Fana: At a Speed of Life!

በጋሞ ዞን ትናትና ምሽት ከፍተኛ ዝናብ ባስከተለው ናዳ 5 የቤተሰብ አባላት ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በጋሞ ዞን ሳምንቱን እየጣለው ባለው ዝናብ የ8 ሰዎች ህይወት ማለፉን የደቡብ ክልለ አታወቀ። በጋሞ ዞን ቅዳሜ ምሽት በገረሴ ወረዳ የጣለው ከፍተኛ ዝናብ ባስከተለው ናዳ 5 የቤተሰብ አባላት ህይወት ማለፉ ተጠቁሟል። በተመሳሳይ ቀን…

በወላይታ ሶዶ ከ1 ሺህ አረጋዊያንና የጎዳና ተዳዳሪዎች ጋር የፋሲካ በዓል ተከበረ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በወላይታ ሶዶ ከ1ሺህ አቅመ ደካማ አረጋዊያንና የጎዳና ተዳዳሪዎች ጋር የፋሲካ በዓል ተከበረ። የፋሲካ በዓል ከአረጋዊያንና ከጎዳና ተዳዳሪዎች ጋር በዚህ መልኩ መከበሩ ወገናዊ መተሳሰብ እየጎለበተ ስለመምጣቱ ማሳያ መሆኑ ተገልጿል፡፡…

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 3 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 108 መድረሱን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።   ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው የ667 ላቦራቶሪ ምርመራ ሶስት ተጨማሪ ሰዎች የኮሮናቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።…

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የታንዛኒያን የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶች ለአውሮፓ ገበያ ሊያቀርብ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ የታንዛኒያን የአትክልት እና ፍራፍሬ ምርቶች በሳምንት ሶስት ቀናት በረራ በማድረግ ለአውሮፓ ገበያ ሊያቀርብ ነው። አየር መንገዱ የታንዛኒያን የአትክልት እና ፍራፍሬ ምርቶች ለአውሮፓ ገበያ እንዲያቀርብ የተደረገው የሀገሪቱ…

ጠ/ሚ ዐቢይ ከጦር አካል ጉዳተኞች ጋር የትንሳኤ በአልን አከበሩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድና የካቢኔ አባላት የትንሳኤ በአልን ከጦር አካል ጉዳተኞች ጋር አክብረዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና የካቤኒ አባሉ ልደታ በሚገኘው የአካል ጉዳተኞች ተሀድሶ ማዕከል በመገኘት ነው በዓሉን ያከበሩት። ጠቅላይ…

የችግር ቀን ደራሽ የራስ አገርና ወገን መሆኑን መገንዘብ ተገቢ ነው- ወይዘሮ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2012( ኤፍ.ቢ.ሲ) የችግር ቀን ደራሽ የራስ አገርና ወገን መሆኑን መገንዘብ ተገቢ መሆኑን የኢፌዴሪ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ገለፁ። ጠቅላይ አቃቤ ህጓ ይህን መልዕክት ያስተላለፉት የለይቶ ማቆያ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት ሚኒስትሮች ጋር በአዲስ አበባ…

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ ለኮቪድ-19 ህመምተኞች ህክምና መስጫ በሚሌኒየም አዳራሽ የተዘጋጀውን ማዕከል ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2012( ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ  ለኮቪድ-19 ህመምተኞች እንዲሆን በሚሌኒየም አዳራሽ የተዘጋጀውን የህክምና ማዕከል ጎበኙ። ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ህክምና የሚያገኙበት ማዕከል ይሆናል ነው የተባለው። ጠቅላይ…

የፋሲካ በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በመከበር ላይ ይገኛል

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2012( ኤፍ.ቢ.ሲ) የፋሲካ በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በመከበር ላይ ይገኛል። በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የሁሉም የክርስትና አምነት ተከታዮች ከወትሮው በተለየ መልኩ ምሽቱን በየመኖሪያ ቤታቸው ፋሲካን ተቀብለዋል። ለሊቱን የተለያዩ እምነት ተከታዮችም…

”እንደ ትንሳኤው ብሩህ ቀናችን ላይ እንደምንደርስ እምነቴ ነው”ኢ/ር ታከለ ኡማ

አዲስ አበባ፣ሚያዚያ 10፣2012(ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ለትንሳኤ በዓል ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት”እንደ ትንሳኤው ብሩህ ቀናችን ላይ እንደምንደርስ እምነቴ ነው” ብለዋል፡፡ "ምንም እንግልት፣ ምንም ስቃይ፣ ምንም መከራ ዘላለማዊ አይደለም"…

የለይቶ ማቆያ አስተባባሪ ኮሚቴ 2500 ሰዎችን ማስተናገድ የሚችሉ ቦታዎችን ተረከበ

አዲስ አበባ፣ሚያዚያ 10፣2012(ኤፍ.ቢ.ሲ) የለይቶ ማቆያ አስተባባሪ ኮሚቴ በአዲስ አበባ 2500 ሰዎችን ማስተናገድ የሚችሉ ቦታዎችን  ተረከበ፡፡ ጠቅላይ አቃቤ ህግ  አዳነች አቤቤ ÷ ኮሚቴው 2 ሺህ አምስት መቶ ሰዎችን ማስተናገድ የሚችሉ ቦታዎችን በአዲስ አበባ መረከቡን በፌስ ቡክ ገጻቸው ላይ…