Fana: At a Speed of Life!

በትግራይ ክልል ሲካሄድ የቆየው የብቃት ምዝና አትሌቲክስ ውድድር ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በትግራይ ክልል ለአንድ ሳምንት ያህል ሲካሄድ የቆየው የብቃት ምዘና የአትሌቲክስ ውድድር ተጠናቀቀ። የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር አትሌትክስ ፌዴሬሽን ጽህፈት ቤት ፀሐፊ አቶ ጌታቸው ማሞ ÷በክልሉ በነበረው ችግር ለሰባት ወራት ያህል ተቋርጦ የቆየውን…

ምርጫው በሰላም እንዲጠናቀቅ ላደረጉ አካላት የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ምስጋና አቀረበ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 6ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ በሰላም እንዲጠናቀቅ ድጋፍ ላደረጉ አካላት የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ምስጋና አቅርቧል፡፡ የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽነር አራርሳ መርዳሳ በሰጡት መግለጫ፥ ምርጫውን ለማደናቀፍ ከውስጥም ከውጭም የተደረጉ ሙከራዎች ቢኖሩም ህዝቡ ለነሱ…

አምባሳደር መለስ ዓለም በኬንያ ከኮሎምቢያ አምባሳደር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር መለስ ዓለም ዛሬ ተቀማጭነታቸውን ኬንያ አድርገው በኢትዮጵያ ከተወከሉት ከኮሎምቢያ አምባሳደር ሞኒካ ግሬፍ ጋር ተወያይተዋል። በውይይቱም በሁለትዮሽ እና በባለብዙ ወገን መድረኮች የሁለቱን አገሮች ትብብር ለማጠናከር…

የመለስ ዜናዊ የአመራር አካዳሚ የአፍሪካ የአመራር ልህቀት ማዕከል በሚል እንዲሰየም ተወሰነ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የሚኒስትሮች ምክር ቤት "የመለስ ዜናዊ የአመራር አካዳሚ" "የአፍሪካ የአመራር ልህቀት ማዕከል" በሚል እንዲሰየም ዛሬ አጽድቋል፡፡ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 98ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ…

በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ የድምፅ ቆጠራ ተጠናቆ ለምርጫ ክልሎች እየተረከበ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ የሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች የድምፅ ቆጠራውን በማጠናቀቅ ለምርጫ ክልሎች እያስረከቡ ነው። በክፍለ ከተማው ምርጫ ክልል 24 ከሚገኙት 160 ጣቢያዎች ወደ 60 የሚጠጉት እስካሁን ቆጠራውን አጠናቀው ማስረከባቸውን…

ኢትዮጵያና እስራኤል በእግር ኳስ ዘርፍ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ሊያደርጉ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያና የእስራኤል እግር ኳስ ማኅበራት ሊቀመንበሮች በዘርፉ የሁለትዮሽ ትብብርን ለማሳደግ የመግባቢያ ስምምነት እንደሚፈራረሙ በኢትዮጵያ የእስራኤል ኤምባሲ አስታውቋል፡፡ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ የእግር ኳስ…

በምርጫ ሂደቱ የኢትዮጵያ ህዝብ ሀገር ለማቅናት የነበረውን ተስፋና እልህ በግልፅ ያየንበት ነው – ወ/ሮ ሙፈሪሃት ከሚል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በምርጫ ሂደቱ የኢትዮጵያ ህዝብ ሀገር ለማቅናት የነበረውን ተስፋና እልህ በግልፅ ያየንበት ነው ሲሉ የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ከሚል ገለጹ፡፡ የሰላም ሚኒስቴር 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ከዋዜማው ጀምሮ የነበረውን ሂደት ገምግሟል፡፡ ሚኒስቴር…

ግብረሃይሉ 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ እና ተዓማኒ ሆኖ በስኬት እንዲጠናቀቅ አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋና አቀረበ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የፌደራልና የክልል የደህንነትና ፀጥታ ተቋማት 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ፣ተዓማኒና ፍትሃዊ ሆኖ በስኬትእንዲጠናቀቅ አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት በሙሉ የላቀ ምስጋና አቅርበዋል። የፌደራልና የክልል የደህንነትና ፀጥታ ተቋማቱ ለመገናኛ ብዙሃን ዛሬ…

በቤልጂየም፣ ሉግዘምበርግ እና ሆላንድ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ሰልፍ አካሄዱ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤልጂየም፣ ሉግዘምበርግ እና ሆላንድ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የውጭ ኃይሎች በኢትዮጵያ ላይ እያሳደሩ ያለውን አግባብ ያልሆነ ጫና በመቃወም በአውሮፓ ኅብረት ኮሚሽን ፊት ለፊት ሰልፍ አካሂደዋል። ሰልፈኞቹ በኢትዮጵያ ላይ…

በድሬዳዋ የተካሄደው ምርጫ በሰላም ተጠናቋል – የድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የተካሄደው 6ኛው ሃገራዊ ምርጫ በሠላም መጠናቀቁን የአስተዳደሩ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽነር አለሙ መገራ ምርጫውን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ፥ ምርጫው በሠላም እንዲጠናቀቅ ከምርጫው አስቀድሞ…