Browsing Category
ዓለምአቀፋዊ ዜና
ግብፅ በሽብር የተከሰሱ 112 ሰዎች የዕድሜ ልክ እስራት ተፈረደባቸው
አዲስ ሰበባ ፣ መጋቢት 1 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በግብጽ በሽብር ድርጊት ተሳትፈዋል የተባሉ 112 ሰዎች የእድሜ ልክ እስራት ተፈረደባቸው ፡፡
ግለሰቦቹ በግብፅ ወታደራዊ ፍርድ ቤት በሽብር ወንጀል በመሳተፍ ነው ጥፋተኛ የተባሉት
ተከሳሾቹ በፍተሻ ጣቢያዎች ላይ ጥቃቶችን በማድረስ ፣ ረዳት…
አሜሪካ በአፍጋኒስታን የሚገኙ ወታደሮቿን ማስወጣት ጀመረች
አዲስ አበባ፣መጋቢት 1፣2012 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ በአፍጋኒስታን የሚገኙ ሰላም አስከባሪ ወታደሮቿን ማስወጣት ጀምራለች።
አሜሪካ እና በአፍጋኒስታን የሚንቀሳቀሰው ታጣቂ ቡድን ታሊባን በቅርቡ በሀገሪቱ ሰላም ማስፈን የሚያስችል ስምምነት መፈራረማቸው ይታወሳል።
በድርድሩ አሜሪካ በሀገሪቱ…
በቡርኪና ፋሶ ታጣቂዎች በፈፀሙት ጥቃት 43 ሰዎች ተገደሉ
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 1 ፣ 2012 ፣ (ኤፍ ቢ ሲ) በቡርኪና ፋሶ በአንድ መንደር ላይ ተፈፀመ ጥቃት 43 ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ፡፡
ታጣቂዎች ቡርኪና ፋሶ ከማሊ ጋር በምትዋሰንበት ሰሜናዊ የሀገሪቱ ክፍል በርካቶችን ሲገድሉ ስድስት ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን መንግስት ገልጿል፡፡…
ጣሊያን በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በመላው ሀገሪቱ የጉዞ እገዳ ጣለች
አዲስ አበባ፣መጋቢት 1፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጣሊያን በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በመላው ሀገሪቱ ህዝባዊ ስብሰባዎችንና የጉዞ እገዳዎችን መጣሏ ተሰምቷል፡፡
ጣሊያን በርካታ ዜጎቿን የገደለባትን የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ለመግታትና ለመቆጣጠር የተለያዩ እርምጃዎችን በመውሰድ ላይ ትገኛለች፡፡…
በኦስትሪያ በበረዶ ናዳ የ6 ሰዎች ሕይወት አለፈ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኦስትሪያ አልፕስ ተራሮች በደረሰ የበረዶ ናዳ የስድስት ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተሰምቷል።
ሰዎቹ በወቅቱ የበረዶ ሽርሽር እያደረጉ ነበር ተብሏል።
አደጋው በሁለት የተለያዩ ቦታዎች መድረሱን ፖሊስ ገልጿል።
ከሳልዝበርግ በስተደቡብ ምስራቅ…
የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ ከግድያ ሙከራ ተረፉ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ ከግድያ መኩራ መትረፋቸው ተገለፀ።
ካርቱም ውስጥ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ባጀቡት ተሽከርካሪዎች ላይ ጥቃት መፈፁሙን የሀገሪቱ መንግስት ቴሌቪዥን ዘግቧል።
የሀገሪቱ ቴሌቪዥን በዘገባው ጠቅላይ…
በጣሊያን በኮሮና ቫይረስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 366 ደረሰ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በጣሊያን በኮሮና ቫይረስ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 366 ደረሰ።
በትናንትናው ዕለት ብቻም 133 ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት ለህልፈት ተዳርገዋል።
በሰሜናዊ ጣሊያን ብቻ 16 ሚሊየን ሰዎች በለይቶ ማቆያ ውስጥ ክትትል እየተደረገላቸው ሲሆን፥ ከ7 ሺህ…
ግብጽ በአፍሪካ የመጀመሪያውን የኮሮና ቫይረስ ሞት አስመዘገበች
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 30 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ግብጽ በአፍሪካ የመጀመሪያውን የኮሮና ቫይረስ ሞት አስመዘገበች።
የሃገሪቱ ጤና ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ሟቹ የ60 አመት ጀርመናዊ ሲሆኑ፥ ከሳምንት በፊት ነበር ግብጽ የገቡት።
ግለሰቡ ግብጽ ከገቡ በኋላ በቀይ ባህር ዳርቻ መዝናኛ ሁርጋዳ…
የአልሸባብ ከፍተኛ አዛዥ የነበረው በሽር መሃመድ ኮርጋብ በሶማሊያ በተፈፀመ የአየር ጥቃት ተገደለ
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 29 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ)የአልሸባብ ከፍተኛ አዛዥ የነበረው በሽር መሃመድ ኮርጋብ በሶማሊያ በተፈፀመ የአየር ጥቃት መገደሉ ተገለፀ፡፡
አሜሪካ በፈረንጆቹ 2008 በሽር መሀመድ ኮርጋብ የሚገኝበትን ለጠቆመ 5ሚሊየን ዶላር ሽልማት አበረክታለሁ በማለት ቃል ገብታ ነበር።…
ጣሊያን የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል 16 ሚሊየን ሰዎችን በልየታ አስቀመጠች
አዲስ አበባ፣የካቲት 29፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በሰሜናዊ ጣሊያን 16 ሚሊየን ሰዎች በልየታ(በኳራንቲን) እንዲቀመጡ መደረጉ ተገለጸ፡፡
ጣሊያን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እየተስፋፋ መምጣቱን ተከትሎ በሽታውን ለመቆጣጠርና ስርጭቱን ለመቀነስ የተለያዩ…