Fana: At a Speed of Life!
Browsing Category

ስፓርት

አትሌት ሳሙኤል በአንድ ማይል የ2020ን ሁለተኛ ፈጣን ሰዓት አስመዘገበ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያዊው አትሌት ሳሙኤል ተፈራ በተያዘው የፈረንጆቹ ዓመት በአንድ ማይል ርቀር ሩጫ ሁለተኛውን የዓለም ፈጣን ሰዓት አስመዘገበ። በትናንትናው ዕለት በአየርላንድ አትሎን የአንድ ማይል የቤት ውስጥ ውድድር ተካሂዷል። አትሌት ሳሙኤል ተፈራ…

በፕሪሚየር ሊጉ ወላይታ ድቻ ሃድያ ሆሳዕናን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 3፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 13ኛ ሳምንት የቀኑ ብቸኛ ጨዋታ በሃዋሳ ከተማ ስታዲየም ዛሬ ተካሂዷል። በዚህም ወላይታ ድቻ ሃድያ ሆሳዕናን  1 ለ 0 በሆነ ውጤት  አሸንፏል። የወላይታ ድቻን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ደጉ ደበበ ከመረብ አገናኝቷል።…

በፕሪሚየር ሊጉ ሲዳማ ቡና አዳማ ከተማን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ አንድ ጨዋታ ተካሄዷል። በሜዳው አዳማ ከተማን ያስተናገደው ሲዳማ ቡና ጨዋታውን 3 ለ 2 ማሸነፍ ችሏል። የማሸነፊያ ጎሎችን አማኑኤል እንዳለ፣ ዳዊት ተፈራ እና ሀብታሙ ገዛኸኝ ማስቆጠር ችለዋል።

በፕሪሚየር ሊጉ ፋሲል ከነማ መቐለ 70 እንደርታን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 13ኛ ሳምንት የቀኑ ብቸኛ ጨዋታ በመቐለ ተካሄዷል። መቐለ ላይ በተካሄደው ጨዋታ ፋሲል ከነማ መቐለ 70 እንደርታን 2 ለ 0 በማሸነፍ የፕሪሚየር ሊጉ መሪ ሆኗል። የፋሲል ከነማ የማሸነፊያ ግቦች የፕሪሚየር ሊጉን…

ሀዲያ ሆሳዕና አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያምን አዲሱ የክለቡ አሰልጣኝ አድርጎ ሾመ

አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሀዲያ ሆሳዕና አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያምን አዲሱ የክለቡ አሰልጣኝ አድርጎ ሾመ። ከአሰልጣኝ ግርማ ታደሰ ጋር የተለያየው ሀዲያ ሆሳዕና የቀድሞውን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲና አርባምንጭ ከተማ አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያን…

ሀዲያ ሆሳዕና የቅጣት ውሳኔ ተላለፈበት

አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀዲያ ሆሳዕና የእግር ኳስ ክለብ የቅጣት ውሳኔ ተላለፈበት። ቅጣቱ ከወልቂጤ ከተማ ጋር በነበረው ጨዋታ አንዳንድ የሀዲያ ሆሳዕና ደጋፊዎች ከስፖርታዊ ጨዋነት ውጭ ጨዋታው ከተጠናቀቀ በኋላ ከሜዳ ውጭ ከፀጥታ ሀይሎች ጋር በፈጠሩት ግርግር ምክንያት…

አትሌት አባዲ ሃዲስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በበርካታ ዓለም አቀፍ እና አህጉራዊ ውድድሮች ኢትዮጵያን ወክሎ የተወዳደረው የ22 ዓመቱ ወጣት አትሌት አባዲ ሀዲስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። አትሌት አባዲ በኦሎምፒክ እና በዓለም ሻምፒዮና ኢትዮጵያን በመከወል በተለያዩ ውድድሮች ተሳትፏል።…

ድሬዳዋ ከተማ እግር ኳስ ክለብ አሰልጣኙን አሰናበተ

አዲስ አበባ፣ ጥር 26፣2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በፕሪሚየር ሊጉ በወራጅ ቀጠና ውስጥ የሚገኘው ድሬዳዋ ከተማ እግር ኳስ ክለብ የቡድኑን ዋና አሰልጣኝ ስምዖን አባይን አሰናበተ። ድሬዳዋ ከተማ ከባለፉት 12 የፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ማግኘት ካለበት 36 ነጥብ ውስጥ 13 ነጥብ ብቻ በመሰብሰብ…

የቶኪዮ ኦሊምፒክ 2020 ዝግጅትን አስመልክቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ዝግጅትን አስመልክቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር አካሄደ። በመድረኩ ላይ የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ዝግጅትን አስመልክቶ የመነሻ ሰነድ፣ ለቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ስለ ስፖርት ህክምና እና…