Fana: At a Speed of Life!

የፅንስ መቋረጥ ከፍተኛ ጭንቀትን ያስከትላል – ጥናት

አዲስ አበባ ፣ ጥር 6 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የፅንስ መጨናገፍ ለከፍተኛ ጭንቀት እንደሚዳርግ አንድ ጥናት አመላከተ። በእንግሊዝ የተደረገው ጥናት በእርግዝና ወቅት ፅንስ መጨናገፍ ያጋጠማቸው ሴቶች ከአደጋው በኋላ ለረጅም ጊዜ ከፍተኛ ለሆነ ውጥረት እና ጭንቀት እንደሚጋለጡ አመላክቷል፡፡…

ኢትዮ ቴሌኮም በግማሽ ዓመቱ ከ22 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱን ገለፀ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 6 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮ ቴሌኮም በግማሽ ዓመቱ 22 ቢሊየን 40 ሚሊየን ብር አጠቃላይ ገቢ ማግኘቱን ይፋ አደረገ። በስድስት ወር አፈጻጸሙ የእቅዱን 104 በመቶ ማሳካቱንም አስታውቋል፤ ካለፈው አመት አንጻር የ32 በመቶ እድገት አሳይቷል። ተቋሙ የውጭ ምንዛሪ…

የአማራ ክልል የማህበረሰብ ተሳትፎ የተፋሰስ ልማት ንቅናቄ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል የማህበረሰብ ተሳትፎ የተፋሰስ ልማት ንቅናቄ በዛሬው እለት መጀመሩ ተገለጸ። ንቅናቄው የፌደራልና የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች እንዲሁም የሃይማኖት አባቶች በተገኙበት በምዕራብ ጎጃም "የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ንቅናቄ ለምርት እድገት…

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ከዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 6 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ከዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ፒተር ማውራ ጋር ተወያይተዋል። በውይይታቸውም የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ በኢትዮጵያ በሚያከናውናቸው ተግባራት ዙሪያ መክረዋል። ዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ…

የሰላም ሚኒስትር ዲኤታዋ ከዓለም አቀፉ የወጣቶች ህብረት መስራች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ አልማዝ መኮንን ከዓለም አቀፉ የወጣቶች ህብረት መስራች ዶክተር ኦክ ሶ ፓርክ ጋር ተወያዩ። ሚኒስትር ዲኤታዋ በውይይታቸው ብሄራዊ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ፕሮግራም በማዘጋጀት ወጣቱን የፕሮግራሙ ተጠቃሚ ለማድረግ ዝግጅት…

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ያሰለጠናቸውን የፀጥታ እና ህግ ማስከበር ዳይሬክቶሬት አመራሮች እና አባላትን አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ያሰለጠናቸውን የፀጥታ እና ህግ ማስከበር ዳይሬክቶሬት አመራሮች እና አባላትን አስመርቋል። ስልጠናው ለአዳዲስ እና ነባር አመራሮች እና አባላት በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል መከላከል ዘርፍ የፀጥታ እና ህግ ማስከበር…

አሜሪካ ሁዋዌ ላይ ተጨማሪ ሽያጮችን ልታግድ ነው

አዲስ አበባ ፣ ጥር 6 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ ለሁዋዌ ተጨማሪ ሽያጮችን ልታግድ መሆኑን አስታወቀች። አሜሪካ የምታመርታቸውን ጨምሮ በተለያዩ ሃገራት የተመረቱ የቴሌኮም ምርቶችን ለግዙፉ የቻይና የቴክኖሎጅ ኩባንያ እንዳይሸጡ ለማገድ ስለመዘጋጀቷም ነው የገለጸችው። የትራምፕ አስተዳደር…

ከትራፊክ አደጋ የፀዳ የትራንስፖርት አገልግሎት ለሃገራዊ ህዳሴ በሚል መሪ ቃል የእግር ጉዞ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2012 (ኤፍቢሲ) ከትራፊክ አደጋ የፀዳ የትራንስፖርት አገልግሎት ለሃገራዊ ህዳሴ በሚል መሪ ቃል የእግር ጉዞ ተደረገ። በዛሬው ዕለት ከሀረሪ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የትራንስፖርትና መንገድ ቢሮ እንዲሁም ትምህርት ቢሮ ጋር በመሆን የእግር ጉዞ ተደርጓል። የሀረሪ…

በፒያሳ አካባቢ በ7 የንግድ ሱቆች ላይ የእሳት አደጋ ደረሰ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 6 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ፒያሳ አካባቢ በሚገኙ ሰባት የንግድ ሱቆች ላይ የእሳት አደጋ ደረሰ፡፡ 4 ሰዓት ከ40 ደቂቃ ላይ በተከሰተው በዚህ እሳት አደጋ ሰባት ሱቆች ላይ ቃጠሎ የደረሰ ሲሆን፥ ከእነዚህ ውስጥ ሁለት ሱቆች ሙሉ…