Fana: At a Speed of Life!

ባንኩ በሀገሪቱ የመጀመሪያ የሆነውን የዲጂታል ማዕከል ከፈተ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 16 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሀገሪቱ የመጀመሪያ የሆነውን የዲጂታል ማዕከል በዛሬው ዕለት ይፋ አድርጓል። አዲሱ የዲጂታል ማዕከል ከ 20 በላይ የገንዘብ መክፈያና መቀበያ ማሽኖችን በአንድ ቦታ በማስቀመጥ ደንበኞች በቀላሉ የባንክ አገልግሎት ተጠቃሚ…

በፕሪምየር ሊጉ ሰበታ ከተማ እና ወላይታ ድቻ ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ ፣ ጥር 16 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 10ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በዛሬው ዕለት በተለያዩ ከተሞች ተካሂደዋል። ሰበታ ከተማ እና ሀዋሳ ከተማ በአዲስ አበባ ስታዲየም ባደረጉት ጨዋታ ሰበታ ከተማ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል። የሰበታ ከተማን የማሸነፊያ…

የወረታ ደረቅ ወደብ በሚቀጥለው ሳምንት ይመረቃል

አዲስ አበባ ፣ ጥር 16 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ100 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት የወረታ ደረቅ ወደብ የመጀመሪያ ምዕራፍ በሚቀጥለው ሳምንት ይመረቃል። የኢትዮጵያ ባህርና ትራንስፖርት ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት የወደብና ተርሚናል ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ ስፈጻሚ አቶ እውነቱ ታዬ…

36ኛው የጃን ሜዳ ኢንተርናሽናል ሀገር አቋራጭ ውድድር ነገ ይካሄዳል

አዲስ አበባ ፣ ጥር 16 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) 37ኛው የጃን ሜዳ ኢንተርናሽናል ሀገር አቋራጭ ውድድር ነገ በጃንሜዳ ይካሄዳል። በውድድሩ አምስት ክልሎች፣ ሁለት የከተማ አስተዳደሮች፣ 37 ክለቦች እና የማሰልጠኛ ተቋማት የሚሳተፉ ይሆናል። 6 ኪሎ ሜትር ወጣት ሴቶች ፤ በ10 ኪሎ ሜትር…

በቻይና በተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 41 ደረሰ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 16 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በቻይና በተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች ቁጥር 41 መድረሱ ተሰምቷል። በቅርብ በቻይና ውሃን  ግዛት የተቀሰቀሰው ኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ አድማሱን በማስፋት በተለየዩ የዓለም ሀገራት ውስጥ መከሰቱ ተነግሯል። ቫይረሱ…

በቱርክ በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ 20 ሰዎች ለህልፈት ተዳረጉ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 16 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በቱርክ በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ 20 ሰወች መሞታቸው ተነገረ። በምስራቅ ቱርክ በደረሰው አደጋ ከሞቱት በተጨማሪ ከ900 በላይ ሰዎች መቁሰላቸውም ነው የተነገረው። በሬክተር ስኬል 6 ነጥብ 8 የተመዘገበው የመሬት መንቀጥቀጥ ወደ 30 የሚጠጉ…

የሰላም ሚኒስቴር ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር የምክክር መድረክ እያካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ጥር 16 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ሚኒስቴር ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር በሃገራዊ ሰላምና የህግ የበላይነት መከበር ዙሪያ የምክክር መድረክ እያካሄደ ነው። የምክክር መድረኩ “ነጋዴው ማህበረሰብ ለሃገራዊ የሰላም ግንባታ” በሚል መሪ ሀሳብ ነው እየተካሄደ ያለው። በመድረኩ…

የትግራይ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 16 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት 5ኛ ዘመን 18ኛ ዙር መደበኛ ጉባዔውን ማካሄድ ጀመረ። በመቐለ ከተማ ምክር ቤት አዳራሽ እየተካሄደ ያለው ጉባዔ ለቀጣዮቹ አምስት ቀናት እንደሚቆይ ተገልጿል። ምክር ቤቱ የክልሉ ሥራ አስፈጻሚ…

የሱዳን መንግስት ከተቃዋሚወች ጋር የሰላም ስምምነት ተፈራረመ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 16 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የሱዳን መንግስት ከተቃዋሚዎች ጋር የሰላም ስምምነት ተፈራረመ። ስምምነቱ ከሰሜኑ የሱዳን ህዝቦች ነፃ አውጭ ንቅናቄ (ኤስ ፒ ኤል ኤም፤ ኤን) ጋር የተፈረመ ነው ተብሏል። የአሁኑ ስምምነት በቀጠናው የተያዘው የሰላም እቅድ አካል መሆኑም ነው…

የጣና በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ግንባታ ከስጋት ወጥቶ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በግንባታ መዘግየትና የጥራት ችግር ምክንያት ስጋት ውስጥ የነበረው የጣና በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ግንባታ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ተገለፀ። የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን የቦርድ አባላት፣ የስራ ኃላፊዎች እና ጋዜጠኞች ዛሬ የፕሮጀክቱን አፈፃፀም…