Fana: At a Speed of Life!
Browsing Category

ዓለምአቀፋዊ ዜና

በዛምቢያ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የተቃዋሚ ፓርቲው ዕጩ አሸነፉ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በዛምቢያ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የተቃዋሚ ፓርቲው ዕጩ ሃካይንዴ ሂቺሌማ አሸነፉ፡፡ የዛምቢያ ምርጫ ኮሚሽን ጉዳዩን አስመክቶ ባወጣው መግለጫ÷ በሀገሪቱ ባሳለፍነው ሳምንት በተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የተቃዋሚው መሪ ሃካይንዴ ሂቺሌማ ማሸነፋቸውን…

በሃይቲ በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ቢያንስ የ304 ሰዎች አለፈ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሃይቲ በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ቢያንስ የ304 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰማ፡፡ በሬክተር ስኬር 7 ነጥብ 2 በተመዘገበው የመሬት መንቀጥቀጥ ሕይወታቸው ካለፈ ሰዎች በተጨማሪ ከ 1 ሺህ 800 በላይ ሰዎች ቆስለዋል። ቅዳሜ ማለዳ…

አልጄሪያ ከሠደድ እሳት አደጋዎች ጋር በተያያዘ 22 ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር አዋለች

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 7፣2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አልጄሪያ በደኖቿ ላይ ከተከሰቱት የሰደድ እሳት አደጋዎች ጋር በተያያዘ የጠረጠረቻቸውን 22 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ማዋሏ ተገለፀ፡፡ ሀገሪቱ በቁጥጥር ስር ያዋለቻቸው ግለሰቦች ተቀጣጣይ ቁሶችን ተጠቅመው አደጋውን አድርሰዋል ብላ የጠረጠረቻቸውን መሆኑ…

የማዳጋስካር ፕሬዚዳንት ሁሉንም ሚኒስትሮች አሰናበቱ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 7፣2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዳጋስካር ፕሬዚዳንት አንድሪ ራጆሊና ሁሉንም የሃገሪቱ ሚኒስትሮች ማሰናበታቸው ተሰማ፡፡ ፕሬዚዳንቱ ሁሉንም ሚኒስትሮች ያሰናበቱበት ምክንያት እንዳልታወቀም ነው የተገለፀው፡፡ ፕሬዚዳንቱ አንዳንዶቹን ሚኒስትሮች አግኝተው የሥራ አፈፃፀማቸው ዝቅተኛ…

የዓለም ጤና ድርጅት ሦሥት በሙከራ ላይ የሚገኙ የኮቪድ 19 መድኃኒቶችን ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 6፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም ጤና ድርጅት÷ በኮቪድ 19 ቫይረስ ምክንያት ሕይወታቸውን ሊያጡ የሚችሉ ሰዎች ቁጥር ይቀንሳል ያላቸውን ሦሥት በሙከራ ላይ ያሉ መድኃኒቶች ይፋ አደረገ፡፡ በሙከራ ላይ ያሉት መድኃኒቶችም አርቴሱኔት፣ ኢሜቲኒብ እና ኢንፊሊክሲማብ እንደሆኑ ነው…

በዛምቢያ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 6፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በዛሬው ዕለት በዛምቢያ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እየተካሄደ መሆኑ ታውቋል፡፡ የዛምቢያ ምርጫ ቦርድ ኮሚሽን ግልፅና ተዓማኒነት ላለው ምርጫ እንደሚሰራ አስታውቋል፡፡ የምርጫውን ሂደትም ዓለም አቀፋዊ ታዛቢዎች እንደሚከታተሉት ታውቋል፡፡…

በአልጄሪያ የሰደድ እሳት አደጋ የ42 ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አልጄሪያ ውስጥ በተነሱ የሰደድ እሳት አደጋዎች እስካሁን የ42 ሰዎች ሕይወት እንዳለፈ ተገለፀ፡፡ የ25 ወታደሮች ሕይወት የተቀጠፈው በካቢሊ ተራራማ አካባቢ ባለ ጥቅጥቅ ደን ውስጥ የተከሰተውን ሰደድ እሳት ለማጥፋት ሲሰሩ እንደሆነም ተጠቅሷል፡፡…

ቻይና እና ሩሲያ መጠነ ሰፊ ጥምር ወታደራዊ ልምምድ እያደረጉ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና እና ሩሲያ በቻይና መካከለኛው ሰሜን አካባቢ መጠነ ሰፊ የጋራ ወታደራዊ ልምምድ እያደረጉ ነው፡፡ “ትብብር - 2021” በተሰኘው በዚህ የጋራ ልምምድ 10 ሺህ የሚደርሱ የምድር እና የአየር ሃይል አባላት ተሳትፈዋል፡፡ ሩሲያ ለልምምዱ ተዋጊ…

በጊኒ የማርበርግ ቫይረስ ተከሰተ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 4፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ጊኒ ለመጀመሪያ ጊዜ የማርበርግ ቫይረስ መከሰቱ ተገለጸ፡፡ እስካሁን ድረስ በቫይረሱ አንድ ሰው ተጠቅቶ ሕይወቱ እንዳለፈ የሀገሪቱ የጤና ባለሙያዎች አረጋግጠዋል፡፡ የቫይረሱ ዝርያ የኢቦላ በሽታን ከሚያስከትለው ቫይረስ…

በአሜሪካ ግዛቶች ደን ላይ ከደረሱ የሰደድ እሳት አደጋዎች የካሊፎርኒያው በአስከፊነቱ 2ኛ ደረጃን ይዟል

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 3፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ ግዛት በሰሜን ካሊፎርኒያ ደን የተነሳው እና እየተባባሰ የመጣው የሰደድ እሳት አደጋ በሀገሪቷ ታሪክ ደን ላይ ከደረሱ የሰደድ እሳት አደጋዎች በ2ኛ ደረጃ ይቀመጣል ተባለ፡፡ እየተባባሰ በመጣው የሰደድ እሳት አደጋ ጋር ተያይዞ…