Fana: At a Speed of Life!

ቤንያሚን ኔታንያሁ በቀረበባቸው የሙስና ክስ ላይ የመጀመሪያ ምስክር መሰማት ጀመረ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 27 ፣ 2013 (ኤፍ .ቢ.ሲ) የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በቀረበባቸው የሙስና ክስ ላይ የመጀመሪያ ምስክር መሰማት ጀምሯል። ኔታንያሁም በምስክር ማሰማት ሂደቱ ላይ ችሎት መገኘታቸው ተነግሯል፡፡ የ71 ዓመቱ ጠቅላይ…

በሚያዚያ ወር የነዳጅ ምርቶች የችርችሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሚያዚያ ወር ከአውሮፕላን ነዳጅ በስተቀር የሌሎች የነዳጅ ምርቶች የችርችሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት እንደሚቀጥል የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ። የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከመጋቢት 26 እስከ ሚያዚያ 30 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ተግባራዊ የሚሆን…

የፕላን እና ልማት ኮሚሽን ከወርልድ ሪሶርስ ኢንስቲቲዩት ጋር አብሮ ለመሥራት የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራረመ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 27 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የፕላን እና ልማት ኮሚሽንና ወርልድ ሪሶርስ ኢንስቲቲዩት በኢኮኖሚያዊ እድገት እንዲሁም ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተገናኘ በተቋም ለውጥ እና አቅም ግንባታ ላይ አብሮ ለመሥራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡…

የሴቶችን ችግር በንግግር እና በመፈክር ብቻ ሳይሆን በተግባር መፍታት ይገባል -ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 27 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ̎ትችያለሽ - በፈተና የተሞረደ ማንነት ለለውጥ የተመቸ ስብዕና ይገነባል!̎ በሚል መሪ ቃል በግንባታው ዘርፍ የተሰማሩ ሴቶችን ሚና፣ አቅምና አርአያነት የሚዘክር ሃገር አቀፍ የምክክር መድረክ በአዲስ አበባ ተካሄደ።…

ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሀብቷን አልምታ የመጠቀም ሙሉ መብት አላት -ፕሮፌሰር ተስፋዬ ታፈሰ 

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 27 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በሉዓላዊ ግዛቷ ውስጥ የሚገኘውን የተፈጥሮ ሀብቷን አልምታ የመጠቀም ሙሉ መብት እንዳላት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦ ፖለቲክስና የአፍሪካ ጥናት ማዕከል መምህርና ተመራማሪ ከሆኑት ፕሮፌሰር ተስፋዬ ታፈሰ አስታወቁ፡፡ በዓባይ ወንዝ…

ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ኮቪድ19ኝን ለመከላከል ከወጣው መመሪያ ጋር በተያያዘ መሰረታዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ሰጠ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ኮቪድ19ኝን ለመከላከል ባለፉት ሳምንታት ከወጣው መመሪያ ጋር በተያያዘ መሰረታዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡ ሙሉ ማብራሪያው እንደሚከተለው ቀርቧል፡- ስለ ስብሰባ፤ ስለ ስብሰባ የሚደነግገው አንቀጽ ውይይት…

ባለፉት ስምንት ወራት ከ2 ቢሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች ተይዘዋል

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 27 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ስምንት ወራት ከ 2 ቢሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዙን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮንትሮባንድ መቆጣጠርና ኦፕሬሽን ዳይሬክቶሬት አስታወቀ። ኮሚሽነር አይንሻ ቶላ…

በህንድ በአንድ ቀን ብቻ ከ100 ሺህ በላይ ሰዎች ኮቪድ19 ተገኘባቸው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ህንድ ወረርሽኙ ከተከሰተ ጀምሮ በአንድ ቀን ብቻ ከ100 ሺህ በላይ ዜጎቿ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን አስታወቀች፡፡ ህንድ ከ100 ሺህ በላይ ዜጎቿ በአንድ ቀን ሲያዙ ከአሜሪካ በመቀጠል ሁለተኛዋ ሃገር ሆናለች፡፡ በአንድ ቀን የተያዙት ዜጎቿ…

የኢጋድ ዩኒቨርሲቲዎች ጉባኤ በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው

አበባ ፣ መጋቢት 27 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) ዩኒቨርሲቲዎች ጉባኤ ዛሬ በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው፡፡ ጉባኤው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ቀጣይነት ላለው የሃገር እድገት የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ የሚዳሰስበት ነው…

ጠ/ሚ ዐቢይ ለኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ሃላፊዎችን ሾሙ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 27 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለሶስት የስራ ሃላፊዎች ሹመት ሰጡ፡፡ በዚህም መሐመድ ኢድሪስ መሐመድ - የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዮናታን ተስፋዬ ረጋሳ - የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር…