጋ በህዝቡና በፀጥታ ኃይሎች ትብብር ሙሉ ለሙሉ ተቀልብሷል – የዕዙ አመራሮች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ፅንፈኛውና ዘራፊው ቡድን ደቅኖት የነበረው አደጋ በክልሉ ህዝብና በፀጥታ ኃይሎች ትብብር ሙሉ ለሙሉ መቀልበሱን የአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ አመራሮች ገለጹ። የክልሉ ሕዝብ፣ የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ከመከላከያ…

ዛሬ ምሽት በሴቶች 10 ሺህ ሜትር የፍፃሜ ሩጫ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ይጠበቃሉ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሃንጋሪ ቡዳፔስት እየተካሄደ በሚገኘው 19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ምሽት በሚካሄደው የሴቶች 10 ሺህ ሜትር የፍፃሜ ሩጫ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ለአሸናፊነትከፍተኛ ግምት ተሰጥቷቸዋል። በውድድሩ በአሜሪካ ኦሬጎን በተካሄደው 18ኛው…

የፋና ላምሮት ምዕራፍ 14 ውድድር በአጸደማርያም ያረጋል አሸናፊነት ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠንካራ ፉክክር የታየበት የፋና ላምሮት የድምፃውያን የተሰጥዖ ውድድር ምዕራፍ 14 በአጸደማርያም ያረጋል አሸናፊነት ተጠናቀቀ። ላለፉት 8 ሳምንታት በዳኞችና በራሳቸው ምርጫ ሲወዳደሩ የነበሩ ተወዳዳሪዎች በዛሬው የፍጻሜ ውድድር ላይ ትንሳኤ ስለሺ፣…

መቄዶንያ በ130 ሚሊየን ብር በመቱ ከተማ ማዕከል ሊገነባ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) መቄዶንያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ሕሙማን መንከባከቢያ በጎ አድራጎት ድርጅት በ130 ሚሊየን ብር በመቱ ከተማ ማዕከል ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ አስቀመጠ፡፡ በበጎ አድራጎት ድርጅቱ የክልል ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ማኅተመ በቃሉ እንደገለጹት÷ በመቱ…

ርዕሳነ መስተዳድሮች ለደቡብ ኢትዮጵያና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ ክልሎች ርዕሳነ መስተዳድሮች የደቡብ ኢትዮጵያና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች ምስረታን አስመልክቶ ‘እንኳን ደስ አላችሁ’ ሲሉ የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ÷ ለክልሎቹ…