Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ ሰራተኞች ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 12፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ ሰራተኞች ለጀግናው መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ የሚውል ከ1 ሚሊየን 651 ሺህ በላይ ብር አሰባሰቡ፡፡ በኤጀንሲው ዋና መስሪያ ቤት እና በቅርንጫፍ መስሪያ ቤት ያሉ ሠራተኞች ሀገራዊ ጥሪን ተቀብለው ከደመወዛቸው ለመከላከያ…

ጠ/ሚ ዐቢይ ለሥራ ጉብኝት አንካራ ገቡ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ልዑካን ቡድናቸው ለሥራ ጉብኝት ቱርክ አንካራ ገብተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቆይታቸው ከቱርኩ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ታይፕ ኤርዶኻን ጋር ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል። በውይይታቸውም በሁለትዮሽ እና…

በአምቦ ከተማ ምክንያታዊ ያልሆነ ዋጋ በጨመሩ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ ተወሰደ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 12፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአምቦ ከተማ በሸቀጦች ላይ ያለአግባብ የዋጋ ጭማሪ ባደረጉ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን የአምቦ ከተማ ንግድ ጽህፈት ቤት ገለጸ፡፡ ሸማቾች በበኩላቸው በየቀኑ እየጨመረ የመጣውን የሸቀጦች ዋጋ ጭማሪ ለመከላከል እየተወሰደ ያለው እርምጃ ተጠናክሮ…

ከዚህ ሳምንት ጀምሮ በሳኡዲ አረቢያ እስር ቤቶች የሚገኙ ዜጎች ወደሃገራቸው ይመለሳሉ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግስት ከሳኡዲ አረቢያ መንግስት ጋር በመቀናጀት ከዚህ ሳምንት ጀምሮ በሳኡዲ አረቢያ በእስር ቤቶችና ማቆያ ማዕከላት የሚገኙ ዜጎች ወደሃገራቸው እንደሚመለሱ ተገለጸ፡፡ ሃገራቱ በሳምንት ሶሶት በረራዎችን በማድረግ በሳኡዲ አረቢያ የተለያዩ ማቆያ…

በጅቡቲ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ለጀግናው መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 12፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)በጅቡቲ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ከ1ነጥብ1 ሚሊየን ብር በላይ ሁለተኛ ዙር የመከላከያ ሠራዊት ድጋፍ አድርገዋል፡፡ በጅቡቲ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን አሸባሪው የህውሓት የጥፋት ቡድን በመንግስት የተሰጠውን የሰላም እድል ወደ ጎን…

በአውስትራሊያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአውስትራሊያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የህልውና ዘመቻን መደገፍ በሚቻልበት ሁኔታ ዙሪያ ውይይት በማካሄድ ድጋፍ አድርገዋል። በአውስትራሊያ የኢፌዴሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር ክቡር ዶክተር ሙክታር ከድር…

በሃይቲ በመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ 2 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሃይቲው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ የ 1 ሺህ 941 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተሰማ፡፡ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋው በሬክተር ስኬል 7 ነጥብ 2 መለካቱም ነው የተነገረው። በአደጋው ህይወታቸው ካለፈው በተጨማሪ 10 ሺህ የሚጠጉ የሀገሪቷ ዜጎች…

አሸባሪዎቹ ኦነግ ሸኔና ህወሓት የኢትዮጵያ ህዝብ ጠላቶች ናቸው – የጅማ ከተማና አካባቢዋ ነዋሪዎች

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪዎቹ ኦነግ ሸኔና ህወሓት በህዝብ ስም የሚቆምሩ የኢትዮጵያ ህዝብ ጠላቶች መሆናቸውን የጅማ ከተማና አካባቢዋ ነዋሪዎች ገለጹ። የጅማ ከተማና አከባቢዋ ነዋሪዎች ዛሬ በጅማ ስቴዲየም በመገኘት የሁለቱን የጥፋት ቡድኖች ሃገር የማፍረስ ተልዕኮ…