Fana: At a Speed of Life!
Browsing Category

ዓለምአቀፋዊ ዜና

የ72 ዓመቱ የዙሉው ንጉስ ጉድዊል ዝዌሊቲኒ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 3 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የ72 ዓመቱ የደቡብ አፍሪካ ዙሉ ንጉስ ጉድዊል ዝዌሊቲኒ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። ንጉሱ ለሳምንታት በሆስፒታል ከቆዩ በኋላ ዛሬ በሞት መለየታቸውን ከንጉሱ ቤተሰብ የወጣው መግለጫ አረጋግጧል። የንጉሳዊያኑ ቤተሰብ ባስተላለፉት መልዕክትም…

ሱዳን በዳርፉር የሚገኘው የሰላም አስከባሪ ኃይል የሚወጣበት ጊዜ እንዲዘገይ ጠየቀች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 2፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሱዳን በዳርፉር የሚገኘው የተባበሩት መንግስታት የሰላም አስከባሪ ኃይል /ዩናሚድ/ የሚወጣበት ጊዜ እንዲዘገይ ጠየቀች፡፡ ካርቱም ካልማ እና ሶርቶኒይ በተባሉ የጸጥታ ስጋት ባለባቸው ሁለት ካምፖች ሰላም አስከባሪው እንዲቆይ ፍላጎት አላት ተብሏል፡፡…

የታንዛኒያ ፕሬዚዳንት ማጉፉሊ ˝በኮቪድ 19 ተይዘው በኬንያ በሚገኝ ሆስፒታል ገብተዋል˝ ተባለ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮሮና ቫይረስ በዓለም ላይ ከተከሰተ ጀምሮ የቫይረሱን እውነተኛነ በመጠራጠርና በማጣጣል የሚታወቁት የታንዛኒያው ፕሬዚዳንት ጆን ማጉፉሊ በኮሮና ቫይረስ ተይዘው ሆስፒታል መግባታቸው እየተዘገበ ነው። ፕሬዚዳንቱ በኬንያ በሚገኝ ሆስፒታል መግባታቸውን…

ፈረንሳይ ከ50 ዓመታት በላይ የሆናቸው የቅኝ ግዛት ዘመን መረጃዎችን ይፋ ልታደርግ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን የቅኝ ግዛት ዘመን መረጃዎች ማግኘት የሚቻልበትን ሂደት የሚያቀል ውሳኔ አሳለፉ። ይፋ የሚደረጉት የቅኝ ግዛት ዘመን መረጃዎች የአልጀሪያ የነፃነት ጦርነትን ጨምሮ ከ50 ዓመታት በላይ የሆናቸው መረጃዎች ናቸው…

አይ ሲ ሲ በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ለጥቃት ሰለባዎች 30 ሚሊየን ዶላር ፈረደ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት /አይ ሲ ሲ/ ዳኞች በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በአማጽያን በተፈጸመ ጥቃት ሰለባ ለሆኑ ሰዎች 30 ሚሊየን ዶላር እንዲሰጣቸው ፈረደ፡፡ የፍርድ ቤቱ 30 ሚሊየን ዶላር ውሳኔ በአማጺ መሪው ቦስኮ…

ስልጣናቸውን በቀጣዩ ወር የሚለቁት የኒጀር ፕሬዚዳንት የ5 ሚሊየን ዶላር ሽልማት አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከሁለት ዙር የስልጣን ዘመን በኋላ ስልጣናቸውን በቀጣዩ ወር የሚለቁት የኒጀሩ ፕሬዚዳንት መሀመዱ የሱፍ የ2020 የአለም ትልቁን የመሪዎች ሽልማት አሸነፉ። በዚህም በሱዳናዊው ቢሊየነር የተቋቋመውን የሞ ኢብራሂም ፋውንዴሽን ሽልማት በማሸነፋቸው 5…

በየመን በማረሚያ ቤት በደረሰ እሳት አደጋ የ30 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰማ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 29 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በየመን በማረሚያ ቤት በደረሰ እሳት አደጋ የ30 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰማ፡፡ አደጋው በስደተኞች ማረሚያ ቤት የደረሰ መሆኑ ተገልጿል፡፡ የእሳት አደጋው በመዲናዋ ሰንዓ ሳዑዲ ዓረቢያ ካደረሰችው ጥቃት በኋላ የተከሰተ ነው ተብሏል፡፡…

በኢኳቶሪያል ጊኒ በደረሰ ፍንዳታ 15 ሰዎች ለህልፈት ተዳረጉ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢኳቶሪያል ጊኒ በተከሰተ ተከታታይ ፍንዳታ 15 ሰዎች ህይወታቸው አለፈ፡፡ ባታ በተባለው ከተማ በደረሰው ፍንዳታ ሕይወታቸው ካለፈው በተጨማሪ 500 ሰዎች ቆስለዋል ነው የተባለው፡፡ የሃገሪቱ መንግስት…

ሞዛምቢክ የኮሮና ቫይረስ ክትባት ዘመቻ ዛሬ ትጀምራለች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሞዛምቢክ የኮሮና ቫይረስ ክትባትን በዘመቻ መልክ ዛሬ መስጠት ትጀምራለች፡፡ በዚህም የጤና ባለሙያዎች በሥራ ወቅት ለቫይረሱ ከፍተኛ ተጋላጭ በመሆናቸው ክትባቱን በቅድሚያ ይወስዳሉ ነው ተባለው፡፡…

የአፍሪካ ሃገራት የኮቪድ-19 ክትባት መስጠት ጀመሩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 26፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ሃገራት የኮቪድ-19 ክትባት መስጠት መጀመራቸው ተነገረ፡፡ ግብጽ እና ጋና የኮቪድ- 19 ክትባት መስጠት የጀመሩ ሲሆን፤ ናይጄሪያን ጨምሮ ሌሎች ሃገራትም ክትባቱን ዛሬ ይጀምራሉ ተብሏል፡፡ እስካሁን በአህጉሪቱ በኮቪድ-19 የተያዙ…