Browsing Category
ዓለምአቀፋዊ ዜና
በአፍሪካ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ3 ነጥብ 2 ሚሊየን አለፈ
አዲስ አበባ ፣ ጥር 9፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ አህጉር በኮሮናቫይረስ (ኮቪድ-19) የአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠርና መከላከል ማዕከል (ሲዲሲ አፍሪካ) በአህጉሩ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ3 ነጥብ 2 ሚሊየን ማለፉን አስታውቋል።
የማዕከሉ በፌስ ቡክ ገጹ ላይ…
ዩዌሪ ሙሴቬኒ በኡጋንዳ የተካሄደውን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ማሸነፋቸው ተረጋገጠ
አዲስ አበባ ፣ ጥር 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኡጋንዳ የተካሄደውን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ዩዌሪ ሙሴቬኒ ማሸነፋቸው የሀገሪቱ ምርጫ ኮሚሽን ይፋ አደረገ።
ይህም ባለፉት 35 ዓመታት ኡጋንዳን የመሩት የ75 ዓመቱ ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ለቀጣዩቹ አምስት አመታት ሀገሪቱን ይመራሉ።
የፕሬዚዳንቱ…
ሱዳናውያን ተቃዋሚዎች ህገ ወጥ ተግባር የሚፈፀምባቸው እስር ቤቶች እንዲዘጉ ተቃውሞ አሰሙ
አዲስ አበባ ፣ ጥር 7 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በርካታ ሱዳናውያን ሁሉም ህገ ወጥ እስር ቤቶች እንዲዘጉ በካርቱም በተቃውሞ ሰልፍ አሰምተዋል።
ሱዳናውያኑ ተቃውሟቸውን ያሰሙት የሀገሪቱ ፈጥኖ ደራሽ ሀይል አንድን ግለሰብ በማሰቃየት እና በመግደል ክስ ከቀረበበት በኋላ ነው።
የሀገሪቱ ፈጥኖ…
ጆ ባይደን የ1 ነጥብ 9 ትሪሊየን ዶላር የኢኮኖሚ ማገገሚያ ማዕቀፍ ይፋ አደረጉ
አዲስ አበባ ፣ ጥር 7 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የ1 ነጥብ 9 ትሪሊየን ዶላር የኢኮኖሚ ማገገሚያ ማዕቀፍ ይፋ አደረጉ፡፡
በፕሬዚዳንቱ ይፋ የሆነው ይህ የኢኮኖሚ ማነቃቂያ እቅድ በኮሮና ቫይረስ የተጎዳውን የአሜሪካን ኢኮኖሚ ለመታደግ ያለመ ነው ተብሏል፡፡…
ፕሬዚዳንት ትራምፕ የካፒቶል ሂሉን ሁከት አነሳስተዋል በሚል እንዲከሰሱ ተወሰነ
አዲስ አበባ ፣ ጥር 6 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የካፒቶል ሂሉን ሁከት አነሳስተዋል በሚል እንዲከሰሱ ውሳኔ ተላለፈ።
የህግ መምሪያ ምክር ቤት እንደራሴዎች ፕሬዚዳንቱ ባለፈው ሳምንት የተከሰተውን የካፒቶል ሂል ሁከት በመምራት እንዲከሰሱ በአብላጫ ድምጽ…
ኤፍ ቢ አይ የታጠቁ የትራምፕ ደጋፊዎች የተቃውሞ ሰልፍ ሊያደርጉ ይችላሉ ሲል አስጠነቀቀ
አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ የወንጀል ምርመራ ቢሮ (ኤፍ ቢ አይ) ታጣቂ የዶናልድ ትራምፕ ደጋፊዎች ጆ ባይደን ቃለ መሃላ ከመፈፀማቸው በፊት በመላ አሜሪካ የተቃውሞ ሰልፍ ሊያደርጉ ይችላሉ ሲል አስጠነቀቀ።
የታጠቁ ቡድኖች ከስምንት ቀን በኋላ ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት…
የአሜሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕን ከስልጣን እንዲያነሷቸው ግፊት እየተደረገ ነው
አዲስ አበባ ፣ ጥር 3 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ዴሞክራቶች የአሜሪካው ምክትል ፕሬዚዳንት ማይክ ፔንስ ዶናልድ ትራምፕን ከስልጣን እንዲያነሷቸው ግፊት እያደረጉ ነው።
በተለይ የአሜሪካ ኮንግረስ አፈ ጉባዔ ናንሲ ፔሎሲ ዶናልድ ትራምፕ ባለፈው ሳምንት በካፒቶል ሂል ከነበረው ሁከት ጋር በተያያዘ…
በጃፓን ሌላ አይነት የኮሮና ቫይረስ ተገኘ
አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በጃፖን ሌላ አይነት የኮሮና ቫይረስ መገኘቱን የሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።
በብሪታኒያ እና ደቡብ አፍሪካ ከተገኘው የኮሮና ቫይረስ ጋር በከፊል ተመሳሳይነት ያለው ቫይረስ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።
የጃፓን የጤና ሚኒስቴር ቫይረሱ ከብራዚል…
በኢንዶኔዥያ 50 ተጓዦችን ይዞ ሲበር የነበረ ቦይንግ 737 የደረሰበት አልታወቀም
አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2013 (ኤፍቢሲ) በኢንዶኔዥያ 50 ተጓዦችን አሳፍሮ ሲበር የነበረው ንብረትነቱ የስሪዊጃያ አየር መንገድ የሆነ ቦይንግ 737 አውሮፕላን የደረሰበት አልታወቀም፡፡
አውሮፕላኑ ከኢንዶኔዥያ ዋና ከተማ ጃካርታ ከተነሳ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ነው መሰወሩ የተነገረው፡፡…
ትዊተር ፕሬዚዳንት ትራምፕን በዘላቂነት አገደ
አዲስ አበባ ፣ ጥር 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ትዊተር የአሜሪካውን ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዘላቂነት ማገዱን አስታወቀ፡፡
ኩባንያው ፕሬዚዳንቱን ተጨማሪ የአመፅ ድርጊቶችን ሊቀሰቅስ ይችላሉ በሚል ስጋት ማህባረዊ የትስስር ገጹን እንዳይጠቀሙ ለዘለቄታው እንደከለከላቸው አስታውቋል፡፡…