Fana: At a Speed of Life!

ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ ከፍተኛ ባለስልጣናት በቅርቡ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 በእሳት አደጋ ጉዳት የደረሰበትን አካባቢ ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አደም ፋራህ፣ የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሺዴ፣ የሴቶችና ህፃናት ሚኒስትሯ ፊልሰን አብዱላ እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች በቅርቡ በቦሌ ክፍለ…

ተጨማሪ 841 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው 588 ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት ለ5 ሺህ 997 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 841 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ፡፡ ሚኒስትሯ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ 230 ሰዎች በፅኑ ህክምና ላይ እንደሚገኙ…

በአዲስ አበባ የሚገኙ የህወሃት አመራሮች በህወሃት የተደረገላቸውን ጥሪ እንደማይቀበሉ ገለጹ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 2 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ የሚገኙ የቀድሞ የህወሃት አመራሮች ህወሃት በፌደራል መንግሥቱ የሚተላለፉ ህጎችን በመተላለፍ የህዝብ ሃላፊነት ይዘው በፌደራል መንግስት የስራ ሃላፊነት ላይ የሚገኙ አመራሮችን ለቃችሁ ኑ በሚል ያቀረበው ጥሪ አግባብ አለመሆኑን ገለጹ፡፡…

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በመተከል ዞን የተፈጸመውን ድርጊት አወገዙ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 2 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በመተከል ዞን በተደጋጋሚ በሚከሰተው የፀጥታ ችግር የዜጎች ህይወት መጥፋት አሳዛኝ እና ልብ ሰባሪ ድርጊት መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ገለጹ፡፡ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዛሬው ዕለት የተፈፀመውን አሳዛኝ ድርጊት መነሻ…

በአውሮፓ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እየተባባሰ በመምጣቱ እገዳዎች እየተጣሉ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአውሮፓ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እየተባባሰ መምጣቱን ተከትሎ ሃገራት የተለያዩ እገዳዎችን መጣል ጀምረዋል፡፡ ባለፈው ሳምንትም በአንድ ቀን ብቻ 100 ሺህ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተነግሯል፡፡ ይህ ቁጥር ወረርሽኙ ከተከሰተ በኋላ…

በኦሮሚያ ክልል ለ2013 የትምህርት ዘመን ዝግጅት እየተጠናቀቀ መሆኑ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኦሮሚያ ክልል የ2013 የትምህርት ዘመን ለማስጀመር ዝግጅት እየተጠናቀቀ መሆኑን በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ አቶ አዲሱ አረጋ ገለፁ። አቶ አዲሱ አረጋ በዛሬው እለት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፥ የ2013…

ሚኒስቴሩ የውጭ ምንዛሬ ግኝትን ማሳደግ የሚያስችሉ ተግባራት በ10 ዓመቱ ዕቅድ ማካተቱን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ምንዛሬ ግኝትን ለማሳደግ የሚያስችሉ ተግባራት በ10 ዓመቱ ዕቅድ መካተታቸውን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ሚኒስቴሩ የዘርፉን የ10 ዓመት መሪ ዕቅድ እና የ2013 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት እቅድ አፈጻጸም አስመልክቶ ከሚኒስቴር…

የአዲስ አበባ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ አመራሮች ያካሄዱትን ድርጅታዊ ኮንፈረንስ አጠናቀቁ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ ) የአዲስ አበባ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ አመራሮች ለሁለት ቀናት አዲስ አበባን በብልጽግና ጎዳና ማራመድ የሚችል አመራር እንገነባለን በሚል መሪ ቃል ሲያካሂዱት የነበረው ድርጅታዊ ኮንፈረንስ ተጠናቀቀ። የአዲስ አበባ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች…

ፌስ ቡክ መገበያያ መተግበሪያ ለኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የፌስ ቡክ ኩባንያ በፌስ ቡክ ገጹ አማካኝነት የሚሰራ ምርቶችን መሸጥ እና መግዛት የሚያስችል የፌስ ቡክ መገበያያ መተግበሪያ ለኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ መጀመሩን አስታውቋል፡፡ የፌስ ቡክ የግብይት መድረኩ ኢትዮጵያውያን የሚፈልጓቸውን ምርቶች በቀላሉ…

አዲስ አበባ ለሚገኙ አምባሳደሮችና የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ተሰጠ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 2 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አዲስ አበባ ለሚገኙ አምባሳደሮችና የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ሰጠ፡፡ የተራዘመው 6ኛ ሃገራዊ ምርጫ፣ ኮቪድ19 እና ኢ ህገ መንግስታዊ የሆነው የትግራይ ክልል ምርጫን የተመለከቱ…