Fana: At a Speed of Life!
Browsing Category

ዓለምአቀፋዊ ዜና

በጣሊያን በኮሮና ቫይረስ የሟቾች ቁጥር 197 ደርሷል

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 28 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በጣሊያን በኮሮና ቫይረስ የሟቾች ቁጥር 197 መድረሱን የሃገሪቱ ባለስልጣናት አስታወቁ። በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 4 ሺህ 600 መድረሱንም ነው ያስታወቁት። በአንድ ቀን ብቻ 49 ሰዎች መሞታቸውንም ገልጸዋል፤ ይህም ቫይረሱ…

በካቡል በተፈጸመ ጥቃት 27 ሰዎች ተገደሉ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 27፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአፍጋኒስታን ዋና ከተማ ካቡል በተፈጸመ ጥቃት ቢያንስ የ27 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተነገረ፡፡ ጥቃቱ የተፈጸመው በ1995 በታሊባኖች የተገደለው የሀዝራ ጎሳ መሪ አብዱል አሊ ማዛሪ መታሰቢያ በዓል ላይ ነው ተብሏል፡፡ በዚህ ጥቃት ህይወታቸው…

ሩሲያ እና ቱርክ በኢድሊብ አዲስ የተኩስ አቁም ስምምነት ደረሱ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 27፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሩሲያና ቱርክ በሶሪያዋ ኢድሊብ የደረሱት የተኩስ አቁም ስምምነት ተግባራዊ መሆን ጀምሯል። ስምምነቱ ትናንት በሞስኮ በሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና በቱርኩ አቻቸው ሬሲፕ ጣይፕ ኤርዶኻን መካከል የተደረሰ ነው። ስምምነቱ በቱርክ…

ቱርክ በድንበር አካባቢ  የሚገኙ ስደተኞች ወደ ሀገሯ እንዳይገቡ  ልታግድ ነው

አዲስ አበባ፣የካቲት 26፣2012(ኤፍ.ቢ.ሲ)ቱርክ  ከግሪክ ጋር በምትዋሰንባቸው   ድንበር አካባቢ የሚገኙ  ስደተኞች ወደ  ሀገሯ  እንዳይገቡ እየሰራች መሆኑን አስታውቃለች። ግሪክ ወደ አውሮፓ ሀገራት ለመግባት ተስፋ የሚያደርጉ በሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞችን   እንዳይገቡ እየሰራች ነው ተብሏል፡፡…

የቀድሞው የተመድ ዋና ጸሐፊ በ100 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 26፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) 5ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ የነበሩት ፔሩያዊው ጃቬር ፔሬዝ በ100 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። ጃቬር ፔሬዝ ሊማ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩ ሲሆን፥ ከላቲን አሜሪካ ድርጅቱን በዋና ጸሀፊነት…

ዴኒስ ሽሚጋል የዩክሬን ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተመረጡ

አዲስ አበባ ፣የካቲት 26 ፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) የዩክሬን ፓርላማ ዴኒስ ሽሚጋልን የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ መረጠ። የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኦሌክሲይ ሆንቻሩክ በፕሬዚዳንት ቮሎዲሚር ዜለንስኪ ጥያቄ ስልጣን ለቀዋል። ፕሬዚዳንቱ ፓርላማው ሽሚጋልን በጠቅላይ ሚኒስትርነት…

በካሊፎርኒያ ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታወጀ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 26፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካዋ ካሊፎርኒያ ግዛት አንድ ሰው በኮሮና ቫይረስ መሞቱን ተከትሎ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታወጀ። በግዛቷ የ71 ዓመት አዛውንት በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት ተዳርገዋል፤ አዛውንቱ ባለፈው ወር መነሻዋን ሳንፍራንሲስኮ ባደረገችው መርከብ ሳይሳፈሩ…

ጣሊያን ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ ትምህርት ቤቶችን ልትዘጋ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጣሊያን መንግስት ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ ትምህርት ቤቶችን እና ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን ሊዘጋ ነው። ትምህርት ቤቶቹ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ በሚል እንደሚዘጉ የሃገሪቱን ባለስልጣናት ዋቢ ያደረገው…

በአሜሪካ በተከሰተ ከባድ አውሎ ነፋስ የ25 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2012(ኤፍ.ቢ.ሲ) በአሜሪካ ቴኔስ ግዛት ናሽቪሌ ከተማ በተከሰተ ከባድ አውሎ ነፋስ አደጋ 25 ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸው ተሰምቷል፡፡ ከዚህ ባለፈም አደጋው ከ150 በላይ በሚሆኑ ዜጎች ላይ ከባድ እና ቀላል ጉዳት ማድረሱን የአካባቢው ባለስልጣናት አስታውቀዋል።…