Fana: At a Speed of Life!

ሀዲያ ሆሳዕና እና ሐዋሳ ከተማ 2 አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ስምንተኛ ሣምንት ጨዋታ ሀዲያ ሆሳዕና ከሐዋሳ ከተማ ሁለት አቻ በሆነ ውጤት ተለያዩ፡፡ የሀዲያ ሆሳዕናን ግቦች÷ ፀጋዬ ብርሃኑ በ25ኛው እና መለሰ ሚሻሞ በ85ኛው ደቂቃ አስቆጥረዋል፡፡ የሐዋሳ ከተማን ግቦች…

የዓለም ምግብ ፕሮግራም ዕርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ትግራይ ክልል መግባታቸውን አስታወቀ

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 7 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰብአዊ ዕርዳታ የጫኑ ከባድ ተሽከርካሪዎች ትግራይ ክልል መግባታቸውን የዓለም ምግብ ፕሮግራም አስታወቀ። ተሽከርካሪዎቹ በጎንደር አድርገው ወደ ትግራይ ክልል መግባታቸውንም ነው የገለጸው። አልሚ ምግቦቹ በቀጣዮቹ ቀናት ውስጥ ለህብረተሰቡ…

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሦስተኛ ደረጃ ሕክምና ለሚሰጡ የጤና ተቋማት ብድር ሊሰጥ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቁና በውጭ ሀገራት የሚሰጡ የሦስተኛ ደረጃ የሕክምና አገልግሎቶችን በሀገር ውስጥ መስጠት ለሚችሉ የጤና ተቋማት ብድር መስጠት ሊጀምር ነው፡፡ ሦስተኛ ደረጃ (ተርሸሪ ሌቭል) ሆስፒታል ዘመናዊ መሣሪያዎችን…

ሚኒስትሮች እና በኢትዮጵያ የጣሊያን አምባሳደር የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል፣ የሥራ እና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል እና በኢትዮጵያ የጣሊያን አምባሳደር አጎስቲኖ ፓሌሴ የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክን ጎበኙ፡፡ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ ሥራ አስኪያጅ…

በሲዳማ ክልል የሌማት ትሩፋትን የማስተዋወቅ መርሐ ግብር ተካሔደ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሲዳማ ክልል በሸበዲኖ ወረዳ በፉራ ቀበሌ የሌማት ትሩፋትን የማስተዋወቅ መርሐ ግብር ተካሔደ፡፡ በመርሐ ግብሩ ላይ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞን ጨምሮ የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡ መርሐ ግብሩ…

የኢትዮቴሌኮምን 40 በመቶ ድርሻ ለመሸጥ ዓለም አቀፍ ጨረታ ዛሬ ይወጣል

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮ ቴሌኮም እና ሳፋሪኮምን የሚቀላቀለው ዓለም አቀፍ የቴሌኮም ኩባንያ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ታህሳስ 7 ቀን 2015 ዓ.ም በሚቆይ ጨረታ ፍላጎቱን እንዲያሳውቅ ገንዘብ ሚኒስቴር ጠየቀ፡፡ የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ እና ሚኒስትር ዴኤታ ኢዮብ…

መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ ኤምባሲዎች የወታደራዊ አታሼዎች ስለ ሰላም ስምምነቱ ማብራሪያ ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በፌደራል መንግስትና በህወሓት መካከል ስለተደረሰው የሰላም ስምምነት መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ ኤምባሲዎች የወታደራዊ አታሼዎች ማብራሪያ ተሰጠ። ማብራሪያውን የሰጡት የመከላከያ የውጭ ግንኙነት እና ወታደራዊ ትብብር ዳይሬክተሩ ሜጀር ጄነራል…

የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት መደበኛ ስብስባ ጠ/ሚ ዐቢይ በተገኙበት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 6 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 2ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ስብስባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት እየተካሄደ ነው፡፡ አሁን ላይም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ…

11ኛው ዓለም አቀፍ የጥራጥሬና ቅባት እህሎች ጉባዔ ነገ ይጀመራል

አዲ አበባ፣ ሕዳር 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 11ኛው ዓለም አቀፍ የጥራጥሬና ቅባት እህሎች ጉባዔ ነገ እና ከነገ በስቲያ በአዲስ አበባ ሸራተን አዲስ ሆቴል ይካሄዳል፡፡ የኢትዮጵያ ጥራጥሬ፣ ቅባት እህሎች እና ቅመማ ቅመም አዘጋጅቶ ላኪዎች ማኅበር ምክትል ፕሬዚዳንት ኤዳኦ አብዲ እንደገለጹት÷…

ሩሲያ ከአፍሪካ ጋር ያላትን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር እየሠራች መሆኗን ገለጸች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ ከአፍሪካ ጋር ያላትን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር እየሠራች መሆኗን የሀገሪቱ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የፕሬዚዳንቱ አማካሪ ተናገሩ፡፡ በሩሲያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ዓለማየሁ ተገኑ ከሩሲያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የፕሬዚዳንቱ…