Fana: At a Speed of Life!
Browsing Tag

የተመረጡ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመጋቢት ፍሬዎችና የነገ ተስፋዎችን የሚያወሳ ሕዝባዊ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል "ትናንት፣ ዛሬና ነገን ለኢትዮጵያ ልዕልና" በሚል መሪ ሐሳብ በተለያዩ ከተሞች የመጋቢት ፍሬዎችና የነገ ተስፋዎችን የሚያወሳ ሕዝባዊ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተካሄደ፡፡ ከክልል እስከ ከተማ በየደረጃው የሚገኙ…

መጋቢት 24ን ምክንያት በማድረግ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ ክልል መጋቢት 24ን ምክንያት በማድረግ የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎችን ያሳተፈ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው፡፡ መጋቢት 24 ሀገራዊ ለውጡ ዕውን የሆነበት እና የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መሠረት የተጣለበት ዕለትን ምክንያት …

ፊቼ ጫምባላላ የአንድነታችን ወርቃማና ብርቱ ሀብል ነው – ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሲዳማ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል ፊቼ ጫምባላላ የአንድነታችን ወርቃማና ብርቱ ሀብል ነው ሲሉ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ገለጹ። የፊቼ ጫምባላላ በዓል ትናንት እና ዛሬ በሀዋሳ ተከብሯል። በዓሉን አስመልክቶ ፕሬዚዳንት ታዬ በማህበራዊ…

ኢ.ቢ.ኤስ ቴሌቪዥን በብርቱካን ተመስገን ዙሪያ ላስተላለፈው ዶክመንተሪ ይቅርታ ጠየቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢ.ቢ.ኤስ ቴሌቪዥን በብርቱካን ተመስገን ዙሪያ ላስተላለፈው ዶክመንተሪ ይቅርታ ጠይቋል፡፡ የኢቢኤስ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አማን ፍስሐፅዮን ጉዳዩን አስመልክተው መገለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸውም በድርጅቱ ውስጥ እና በውጭ የተቀናጀ ሃይል…

የሴቶችን ጥቃት ለፖለቲካ አጀንዳ ማስፈጸሚያ መጠቀም ከሰብዓዊነት ያፈነገጠ ተግባር ነው – ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሴቶችን ጥቃት ለፖለቲካ አጀንዳ ማስፈጸሚያ መጠቀም ከሰብዓዊነት ያፈነገጠ ተግባር መሆኑን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) ሰሞኑን ብርቱካን ተመስገን ተብላ በምትጠራ…

ሚኒስቴሩ ከብርቱካን ተመስገን ከበደ ጋር በተያያዘ ማብራሪያ ሰጥቷል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሰሞኑን በማኅበራዊ ሚዲያ መነጋገሪያ በሆነችው ብርቱካን ተመስገን ከበደ የትምህርት ሁኔታ ጋር በተያያዘ ትምህርት ሚኒስቴር ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡ የማብራሪያው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፡- ሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያ መነጋገሪያ ስለሆነችው…

የፊቼ ጫምባላላ በዓል በስኬት ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሲዳማ ብሔር የዘመን መለወጫ የፊቼ ጫምባላላ በዓል በስኬት መጠናቀቁን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሽመልስ ቶማስ ገለጹ፡፡ በዓሉ በተለይም በሐዋሳ ሶሬሳ ጉዱማሌ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ በሚገኝበት የሚከበር በመሆኑ አስቀድሞ ዝግጅት…

ርዕሳነ መስተዳድሮቹ ለፍቼ ጫምባላላ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኦሮሚያ፣ የሶማሌ፣ የደቡብ ኢትዮጵያና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች ርዕሳነ መስተዳድሮች ለሲዳማ ብሄር የዘመን መለወጫ ፍቼ ጫምባላላ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ…

ፍቼ ጫምባላላ የአብሮነት እና የህብረ ብሔራዊነት ነፀብራቅ የሆነ ድንቅ በዓል ነው – አቶ አደም ፋራህ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ ለፍቼ ጫምባላላ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ አቶ አደም ፋራህ በማህበራዊ ትስስር…

ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ከቻይና ብሔራዊ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ጋር በትብብር ለመስራት ተስማማ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ከቻይና ብሔራዊ ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ጋር በትብብር ለመስራት ስምምነት አድርጓል። የፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አድማሱ ዳምጠው በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲ የባህል ዘርፍ አማካሪ ዣንግ ያዌይን እና በቻይና…