Fana: At a Speed of Life!

በጣሊያን በአንድ ቀን በኮሮና ቫይረስ 475 ሰዎች ለህልፈት ተዳረጉ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 10 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በጣሊያን በአንድ ቀን 475 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ ህይዎታቸው አለፈ። በአንድ ቀን የተመዘገበው የሟቾች ቁጥር ቫይረሱ ከተከሰተ ወዲህ ከፍተኛው ሆኖ ተመዝግቧል። በሃገሪቱ በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር ወደ 3 ሺህ…

የፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ለ15 ቀን የታራሚዎችን ቤተሰብ ጥየቃ ማገዱን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ከኮሮና ቫይረስ ስርጭት ታራሚዎችን ለመጠበቅ ሲባል ለመጭዎቹ 15 ቀናት ታራሚዎች ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዳይገናኙ እግድ መጣሉን አስታውቋል። የማረሚያ ቤቱ ጄኔራል ኮሚሽነር ጀማል አብሶ እንደገለጹት፥ ክልከላው…

ጠ/ሚ ዐቢይ በዶክተር ካትሪን ሐምሊን ሕልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዶክተር ካትሪን ሐምሊን ሕልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ። በኢትዮጵያ የፌስቱላ ህክምና መስራች የነበሩት ዶክተር ካትሪን ሐምሊን በ96 ዓመታቸው በትናንትናው እለት ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ተገልጿል።…

በደቡብ ወሎ ዞን አምባሰል ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ10 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣መጋቢት 10 ፣2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን አምባሰል ወረዳ ትናንት በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ10 ሰዎች ህይዎት አለፈ። አደጋው ከሰሜን ወሎ ዞን ላልይበላ ከተማ ወደ ግሸን ደብረከርቤ ይጓዝ የነበረ አውቶብስ ጥልቅ ገደል በመግባቱ የተከሰተ መሆኑን የደቡብ ወሎ…

ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር ኢድሪስ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን አስመልክቶ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 10 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር ኢድሪስ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን አስመልክቶ መልዕክት አስተላልፈዋል። በመልዕክታቸውም ነጋዴወች እና ባለሃብቶች ለአቅመ ደካሞች ሰደቃ ወይም ምጽዋት በመስጠት…

ዶ/ር ካትሪን ሐምሊን ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ የፌስቱላ ሆስፒታል መስራች ዶክተር ካትሪን ሐምሊን ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። ዶክተር ካትሪን ሐምሊን በ96 ዓመታቸው በትናንትናው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ተገልጿል። ዶክተር ካትሪን ሀምሊን ፌስቱላ ኢትዮጵያ የተባለ ግብረሰናይ…

ኳራንቲን ምንድነው?

ከባለፈው ዜና የሰማነው አንድ በኮሮና ቫይረስ ህመም ተጠርጥሮ ወደ ለይቶ ማቆያና ህክምና ተቋም በሚወሰድበት ሰዓት አምልጦ የተለያየ ቦታ ከደረሰ በኋላ ተይዞ ምርመራ ሲደረግለት ነጻ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ይህ ስለ ለይቶ ማቆያ በቂ ያልሆነና የተዛባ መረጃ መድረስ ጋር ተያይዞ የሚፈጠር መደናበር የሚከሰት…

በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ከተያዙት አራቱ የህመም ምልክቶችን ማሳየት ማቆማቸው ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ከተያዙት አራቱ የህመም ምልክቶችን ማሳየት ማቆማቸውን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ገለፁ። በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ተይዘው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው የሚገኙ 6 ታካሚዎች ናቸው። ከእነዚህ ውስጥ…

ኮርፖሬሽኑ ለንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች ማዘጋጃ የሚውል በቂ ቴክኒካል አልኮል መኖሩን አስታወቀ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 9፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የስኳር ኮርፖሬሽን ለንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች ማዘጋጃ የሚያገለግል ከ3 ሚሊየን ሊትር ቴክኒካል አልኮል መኖሩን አስታወቀ። ኮርፖሬሽኑ ለጣቢያችን በላከው መግለጫ አልኮሉ በፊንጫ እና መተሐራ ስኳር ፋብሪካዎች እንደሚገኝ አስታውቋል። አሁን…

በሃዋሳ ከተማ የዋጋ ጭማሪ ያደረጉ እና ባዕድ ነገር ቀላቅለው ለገበያ ባቀረቡ አካላት ላይ እርምጃ ተወሰደ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 9፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በሃዋሳ ከተማ የኮሮና ቫይረስን መከሰት ምክንያት በማድረግ ምክንያታዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ ያደረጉ እና ባዕድ ነገር በመቀላቀል ለገበያ ሲያቀርቡ በነበሩ አካላት ላይ እርምጃ ተወሰደ። የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ደቡብ ቅርንጫፍ፣…