Fana: At a Speed of Life!

በጋዛ የተኩስ አቁም ዙሪያ ላይ የቀረበው ረቂቅ የውሳኔ ሃሳብ በፀጥታው ምክር ቤት ውድቅ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ የተዘጋጀውና በአሜሪካ አማካኝነት የቀረበው ረቂቅ የውሳኔ ሃሳብ በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ውድቅ መደረጉ ተገለጸ፡፡ የፀጥታው ምክር ቤት በኒውዮርክ በሚገኘው የመንግስታቱ ድርጅት ዋና መስሪያ ቤት…

ኢትዮጵያ በ1 ሺህ 500 ሜትር ሴቶች ሩጫ ውድድር የወርቅና የብር ሜዳሊያ አገኘች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋና እየተካሄደ ባለው 13ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች ኢትዮጵያ በ1 ሺህ 500ሜትር ሴቶች ሩጫ ውድድር የወርቅና የብር ሜዳሊያ አገኘች። በርቀቱ ለኢትዮጵያ የወርቅና የብር ሜዳሊያ ያመጡት አትሌት ሂሩት መሸሻ እና አትሌት ሀዊ አበራ ናቸው።…

ኢትዮጵያ በ5 ሺህ ሜትር ወንዶች ሩጫ ውድድር የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋና እየተካሄደ ባለው 13ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች ኢትዮጵያ በ5 ሺህ ሜትር ወንዶች ሩጫ ውድድር በሀጎስ ገብረህይወት አማካኝነት የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች። አትሌት ሀጎስ ገብረህይወት 13:38.12 በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ ውድድሩን በቀዳሚነት…

ኢትዮጵያ በሴቶች የቦክስ ውድድር 2 የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋና እየተካሄደ ባለው 13ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች ኢትዮጵያ በ52 እና በ66 ኪሎ ግራም ሴቶች የቦክስ ውድድር 2 የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች። ቤተልሔም ገዛኸኝ ለሀገሯ የወርቅ ሜዳሊያ ያመጣችው በፍጻሜ ውድድሩ የሞሮኮዋን ቼዳል…

በሱዳን ያለውን ግጭት ለመፍታት ሁሉን አቀፍና አካታች ውይይት ያስፈልጋል – አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሱዳን ያለውን ግጭት ለመፍታት ሱዳናያውን በባለቤትነት የሚተሳተፉበት አፍሪካ መር ሁሉን አቀፍና አካታች ውይይት ያስፈልጋል ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ተናገሩ፡፡ ሚኒስትሩ በአፍሪካ ሕብረት ማዕቀፍ በሰላም እና…

ኢትዮጵያ በአህጉር ደረጃ ፍትሃዊ የውሃ አጠቃቀም እንዲረጋገጥ እየሰራች እንደሆነ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በብሔራዊና አህጉር ደረጃ ፍትሃዊ የውሃ አጠቃቀም እንዲረጋገጥ ሚናዋን እየተወጣች መሆኑን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታወቀ። የዓለም የውሃ ቀን "ውሃ ለሰላም" በሚል መሪ ሃሳብ የዓለም አቀፍ ተቋማትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት…

ማህበሩን ከ12 ሚሊየን ብር በላይ ያሳጡ ግለሰቦች እስከ 18 ዓመት በሚደርስ እስራትና በገንዘብ ተቀጡ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በህብረት ስራ ማህበራት ስም ሀሰተኛ የገቢ ደረሰኝ በማዘጋጀትና ገቢ በመሰብሰብ እንዲሁም የህብረት ስራ ማህበሩን የአፈር ማዳበሪያን ጨምሮ ሌሎች ምርቶችን ለግል ጥቅም በማዋል በአጠቃላይ ከ12 ሚሊየን ብር በላይ አሳጥተዋል የተባሉ ሶስት ተከሳሾች በፅኑ…

ውሃን ለመቆጠብ፣ ጥራቱን ለማሳደግና አቅርቦቱን ለማረጋገጥ ባለድርሻ አካላት ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ውሃን ለመቆጠብ፣ ጥራቱን ለማሳደግና አቅርቦቱን ለማረጋገጥ ባለድርሻ አካላት ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ። በየዓመቱ በፈረንጆቹ መጋቢት 22 የሚከበረው የዓለም የውሃ ቀን “ውሃ ለሰላም” በሚል መሪ ሀሳብ እየተከበረ ይገኛል፡፡ የዓለም የውሃ…

በሚኒስትሮች የተመሩ የተለያዩ ልዑኮች የልማት ሥራዎችን እየጎበኙ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በፌደራል መንግሥት ከፍተኛ አመራሮች የተመሩ የተለያዩ የድጋፍ እና ክትትል ልዑካን ቡድኖች እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎችን እየጎበኙ ነው፡፡ በትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) የተመራ ልዑክም በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል…

ናይጄሪያውያን ባለሃብቶች አውሮፓ ውስጥ የእግር ኳስ ክለብ ባለቤት መሆን ጀምረዋል ተባለ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ናይጄሪያውያን ባለሀብቶች አንዳንዶቹ በአውሮፓ ውስጥ የእግር ኳስ ክለቦችን መግዛት በመጀመራቸው በዓላም ታሪክ ስማቸውን መፃፍ መቻላቸው ተነግሯል፡፡ ናጄሪያውያኑ በፖርቹጋል ሁለት የእግር ኳስ ቡድኖች ሲኖራቸው አንዱ ደግሞ በዴንማርክ አንድ ቡድን…