Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

የፓሪስ ኦሊምፒክ የመዝጊያ ሥነ- ሥርዓት ዛሬ ምሽት ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የ33ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች የመዝጊያ ሥነ-ሥርዓት 80 ሺህ ተመልካቾችን በሚያስተናግደው በስታድ ደ ፍራንስ ብሔራዊ ስታዲየም ከምሽቱ 4 ሠዓት ጀምሮ ይከናወናል፡፡ የኦሊምፒክ ባንዲራም 34ኛውን የኦሊምፒክ ጨዋታዎች በፈረንጆቹ 2028 ለምታስተናግደው ሎስ አንጀለስ የውድድር አዘጋጆች የማስተላለፍ መርሐ-ግብር ይከናወናል፡፡ ፓሪስ ያስተናገደችው 33ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች ከሐምሌ 19 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ሲካሄድ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ በኦሊምፒኩ ኢትዮጵያ 1 የወርቅ እና ሦስት የብር…
Read More...

ኢትዮጵያ በሴቶች ማራቶን የብር ሜዳሊያ አገኘች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ በ33ኛው የፓሪስ ኦሊምፒክ ወድድር በሴቶች ማራቶን አትሌት ትዕግስት አሰፋ ለሀገሯ የብር ሜዳሊያ አስገኝታለች፡፡ በ33ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የተጠበቁበት የሴቶች ማራቶን ውድድር ከጠዋቱ 3 ሰዓት ጀምሮ ተካሂዷል፡፡ በዚህም አትሌት ትዕግስት አሰፋ ርቀቱን 2ኛ ሆና በማጠናቀቅ ለሀገሯ የብር ሜዳሊያ…

ኢትዮጵያ በሴቶች 1 ሺህ 500 ሜትር ውድድር የሜዳሊያ ሰንጠረዥ ውስጥ መግባት አልቻለችም

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በፓሪስ እየተካሄደ ባለው 33ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች ኢትዮጵያ በሴቶች 1 ሺህ 500 ሜትር ውድድር የሜዳሊያ ሰንጠረዥ ውስጥ መግባት አልቻለችም። ከምሽቱ 3 ሰዓት ከ15 ላይ በተካሄደው የ1 ሺህ 500 ሜትር ሴቶች የፍጻሜ ውድድር ኢትዮጵያን በመወከል አትሌት ድርቤ ወልተጂ እና ጉዳፍ ፀጋይ ተሳትፈዋል። በዚህም አትሌት ድርቤ…

ኢትዮጵያ በወንዶች 5 ሺህ ሜትር ውድድር ድል አልቀናትም

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በፓሪስ እየተካሄደ ባለው 33ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች ኢትዮጵያ በወንዶች 5 ሺህ ሜትር የሜዳሊያ ሰንጠረዥ ውስጥ ሳትገባ ቀርታለች። በፓሪስ 2024 የኦሊምፒክ ውድድር ዛሬ ምሽት 2 ሰዓት ከ50 ላይ በተካሄደው የወንዶች 5 ሺህ ሜትር ፍጻሜ ውድድር ኢትዮጵያን በመወከል አትሌት ሐጎስ ገብረሕይወት፣ አትሌት ቢኒያም መሐሪና አትሌት…

ኢትዮጵያ በኦሊምፒኩ የመጀመሪያ ወርቋን አገኘች 

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በፓሪስ 2024  የኦሊምፒክ ወድድር በማራቶን ኢትዮጵያ በአትሌት ታምራት ቶላ አማካኝነት የመጀመሪያ ወርቋን አግኝታለች፡፡ በፓሪስ ኦሊምፒክ የወንዶች የማራቶች ውድድር የተካሄደ ሲሆን ÷አትሌት ታምራት ቶላ ፣ቀነኒሳ በቀለና ደሬሳ ገለታ ኢትዮጵያን ወክለው ተወዳድረዋል። በዚህም ታምራት ቶላ ውድድሩን  2 ሰዓት ከ6 ደቂቃ…

እየተካሄደ የሚገኘውን የማራቶን ውድድር ጨምሮ ኢትዮጵያ የምትጠበቅበት ሶስት ውድድሮች ዛሬ ይካሄዳሉ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)እየተካሄደ የሚገኘውን የወንዶች የማራቶን ውድድር ጨምሮ ኢትዮጵያ የምትጠበቅበት ሶስት ውድድሮች ዛሬ ይካሄዳሉ፡፡ በፓሪስ 2024  የኦሊምፒክ ወድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የሚጠበቁት የወንዶች ማራቶን የፍጻሜ ውድድር በመካሄድ ላይ ይገኛል። አትሌት ቀነኒሳ በቀለ፣ አትሌት ታምራት ቶላና አትሌት ደሬሳ ገሌታ ኢትዮጵያን ወክለው…