Fana: At a Speed of Life!

አቶ ኢሳያስ ጅራ ከካፍ ፕሬዚዳንት ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ ከአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ፕሬዚዳንት ፓትሪስ ሞሴፔ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡ ፕሬዚዳንት ፓትሪስ ሞሴፔ በፌዴሬሽኑ ባለቤትነት ግልጋሎት እየሰጠ የሚገኘውን…

በአዲስ አበባ ሰሞኑን የወጣው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ  ውድቅ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሐምሌ 1 ቀን 2014 ያወጣውን የ20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ዕጣ ውድቅ አደረገ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዛሬው ዕለት በሰጡት መግለጫ÷  ባሳለፍነው ሐምሌ 1 ቀን…

በአንዳንድ አካባቢዎች ቅጽበታዊ ጎርፍ ሊያስከትል የሚችል ከባድ ዝናብ ሊኖር ስለሚችል ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በመጠንም ሆነ በስርጭት ብዙ አካባቢዎችን የሚሸፍን እርጥበት እንደሚኖር እና በአንዳንድ አካባቢዎች ቅጽበታዊ ጎርፍ ሊያስከትል የሚችል ከባድ ዝናብ ሊኖር ስለሚችል ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ብሔራዊ የሚቲዮሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስጠነቀቀ፡፡…

የፌዴሬሽን ምክር ቤት ነገ መደበኛ ስብሰባውን ያካሂዳል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴሬሽን ምክር ቤት 6ኛውን የፓርላማ ዘመን 1ኛ ዓመት የሥራ ጊዜና 2ኛ መደበኛ ስብሰባውን ነገ ያካሂዳል፡፡ የምክር ቤቱ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ተረፈ በዳዳ እንደገለጹት÷ ምክር ቤቱ በስብሰባው በበርካታ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ…

ከሕዝብ በተነሱ ጥያቄዎች እና መፍትሄዎቻቸው ዙሪያ ምክክር እየተደረገ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ከሕዝብ በተነሱ ጥያቄዎች ላይ እና መፍትሄዎቻቸው ዙሪያ ዛሬ ከአስፈፃሚ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ጋር እየመከሩ ነው። ሕዝቡ ያነሳቸው የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ የምክር ቤት አባላቱ በቁርጠኝነት…

ኦሮሚያ ባንክ “የአውሮፓ ሶሳይቲ ፎር ኳሊቲ ሪሰርች” የ2022 አገልግሎት ጥራት ተሸላሚ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኦሮሚያ ባንክ “የአውሮፓ ሶሳይቲ ፎር ኳሊቲ ሪሰርች” የ2022 አገልግሎት ጥራት ተሸላሚ ሆኗል። ከተመሠረተ 14 አመት የሆነው የኦሮሚያ ባንክ በዓለም አቀፍ ንግድ እና ሁሉ አቀፍ የአገልግሎት ልሕቀት እንዲሁም እያከናወነ ያለውን የትራንስፎርሜሽን…

እስካሁን 50 ሺህ 337 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) እስካሁን 50 ሺህ 337 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ በሳዑዲ ዓረቢያ በችግር ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ ከመጋቢት 21 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ…

“ግሪን ትራንስፖርት” የተሰኙ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ስራ ጀመሩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) "ግሪን ትራንስፖርት" የተሰኙ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ዛሬ ስራ ጀምረዋል። ተሽከርካሪዎቹ "ግሪን ቴክ አፍሪካ" በተሰኘ ኩባንያ የተመረቱ ሲሆን÷ የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ የተሽከርካሪዎቹን ስራ ዛሬ በአዲስ አበባ…

በሕክምና የሚታዩ ስህተቶችን ለመቀነስ የሙያ ክህሎትን ማጎልበት እንደሚያስፈልግ ተጠቆመ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሕክምና አገልግሎት አሰጣጥ የሚታዩ የሕክምና ስህተቶችን ለመቀነስ ለባለሙያዎች የተግባቦትና የሙያ ክህሎት ስልጠናዎች ትኩረት ሊሰጣቸው እንደሚገባ የአዲስ አበባ የምግብ፣ መድኃኒት፣ ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለሥልጣን አስታወቀ። ባለሥልጣኑ…

ለትግራይ ክልል የመልሶ ማቋቋሚያ ፕሮጀክት የሶስተኛ ወገን የትግበራ ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 5 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ክልል ለሚካሄደው የመልሶ ማቋቋሚያ ፕሮጀክት ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፕሮጀክቶች አገልግሎት ቢሮ ጋር የሶስተኛ ወገን የትግበራ ስምምነት ተፈራረመ። ስምምነቱን የኢፌዴሪ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ…