Browsing Category
ዓለምአቀፋዊ ዜና
ትራምፕና ባይደን የመጨረሻ ፕሬዚዳንታዊ ክርክር አደረጉ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕና የቀድሞው ምክትል ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የመጨረሻውን የ2020 ፕሬዚዳንታዊ ክርክር አካሂደዋል፡፡
ሌሊት በተካሄደው ክርክር የኮሮና ቫይረስ፣ የአየርንብረት እና በዘር ላይ ያተኮሩ ጉዳዮች መድረኩን ተቆጣጥረውት…
ሰዓድ ሃሪሪ በድጋሚ የሊባኖስ ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን ተሾሙ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከዓመት በፊት ስልጣን የለቀቁት የሊባኖሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሰዓድ ሃሪሪ በድጋሚ መመረጣቸው ተሰማ፡፡
ሃሪሪ በፓርላማ ድጋፍ የተነፈጋቸውን ሙስጠፋ አዲብን በመተካት ነው በድጋሚ ጠቅላይ ሚኒስትር የሆኑት፡፡
ሃሪሪ በፓርላማ ውስጥ መንግስት…
የእስራኤል ባለስልጣናት በዚህ ሳምንት ሱዳንን ሊጎበኙ ነው
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የእስራኤል ከፍተኛ ባለስልጣናት በዚህ ሳምንት ሱዳንን ሊጎበኙ መሆኑ እየተነገረ ነው፡፡
ይህ የተሰማው አንድ የንግድ አውሮፕላን ከቴልአቪቭ ተነስቶ ካርቱም ማረፉ ከተነገረ በኋላ ነው ተብሏል፡፡
በዚህ ሳምንት ይካሄዳል በተባለው ጉብኝት ልዑኩን…
የአሜሪካ የምርመራ ቢሮ ኢራንና እና ሩሲያ የመራጮች መረጃ እንዳላቸው አስታወቀ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአሜሪካ የጸጥታ ኃላፊዎች ኢራንና እና ሩሲያ የመራጮች መረጃ አላቸው ሲሉ ገለጹ፡፡
የአሜሪካ ብሔራዊ ደህንነት ዳይሬክተር ጆን ራትክሊፍ ኢራን ለዴሞክራት መራጮች ዛቻ ያዘሉ የኢሜል መልዕክቶችን ልከዋል በሚል ተጠያቂ አድርገዋል፡፡
በተለይም…
በስፔን ኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ከ1 ሚሊየን አለፈ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በስፔን ኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎቸ ቁጥር ከአንድ ሚሊየን ማለፉ ተነገረ፡፡
ስፔን በአውሮፓ ከፍተኛ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከተመዘገበባቸው ሃገራት የመጀመሪያዋ ሆናለች ነው የተባለው፡፡
…
የሌጎስ አስተዳዳሪ ነዋሪዎች እንዲረጋጉ ጥሪ አቀረቡ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በናይጀሪያ ለተቃውሞ በወጡ ሰልፈኞች ላይ ተኩስ መከፈቱን ተከትሎ የሌጎስ አስተዳዳሪ ባባጂዴ ሳንዎ ኦሉ የከተማዋ ነዋሪዎች እንዲረጋጉ ጥሪ አቀረቡ፡፡
ናይጀሪያውያን ከሰሞኑ ፖሊሶች የሚፈጽሙትን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ተከትሎ ለተቃውሞ አደባባይ…
ትራምፕ በቻይና የባንክ ደብተር አላቸው ተባለ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ቻይናን በመተቸት የሚታወቁት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሀገሪቱ የባንክ ደብተር እንዳላቸው ኒውዮርክ ታይምስ ዘገበ፡፡
እንደ ኒውዮርክ ታይምስ ዘገባ ፕሬዚዳንቱ በቻይና የባንክ ደብተር እንዳላቸው አምነዋል፡፡
የባንክ ደብተሩ…
በህገ ወጥ መልኩ ወደ አሜሪካ ሊገቡ የነበሩ ጥንታዊ የካሜሩን የድንጋይ ላይ ቅርጻ ቅርጾች ተያዙ
አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 11 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአሜሪካ የጉምሩክ ባለሥልጣናት ሐሰተኛ ሰነዶችን በመጠቀም በሕገወጥ መንገድ ከካሜሩን ወደ አሜሪካ ሊገባ የነበረ በርካታ ጥንታዊ የድንጋይ ቅርጻ ቅርጾች መያዛቸውን አስታወቁ።
የድንጋይ ቅርጻ ቅርጾቹ የተያዙት በሚያሚ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን…
ብሪታንያ በአውሮፕላን ማረፊያዎች የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ጀመረች
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ብሪታንያ በአውሮፕላን ማረፊያዎች ውስጥ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ መጀመሯ ተነግሯል።
በዛሬው እለት ከለንደን ሂትሮ አውሮፕላን ማረፊያ ወደ ሆንግ ኮንግ በረራ ያደረጉ መንገደኞች ፈጣን የኮሮና ቫይረስ ምርመራ አገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆናቸውም ተነግሯል።…
በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ታጣቂዎች 900 እስረኞችን አስለቀቁ
አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 10 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በምስራቃዊ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ቤኒ ከተማ ታጣቂዎች 900 እስረኞችን ማስለቀቃቸው ተገለፀ።
ከካንግባዩ እስር ቤት ካመለጡት 900 እስረኞች መካከል የታጣቂ ቡድን አባላት እንደሚገኙበት ቢቢሲ የከተማዋን ከንቲባ ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።…