Fana: At a Speed of Life!

የ2012 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ፈተና ከታህሳስ 1 እስከ 30 ባሉት ጊዜያት ውስጥ ይሰጣል

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 15 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የ2012 ዓ.ም 8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከታህሳስ 1 እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2013 ዓ.ም ክልሎች በሚያወጡ መርሃ ግብር መሰረት እንደሚሰጥ የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። የትምህርት ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ሚሊየን ማቲዮስ በሰጡት መግለጫ በታህሳስ…

መንግሥት የሰጠውን የ72 ሰዓት ጊዜ በመጠቀም በርካታ የትግራይ ሚሊሻና ልዩ ኃይል አባላት እጅ እየሰጡ ነው

አዲስ አበባ፣ ህዳር 15፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) መንግሥት የሰጠውን የ72 ሰዓት ጊዜ በመጠቀም እጅግ በርካታ የትግራይ ሚሊሻና ልዩ ኃይል አባላት በየግንባሩ እጅ እየሰጡ መሆኑን የአስቸኳይ ጊዜ መረጃ ማጣሪያ አስታወቀ። በአፋር ክልል በኩል ብዙዎች ገብተው እጅ የሰጡ ሲሆን በማይ ጸብሪ ተቆርጦ…

የህወሓት ቡድን ሲጠቀምበት የነበረ 32 ኩንታል አደንዛዥ እፅ ተያዘ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 15 ፣2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የህወሓት ቡድን ሲጠቀምበት የነበረ 32 ኩንታል አደንዛዥ እፅ ተያዘ፡፡ አደንዛዥ እፁ በተሽከርካሪ ተጭኖ ከሁመራ ወደ የተለያዩ አካባቢዎች ሊገባ ሲል መያዙን የአማራ ክልል ልዩ ኃይል ቴዎድሮስ ብርጌድ ዋና አዛዥ ኮማንደር ዘለቀ ምትኩ ለአብመድ…

አቶ ሞላ መልካሙ የጎንደር ከተማ ከንቲባ ሆነው ተሾሙ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 15 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጎንደር ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት 8ኛ ዓመት 2ኛ አስቸኳይ ጉባዔውን እያካሄደ ነው። ምክር ቤቱ በጉባኤው አቶ ሞላ መልካሙን የከተማዋ ከንቲባ አድርጎ ሾሟል፡፡ በዛሬው ጉባኤ ሌሎች ልዩ ልዩ ሹመቶችን ያፀድቃሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከጎንደር…

ብሔራዊ የጀግኖችና የሕፃናት አምባ የተሰኘ የበጎ አድራጎት ድርጅት ተቋቋመ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 15 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ትብብር "ብሔራዊ የጀግኖችና የሕፃናት አምባ" የተሰኘ የበጎ አድራጎት ድርጅት መቋቋሙ ተገለፀ። ድርጅቱ የተቋቋመው በጦር ሜዳ ጉዳት ለደረሰባቸው አባላት እንክብካቤ ለማድረግና የሕይወት መሥዋዕትነት የከፈሉ የሠራዊት…

አንቶኒ ብሊንኬን በጆ ባይደን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው መታጨታቸውን ይፋ አደረጉ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 15 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ. ሲ) አንቶኒ ብሊንኬን በተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ቀጣዩ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው መታጨታቸውን ይፋ አደረጉ። እጩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ባለፉት ቀናት ከስራ ባልደረቦች እና ጓደኞች የደረሱኝ መልዕክቶች ኩራትን…

አምባሳደር ታዬ ለተመድ ዋና ፀሃፊ የዘር ማጥፋት ወንጀል መከላከል አማካሪ በትግራይ ክልል እየተካሄደ ስላለው ህግን የማስከበር ዘመቻ ገለጻ አደረጉ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በተመድ የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ለመንግስታቱ ድርጅት ዋና ፀሃፊ የዘር ማጥፋት ወንጀል መከላከል አማካሪ ፕራሚላ ፓተን በትግራይ ክልል እየተካሄደ ስላለው ህግን የማስከበር ዘመቻ ገለጻ አደረጉ። አምባሳደር ታዬ በዚህ…

ምርጫ ቦርድ ባዘጋጃቸው የተለያዩ መመሪያዎች ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክሮችን አከናወነ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 14፣ 2013 (ኤፍቢሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባዘጋጃቸው የተለያዩ መመሪያዎች ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክሮችን አከናወነ፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በአዋጅ 1162/ 2011 በተሰጠው ስልጣን መሰረት የተለያዩ መመሪያዎችን በማዘጋጀት ከመጽደቃቸው በፊት…

289 ኢትዮጵያውያን ዜጎች ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሃገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 289 ኢትዮጵያውያን ዜጎች በዛሬው እለት ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሃገራቸው ተመለሱ፡፡ ከተመላሾቹ መካከል 90ዎቹ ጨቅላ እና ታዳጊ ህጻናት መሆናቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡ ኢትዮጵያውያኑ መንግስት ከሳዑዲ…

የትምህርት ሚኒስቴርና የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግና አመራሮችና ሰራተኞች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የደም ለገሱ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 14፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የትምህርት ሚኒስቴር እና የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አመራሮች እና ሰራተኞች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የደም ልገሳ መርሃ ግብር አካሂደዋል። የኢፌዴሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አመራሮች እና ሰራተኞች “ደሜን ለህግ መከበር ህይወታቸውን ለሰጡት ለመከላከያ ሰራዊት…