Fana: At a Speed of Life!

343 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 30 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 343 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ሪያድ ከተማ መመለሳቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄኔራል ተወካይ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው ለተመላሾቹ አቀባበል አድርገዋል።…

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከካናዳው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 29 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከካናዳው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርክ ጋርኒው ጋር በስልክ ተወያዩ፡፡ በውይይታቸው ወቅትም ስለትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ ገለጻ ያደረጉ ሲሆን፥ በክልሉ ሰብአዊ ድጋፍ…

በየመን በኢትዮጵያውያን ዜጎች ላይ የደረሰውን ጉዳት በተመለከተ መንግስት ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን አስታወቀ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 29 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የካቲት 28 ቀን 2013 ዓ.ም በየመን ዋና ከተማ ሰንዓ ማቆያ እስር ቤት ላይ በተከሰተ የእሳት አደጋ በእስር ቤቱ ውስጥ በነበሩ እስረኞች ላይ የሞትና የቁስለት አደጋ እንደደረሰ በሙስካት (ኦማን) የሚገኘው የኢፌዴሪ ኤምባሲ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር…

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ከኬንያው ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 29 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ከኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር ተወያዩ፡፡ ፕሬዚዳንቷ በኬንያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት እያደረጉ ነው፡፡ በጉብኝታቸውም ከፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡ በተለይም…

የብልጽግና ፓርቲ በአዲስ አበባ ደረጃ የሚወዳደሩ ዕጩዎቹን አስተዋወቀ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 29 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልጽግና ፓርቲ ለስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ በአዲስ አበባ ደረጃ ለህዝብ ተወካዮችና ለአዲስ አበባ ምክር ቤት የሚወዳደሩ ዕጩዎቹን በሸራተን አዲስ አስተዋወቀ። ፓርቲው 23 ዕጩዎችን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማቅረቡን አስታውቋል፡፡ ከዚህ…

ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን “ትችያለሽ” በሚል መሪ ቃል በወዳጅነት አደባባይ ተከበረ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 29 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በአዲስ አበባ “ትችያለሽ” በሚል መሪ ቃል በወዳጅነት አደባባይ ተከበረ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ “እለቱ ጾታን መሰረት ያደረጉ በደሎች እንዲቆሙ በቆራጥነት የምንሰራበት፣…

ስልጣናቸውን በቀጣዩ ወር የሚለቁት የኒጀር ፕሬዚዳንት የ5 ሚሊየን ዶላር ሽልማት አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከሁለት ዙር የስልጣን ዘመን በኋላ ስልጣናቸውን በቀጣዩ ወር የሚለቁት የኒጀሩ ፕሬዚዳንት መሀመዱ የሱፍ የ2020 የአለም ትልቁን የመሪዎች ሽልማት አሸነፉ። በዚህም በሱዳናዊው ቢሊየነር የተቋቋመውን የሞ ኢብራሂም ፋውንዴሽን ሽልማት በማሸነፋቸው 5…

በሁለተኛ ዙር 40/60 ዕጣ ለወጣባቸው ቤቶችን ለባለ ዕድለኞች የቁልፍ ርክክብ መሰጠት ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሁለተኛ ዙር 40/60 ዕጣ የወጣባቸው እና የግንባታ አፈጻጸማቸው የተሻሉትን ቤቶችን ለባለ ዕድለኞች የቁልፍ ርክክብ መሰጠት ተጀመረ ። በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይ እና  የአዲስ…

ም/ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ሂደትን ተመለከቱ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በእቴጌ መነን የልጃገረዶች ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመገኘት የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ሂደትን ተመልክተዋል ። የ12ተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በአዲስ አበባ…

በዐቢይ ፆም ወቅት ሰላም፣ ፍቅር፣ ይቅር ባይነት መታዘዝና አካፍሎ መብላትን መተግበር ይገባል – ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 29 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በዐቢይ ፆም ወቅት ሰላም፣ ፍቅር፣ ስምምነት፣ ይቅር ባይነት መታዘዝና አካፍሎ መብላትን ምዕመኑ መተግበር እንደሚገባው ጥሪ አቀረቡ፡፡ ፓትርያርኩ የዐቢይ ጾም…