ስፓርት
ቼልሲ ፔድሮ ኔቶን ከወልቭስ ለማስፈረም ተስማማ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ቼልሲ የወልቭሱን የፊት መስመር አጥቂ ፔድሮ ኔቶን ለማስፈረም ስምምነት ላይ መድረሱ ተገለፀ፡፡
የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ለተጫዋቹ ዝውውር በአጠቃላይ 63 ሚሊዮን ዩሮ አውጥቷል፡፡
ዎልቭስ ተጫዋቹን ለመተካት ካርሎስ ፎርብስን ከአያክስ ለማስፈረም መስማማቱ ተገልጿል፡፡
ፔድሮ ኔቶ ሰማያዊዎቹን በይፋ ለመቀላቀል የሚያስችለውን የህክምና ምርመራ ለማድረግ ቀጠሮ መያዙ ታውቋል፡፡
በተመሳሳይ ባርሴሎና ስፔናዊውን አጥቂ ዳኒ ኦልሞን አስፈርሟል፡፡
ኦልሞ በባርሴሎና እስከ 2030 የሚያቆየውን…
Read More...
ኢትዮጵያ የምትጠበቅበት የሴቶች 10 ሺህ ሜትር ፍጻሜ ዛሬ ምሽት ይካሄዳል
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ33ኛው የፓሪስ ኦሊምፒክ ኢትዮጵያ የምትጠበቅበት የሴቶች 10 ሺህ ሜትር ፍጻሜ ውድድር ዛሬ ምሽት ይካሄዳል፡፡
በፍጻሜው አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ፣ አትሌት ጽጌ ገብረሰላማና አትሌት ፎትዬን ተስፋይ ኢትዮጵያን በመወከል ብርቱ ፉክክር ያደርጋሉ፡፡
ውድድሩ ምሽት 3 ሰዓት ከ57 ደቂቃ ላይ በስታደ ደ ፍራንስ ብሔራዊ ስታዲየም…
በ1500 ሜትር ማጣሪያ ጉዳፍ ፀጋይና ድርቤ ወልተጂ ለፍጻሜ አለፉ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ1500 ሜትር የሴቶች ግማሽ ፍጻሜ ውድድር አትሌት ጉዳፍ ጸጋይና ድርቤ ወልተጂ አልፈዋል፡፡
በፓሪስ እየተካሄደ በሚገኘው 33ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች የዛሬ መርሐ-ግብር የ1 ሺህ 500 ሜትር ሴቶች የግማሽ ፍጻሜ ውድድር ምሽት ላይ ተካሂዷል፡፡
አትሌት ድርቤ ወልተጂ 1ኛ ደረጃ እንዲሁም አትሌት ጉዳፍ ጸጋይ 4ኛ ደረጃ…
አትሌት ለሜቻ ግርማ በመልካም የጤና ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ተገለፀ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የ3 ሺህ መስናክል አትሌት ለሜቻ ግርማ ካጋጠመው ጉዳት አገግሞ በመልካም የጤና ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ተገለፀ፡፡
አትሌቱ ትናንት ምሽት በፈረንሳይ ፓሪስ ኦሊምፒክ በተካሄደው የወንዶች 3 ሺህ ሜትር መሰናክል ውድድር በመጨረሻ ዙር የመሰናከሉ ጠልፎት በመውደቁ ጉዳት ማስተናገዱ ይታወሳል፡፡
በዚህም ወደ ሆስፒታል ገብቶ…
እሁድ ሊካሄድ የነበረው የአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ ጨዋታ ተራዘመ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፊታችን እሁድ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ኢትዮጵያ ቡና መካከል ሊደረግ የነበረው የአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ ጨዋታ ተራዘመ፡፡
ጨዋታው በአዲስ አበባ ስታዲየም ሐምሌ 5 ቀን 2016 ዓ.ም ሊከናወን ታስቦ የነበረ ቢሆንም ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል፡፡…
‘አሰልጣኟ አይደለህም፣ አናውቅህም’ ተብየ ኦሊምፒኩን እንዳልከታተል ተደርጌያለሁ – የአትሌት ጽጌ ዱጉማ አሰልጣኝ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ‘አሰልጣኟ አይደለህም፣ አናውቅህም’ ተብየ ኦሊምፒኩን እንዳልከታተል ተደርጌያለሁ ሲል የአትሌት ጽጌ ዱጉማ አሰልጣኝ ዓለሙ ዋቅጅራ ተናገረ፡፡
አሰልኙ የፓሪስ ኦሊምፒክ መለያ ባጅ መከልከሉን ተክትሎ በኢትይጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ አመራሮች ላይ ቅሬታውን አቅርቧል፡፡
ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረገው አሰልጣኝ…
በ5 ሺህ ሜትር የወንዶች ሩጫ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ለፍጻሜ ደረሱ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ33ኛው የፓሪስ ኦሊምፒክ በ5 ሺህ ሜትር የወንዶች ሩጫ አትሌት ሐጎስ ገብረ ሕይወት፣ ቢንያም መሐሪ እና አዲሱ ይሁኔ ለፍጻሜ አልፈዋል፡፡
የ5 ሺህ ሜትር የወንዶች ማጣሪያ ውድድር 6 ሰዓት ከ10 ላይ ተካሂዷል፡፡
በዚህም አትሌት ሐጎስ በምድብ አንድ 2ኛ እንዲሁም በምድብ ሁለት ቢንያም መሐሪና አዲሱ ይሁኔ በቅደም ተከተል…