Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ ተጨማሪ አራት ግለሰቦች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው፤ ከህመሙ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 10 ደርሷል

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 3 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት የላቦራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 345 ግለሰቦች መካከል አራቱ የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው መረጋገጡን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። ቫይረሱ ተገኝቶባቸው ክትትል እያደረጉ ከሚገኙት መካከል 10 ግለሰቦች አገግመዋል።…

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 45 ሺህ የፊት መሸፈኛ ማስኮች፣ የእጅ ጓንቶችና የህክምና ጋዎኖችን በድጋፍ አገኘ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 3 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ከሜድ ሼር አለም አቀፍ የበጎ አድራጎት ተቋም የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ለመከላከል የሚያስችሉ ቁሳቁስ ድጋፍን ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አደረገ። ድጋፉን የተረከቡት ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ለተቋሙ እና በተቋሙ ውስጥ ይህ ድጋፍ…

በትግራይ ክልል ሁሉም ወረዳዎችና ከተሞች የኮሮና ቫይረስ የቤት ለቤት ዳሰሳ ከሚቀጥለው ሰኞ ጀምሮ ሊካሄድ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 3 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል ሁሉም ወረዳዎችና ከተሞች የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ያለመ የቤት ለቤት ዳሰሳ ከሚቀጥለው ሰኞ ሚያዚያ 5 ቀን 2012 ጀምሮ ለተከታታይ አራት ቀናት እንደሚካሄድ የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ። የቢሮው ሀላፊ…

በአዲስ አበባ የቤት ለቤት የኮሮና ቫይረስ ልየታ ሊጀመር ነው

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 3 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ከቀጣዩ ሳምንት ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ የቤት ለቤት የኮሮና ቫይረስ ልየታ እንደሚጀመር አስታወቁ። ምክትል ከንቲባው ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ በአስተዳደሩ እየተከናወኑ…

ከ1 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የምግብና አልባሳት ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 3 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የገቢዎች ሚኒስቴርና የጉምሩክ ኮሚሽን 1 ቢሊየን 47 ሚሊየን 909 ሺህ 135 ብር የሚያወጡ የተለያዩ የምግብና አልባሳት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረጉ። ድጋፉ ለዘጠኙም ክልሎች እና ለሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም ለ26 በጎ አድራጎት ማህበራት…

ዓለም ላይ በኮሮና ቫይረስ ህይዎታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 102 ሺህ አልፏል

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 3፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም ላይ በኮሮና ቫይረስ ህይዎታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 102 ሺህ አልፏል። እንደ ጆን ሆፕኪንስ መረጃ በቫይረሱ ሳቢያ 102 ሺህ 782 ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋል። ከዚህ ውስጥ በጣሊያን እና አሜሪካ በተናጠል ከ18 ሺህ በላይ ሰዎች…

የዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም አመራር ወቅቱንና ኃላፊነታቸውን የሚመጥን ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 3 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም አመራር ወቅቱንና ኃላፊነታቸውን የሚመጥን መሆኑን አስታወቁ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ጋር ተወያይተዋል። በውይይታቸውም ጊዜው…

በፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ የሚመራውና በዩኔስኮ የተቋቋመው አለም አቀፍ የትምህርት ኮሚሽን አስቸኳይ ውይይት አካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 2፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ የሚመራውና በዩኔስኮ የተቋቋመው አለም አቀፍ የትምህርት ኮሚሽን አስቸኳይ ውይይት አካሄደ። ውይይቱ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በትምህርት ዘርፉ ላይ የሚያስከትለውን ተጽዕኖ አስቀድሞ ለመከላከል መወሰድ…