Fana: At a Speed of Life!

የኔዘርላንድስ ፖሊስ በሩዋንዳ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተጠርጣሪን በቁጥጥር ስር አዋለ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የኔዘርላንድስ ፖሊስ በሩዋንዳ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተጠርጣሪ የሆነን ግለሰብ በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ፡፡ የ71 አመቱ ግለሰብ በፈረንጆቹ 1994 በሩዋንዳ በተፈጸመው የዘር ማጥፋት ወንጀል ተሳትፈዋል በሚል ተጠርጣሪ ናቸው፡፡ የቀድሞው…

በመዲናዋ የትራፊክ ህግ የተላለፉ 15 ሺህ 837 አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ ተወሰደ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17 ቀን 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓትን ለማሻሻል የወጡ የትራፊክ ህጎችን የተላለፉ 15 ሺህ 8 37 አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ ተወስዷል፡፡ ቅጣቱ ህግ በጣሱ፣ ከአቅም በላይ ትርፍ በጫኑ፣ ከታሪፍ በላይ ባስከፈሉ፣…

የተለያዩ ተቋማት ለገበታ ለሃገር ድጋፍ እያደረጉ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17 ቀን 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለገበታ ለሃገር ያቀረቡትን ጥሪ ተከትሎ የተለያዩ ተቋማት ድጋፍ እያደረጉ ነው፡፡ በዚህም አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ 10 ሚሊየን ብር፣ ሕብረት ባንክ 10 ሚሊየን ብር ፣የኢትዮጵያ ልማት ባንክ 10…

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ሰብላቸው በአንበጣ መንጋ የወደመባቸው የምዕራብ ሐረርጌ ዞን አርሶ አደሮችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከግብርና፣ አርብቶ አደርና አካባቢ ጥበቃ እንዲሁም ከውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴዎች የተዋቀረ ቡድን በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሐረርጌ ዞን በአንበጣ መንጋ ሳቢያ ጉዳት የደረሰባቸው አከባቢዎችን ጎብኝተዋል፡፡…

አዲስ እየተዘጋጀ ባለው የማዕድንና ነዳጅ ረቂቅ ፖሊሲ ላይ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ እየተዘጋጀ ባለው የማዕድንና ነዳጅ ረቂቅ ፖሊሲ ላይ ውይይት ተካሂዷል።   በውይይቱ ላይ የማዕድን ነዳጅ ሚኒስትር ኢንጅነር ታከለ ኡማና የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴን ጨምሮ የማይክሮ ኢኮኖሚ አማካሪ ቡድን…

ለጠ/ሚ ዐቢይ በተጠራ ሰልፍ ላይ ቦንብ በመወርወር የሰው ህይወት በማጥፋትና የአካል ጉዳት በማድረስ ጥፋተኛ የተባሉ ግለሰቦች ላይ ከ5 እስከ እድሜ ፅኑ እስራት…

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በተጠራው የድጋፍ ሰልፍ ላይ በመስቀል አደባይይ በቦንብ በመወርወር የሁለት ሰዎች ህይወት እንዲያልፍ እና በ150 ሰዎች የአካል ጉዳት መድረስ ወንጀል ጥፋተኛ የተባሉ 5 ግለሰቦች ከ5 ዓመት…

163 ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ ፣ጥቅምት 17 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) 163 ኢትዮጵያውያን ዛሬ ከቤሩት ወደ አገራቸው ተመለሱ፡፡ ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ ሰነድ አልባ ዜጎችን ወደ አገራቸው የመመለሱ ስራ እየተከናወነ መሆኑ ተገልጿል፡፡ በዚህም በአንድ ሳምንት ውስጥ 947 ዜጎች ወደ አገራቸው እንዲገቡ…

በትራምፕ የታጩት ኤሚ ኮኒ ባሬት የአሜሪካ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ መሆናቸው ተረጋገጠ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 17 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የታጩት ኤሚ ኮኒ ባሬት የአሜሪካ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ እንዲሆኑ በሴኔቱ ፀደቀላቸው። የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ሊካሄድ ሳምንት በቀረበት ወቅት ኤሚ ኮኒ ባሬት ከዘጠኞቹ አንዷ የከፍተኛው ፍርድ ቤት…

የ2012 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የተፈታኞች ምዝገባ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የ2012 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የተፈታኞች ምዝገባ በኦንላይን ተጀምሯል። የኦንላይን ምዝገባውም በየአካባቢያቸው ባሉ ትምህርት ቤቶች መጀመሩን የትምህርት ሚኒስቴር ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር ወይዘሮ ሀረጓ ማሞ ተናግረዋል።…

የአዋሽ 3 የኃይል ማመንጫ ጣቢያ በከፊል አገልግሎት መስጠት ጀመረ

አዲስ አበባ ፣ጥቅምት 17 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዋሽ ወንዝ ሙላት ሳቢያ በጎርፍ ተጥለቅልቆ አገልግሎት አቋርጦ የነበረው የአዋሽ 3 የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ በከፊል አገልግሎት መስጠት መጀመሩን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ፡፡ 32 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ያለው የአዋሽ 3…