Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

 ኢትዮጵያ ከ12 ዓመት በኋላ በአትሌት አበባ አረጋዊ የነሐስ ሜዳሊያ አገኘች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በፈረንጆቹ 2012 በለንደን በተካሄደው የአሊምፒክ ጨዋታዎች ኢትዮጵያን በ1 ሺህ 500 ሜትር የወከለችው አትሌት አበባ አረጋዊ ከ12 ዓመት በኋላ ሜዳሊያዋን አግኝታለች። አትሌቷ ከ12 ዓመት በፊት በለንደን በተካሄደው የ1 ሺህ 500 ሜትር የሴቶች ፍፃሜ ውድድር 5ኛ በመውጣት አጠናቃለች፡፡ ይሁን እንጂ በውጤቱ ተሳትፎ የነበራቸው ሌሎች አትሌቶች በተለያዩ ምክንያቶች በዓለም ዓቀፉ የኦሊምፒክ ኮሚቴ ውጤታቸው እንዲሰረዝ ተደርጓል፡፡ ይህን ተከትሎም በወቅቱ 5ኛ ደረጃን ይዛ ያጠናቀቀችው አትሌት…
Read More...

ከኢትዮጵያ ርቆ የቆየውን የማራቶን ኦሊምፒክ ድል በማስመለሴ ደስ ብሎኛል – አትሌት ታምራት ቶላ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከኢትዮጵያ ርቆ የቆየውን የማራቶን ኦሊምፒክ ድል በማስመለሴ ደስ ብሎኛል ሲል በኦሊፒኩ በወንዶች ማራቶን የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊው ታምራት ቶላ ተናገረ፡፡ አትሌት ታምራት ቶላን ጨምሮ በፈረንሳይ ፓሪስ በተካሄደው 33ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች የተሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ሲደርስ ደማቅ አቀባበል…

31 ክብረ ወሰኖች የተሻሻሉበት የፓሪሱ ኦሊምፒክ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በፈረንሳይ አስተናጋጅነት የተካሄደው 33ኛው የፓሪሱ ኦሊምፒክ 31 አዳዲስ ክብረ ወሰኖች ሲመዘገቡበት በርካታ አይረሴ ድራማዊ ክስተቶችንም አስተናግዶ አልፏል፡፡ የደቡብ ኮሪያ አትሌቶች በመድረኩ የሰሜን ኮሪያ ተብለው መጠራታቸው እንዲሁም በደቡብ ሱዳን ብሄራዊ መዝሙር ምትክ የሱዳን ብሄራዊ መዝሙር መለቀቁ ኦሎምፒኩን አነጋጋሪ…

የፓሪስ ኦሊምፒክ የመዝጊያ ሥነ- ሥርዓት ዛሬ ምሽት ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የ33ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች የመዝጊያ ሥነ-ሥርዓት 80 ሺህ ተመልካቾችን በሚያስተናግደው በስታድ ደ ፍራንስ ብሔራዊ ስታዲየም ከምሽቱ 4 ሠዓት ጀምሮ ይከናወናል፡፡ የኦሊምፒክ ባንዲራም 34ኛውን የኦሊምፒክ ጨዋታዎች በፈረንጆቹ 2028 ለምታስተናግደው ሎስ አንጀለስ የውድድር አዘጋጆች የማስተላለፍ መርሐ-ግብር ይከናወናል፡፡…

ኢትዮጵያ በሴቶች ማራቶን የብር ሜዳሊያ አገኘች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ በ33ኛው የፓሪስ ኦሊምፒክ ወድድር በሴቶች ማራቶን አትሌት ትዕግስት አሰፋ ለሀገሯ የብር ሜዳሊያ አስገኝታለች፡፡ በ33ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የተጠበቁበት የሴቶች ማራቶን ውድድር ከጠዋቱ 3 ሰዓት ጀምሮ ተካሂዷል፡፡ በዚህም አትሌት ትዕግስት አሰፋ ርቀቱን 2ኛ ሆና በማጠናቀቅ ለሀገሯ የብር ሜዳሊያ…

ኢትዮጵያ በሴቶች 1 ሺህ 500 ሜትር ውድድር የሜዳሊያ ሰንጠረዥ ውስጥ መግባት አልቻለችም

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በፓሪስ እየተካሄደ ባለው 33ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች ኢትዮጵያ በሴቶች 1 ሺህ 500 ሜትር ውድድር የሜዳሊያ ሰንጠረዥ ውስጥ መግባት አልቻለችም። ከምሽቱ 3 ሰዓት ከ15 ላይ በተካሄደው የ1 ሺህ 500 ሜትር ሴቶች የፍጻሜ ውድድር ኢትዮጵያን በመወከል አትሌት ድርቤ ወልተጂ እና ጉዳፍ ፀጋይ ተሳትፈዋል። በዚህም አትሌት ድርቤ…