Fana: At a Speed of Life!

ተጨማሪ 220 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ11 ሰዎች ህይወት አልፏል

አዲስ አበባ ፣ ጥር 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 24 ሰአታት ለ3 ሺህ 952 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 220 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤኔ ሚኒስቴር አስታወቀ። ይህን ተከትሎም በአጠቃላይ 127 ሺህ 792 ሰዎች ቫይረሱ እንደተገኘባቸውም ነው ሚኒስቴሩ ያስታወቀው።…

አቶ ደመቀ መኮንን ከፐብሊክ ዲፕሎማሲ ክላስተር አስተባባሪዎች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2013 (ኤፍቢሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድን የክላስተር አስተባባሪዎች ጋር ተገናኝተው ተወያዩ። አቶ ደመቀ በውይይታቸው በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለተሰብሳቢዎቹ ዝርዝር ገለፃ አድርገዋል። የውይይቱ ዋና…

ስብሃት ነጋን ጨምሮ በቁጥጥር ስር የዋሉ ዘጠኝ የጁንታው አመራሮች አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2013 (ኤፍቢሲ) የጥፋት ስትራቴጂስቱና ዋነኛው የጁንታ መሪ ስብሃት ነጋን ጨምሮ በቁጥጥር ስር የዋሉ ዘጠኝ የጁንታው አመራሮች አዲስ አበባ ገብተዋል። የሀገር መከላከያ ሰራዊት የጥፋት ስትራቴጂስቱና ዋነኛው የጁንታ መሪ ስብሃት ነጋን ጨምሮ ሌሎች የጥፋት ቡድኑ አመራሮች…

ወላይታ ዲቻ ዋና አስልጣኙን ደለለኝ ደቻሳን አሰናበተ

አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2013 (ኤፍቢሲ) ወላይታ ዲቻ ስፖርት ክለብ ዋና አስልጣኝ ደለለኝ ደቻሳ እና ምክትል አሰልጣኙን ማሰናበቱን አስታወቀ፡፡   የወላይታ ዲቻ የስፖርት ክለብ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሳሙኤል ፎላ በክለቡ ወቅታዊ አቋም ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል።   አቶ…

በስልጤ ዞን ለሚገነባው የካሊድ ዲጆ የግድብና መስኖ ፕሮጀክት በነገው ዕለት የመሰረት ድንጋይ ይቀመጣል

አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2013 (ኤፍቢሲ) ከ1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ ወጭ በስልጤ ዞን ለሚገነባው የካሊድ ዲጆ የግድብና መስኖ ፕሮጀክት በነገው ዕለት የመሰረት ድንጋይ ይቀመጣል። ግድቡ 1 ሺህ 731 ሜትር ርዝመትና ከ30 በላይ ሜትር ከፍታ ሲኖረው ፕሮጀክቱ ከ1 ሺህ 800 ሄክታር በላይ…

በአዲስ አበባ ከተማ ለ500 ሺህ ተማሪዎች የልደት ሰርተፍኬት ሊሰጥ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2013 (ኤፍቢሲ) የአዲስ አበባ ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ መረጃ ኤጀንሲ በመዲናዋ ለ500 ሺህ ተማሪዎች የልደት ሰርተፍኬት ለመስጠት መዘጋጀቱን አስታወቀ። በኢትዮጵያ ከ1952 ዓ.ም ጀምሮ የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ የፍትሃብሄር አካል አድርጎ ያስቀመጠው ቢሆንም፤ ህጉ ከ50…

የታላቁ የሩጫ ውድድር የሚካሄድባቸው መንገዶች ለትራፊክ ዝግ ስለሚሆኑ አሽከርካሪዎች አመራጭ መንገድ እንዲጠቀሙ ተጠይቋል

አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2013 (ኤፍቢሲ)በነገው ዕለት የታላቁ የሩጫ ውድድር የሚካሄድባቸው መንገዶች ለትራፊክ ዝግ ስለሚሆኑ አሽከርካሪዎች አመራጭ መንገድ እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ፖሊስ ከሚሽን ጠይቋል፡፡ ፖሊስ የሚያደርገውን  የፀጥታ ዝግጅት በቀና መንፈስ በመተባበር የሚታወቀው መላው የመዲናዋ…

በኢንዶኔዥያ 50 ተጓዦችን ይዞ ሲበር የነበረ ቦይንግ 737 የደረሰበት አልታወቀም

አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2013 (ኤፍቢሲ) በኢንዶኔዥያ 50 ተጓዦችን አሳፍሮ ሲበር የነበረው ንብረትነቱ የስሪዊጃያ አየር መንገድ የሆነ ቦይንግ 737 አውሮፕላን የደረሰበት አልታወቀም፡፡ አውሮፕላኑ ከኢንዶኔዥያ ዋና ከተማ ጃካርታ ከተነሳ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ነው መሰወሩ የተነገረው፡፡…

በታሪክ ላይ ተገቢውን እሳቤ መያዝ ለዘላቂ ሰላም ግንባታ ጉልህ ፋይዳ አለው -የሰላም ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል

አዲስ አበባ ፣ ጥር 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ በታሪክ ላይ ትክክለኛውን ነገር መያዝ ለዘላቂ ሰላም ግንባታ ፋይዳው የጎላ መሆኑን የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል ገለጹ። በሰላም ሚኒስቴር አዘጋጅነት “የሰላም ወግ፤ ብሔራዊ መግባባት ለዘላቂ ሰላም ግንባታ” በሚል መሪ ሃሳብ…

አንደኛው ዙር የምክንያታዊ ወጣቶች ውይይት መድረክ በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ጥር 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በብልጽግና ወጣቶች ሊግ አዘጋጅነት በሀገር ደረጃ በከተሞች እየተካሄደ ያለው አንደኛው ዙር የምክንያታዊ ወጣቶች ውይይት መድረክ ዛሬ በአፋር ሰመራ ከተማ እየተካሄደ ነው። በመድረኩ ከክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የተውጣጡ ምሁራን ወጣቶች እየተሳተፋበት…