Fana: At a Speed of Life!

የብድር አያያዝ ውሎችና ሁኔታዎችን በተመለከተ ግልፅ አሰራርን የበለጠ ማጎልበት ይገባል – ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በተበዳሪው ሀገር እና በአበዳሪዎች ኮሚቴ መካከል የብድር አያያዝ ውሎችና ሁኔታዎችን ይፋ በማድረግ ግልፅ አሰራርን የበለጠ ማጎልበት እንደሚገባ የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ገለጹ። የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በዋሽንግተን ዲሲ…

የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ማሻሻያ የሚታይ ውጤት እያስመዘገበ ነው – አቶ ማሞ ምህረቱ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም ጠንካራ እና የሚታይ ውጤት እያስመዘገበ ነው ሲሉ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ ገለፁ። ባንክ ገዥው በ2025 አይኤምኤፍ እና የዓለም ባንክ ስብሰባ ላይ፤ ኢትዮጵያ ከ50 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ…

10 ነጥብ 7 ሚሊየን የኢትዮ ቴሌኮም የአክሲዮን ድርሻዎች ተሽጠዋል

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮ ቴሌኮም የ10 በመቶ አክሲዮን ሽያጭ 10 ነጥብ 7 ሚሊየን የአክሲዮን ድርሻዎች መሸጣቸውን ኢትዮ ቴሌኮም አስታወቀ። የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ የ10 በመቶ የአክሲዮን ሽያጭን በተመለከተ በሰጡት መግለጫ፤…

የሞሮኮ ሮያል አርሚ ከፍተኛ ልዑክ የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አሥተዳደርን ጎበኘ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሞሮኮ ሮያል አርሚ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል መሐመድ በሪድ የተመራ የሞሮኮ ሮያል አርሚ ከፍተኛ ልዑክ በኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አሥተዳደር ጉብኝት አድርጓል። የአሥተዳደሩ ዋና ዳይሬክተር ትዕግስት ሃሚድ በዚሁ ወቅት፤ የኢትዮጵያን የሳይበር…

በኦሮሚያ ክልል 5 ነጥብ 5 ሚሊየን ኩንታል ማዳበሪያ ለዩኒየኖችና ማኅበራት ደረሰ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ለ2017/18 የመኸር ወቅት የሚውል 5 ነጥብ 5 ሚሊየን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ወደ ዩኒየኖችና ማኅበራት መድረሱን የኦሮሚያ ክልል ኅብረት ሥራ ማስፋፈያ ኤጀንሲ አስታወቀ። ማዳበሪያው በጊዜ በመድረሱ ሥርጭቱም በአግባቡ እየተከናወነ መሆኑን…

በተማሪዎችና መምህራን የሚሰሩ የፈጠራ ስራዎች ወደ ተሻለ ደረጃ እንዲደርሱ ድጋፍ ይደረጋል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በተገኙበት 10ኛው ከተማ አቀፍ የተማሪዎችና የመምህራን የሳይንስና የፈጠራ ስራ አውደ ርዕይ ተከፍቷል። አውደ ርዕዩ "በፈጠራ ስራ የተካነ ትጉህ ትውልድ ለሀገር ብልጽግና" በሚል መሪ ሐሳብ…

ከ356 ሺህ በላይ አዳዲስ ደንበኞች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ሆኑ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ባለፉት ዘጠኝ ወራት 356 ሺህ 935 አዳዲስ ደንበኞች የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ መሆናቸው አስታውቋል፡፡ ሰሜን አዲስ አበባ 4 ሺህ 440፣ ባሌ ሮቤ 9 ሺህ 219 እና ሆሳዕና 14 ሺህ 83 ደንበኞች አዳዲስ…

ዘርፉ ለሀገሪቱ ትላልቅ ፕሮጀክቶች አፈፃፀም የላቀ አስተዋፅኦ አበርክቷል – ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ዘርፉ ለሀገሪቱ ትላልቅ ፕሮጀክቶች አፈፃፀም የላቀ አስተዋፅኦ አበርክቷል ሲሉ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) ገለጹ። ሚኒስቴሩ እና ተጠሪ ተቋማት በ2017 በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት ተስፋ…

ካዛንቺስ ዛሬ የጋራ ጥረት እና ለውጥ ሽልማታችን ሆኖ ተገኝቷል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 14፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የተጎሳቆሉ እና በእጅጉ የተጎዱ ቤቶች እና ከባቢ መገኛ የነበረው ካዛንቺስ ዛሬ የጋራ ጥረት እና ለውጥ ሽልማታችን ሆኖ ተገኝቷል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት…

አየር መንገዱ ከካሜሩን ለሚጓዙ ሃጃጆች የበረራ አገልግሎት ለመስጠት ቁርጠኛ መሆኑን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 14፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከካሜሩን ለሚጓዙ ሃጃጆች እንዲሁም ወደ ያውንዴ እና ዱዋላ የሚያደርገውን መደበኛ የበረራ አገልግሎት ለመስጠት ቁርጠኛ መሆኑን ገልጿል። የካሜሩን የግዛት አስተዳደር ሚኒስትር እና የሃጅ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ፖል አታንጋ ንጂ…