ስፓርት
በሎስአንጀለስ በተካሄደ የ1 ሺህ 500 ሜትር ውድድር ድርቤ ወልተጂ አሸነፈች
አዲስ አበባ፣ ግንቦት11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሎስአንጀለስ በተካሄደ የ1 ሺህ 500 ሜትር የሴቶች ሩጫ ውድድር ድርቤ ወልተጂ አሸንፋለች፡፡
አተሌት ድርቤ ርቀቱን 3 ደቂቃ 55 ሰከንድ ከ25 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ ነው ቀዳሚ የሆነችው፡፡
ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊ አትሌት ፍሬወይኒ ሃይሉ ደግሞ 3 ደቂቃ 55 ሰከንድ ከ48 ማይኮሮ ሰከንድ በመግባት 2ኛ ደረጃ መያዟን የፌደሬሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡
Read More...
በፕሪሚር ሊጉ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ሀድያ ሆሳዕና አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ25ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ሀድያ ሆሳዕና አንድ አቻ ተለያይተዋል፡፡
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ በበረከት ወልዴ ጎል ሲመራ ቢቆይም ከረፍት መልስ ኡመድ ኡኩሪ ባስቆጠራት ጎል ሀድያ ሆሳዕና ነጥብ ተጋርቷል፡፡
ውጤቱን ተከትሎ ፈረሰኞቹ በ40 ነጥብ 4ኛ…
በ5000 ሜትር የወንዶች ውድድር ሰለሞን ባረጋ አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሎስ አንጀለስ በተካሄደው የ5000 ሜትር የወንዶች ሩጫ ሰለሞን ባረጋ 12:51.60 በመግባት ውድድሩን በበላይነት አጠናቋል፡፡
በሪሁ አረጋዊ ደግሞ በ12:52.09 በመግባት በ2ኛነት ማጠናቀቁን ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ፡፡
ኮል ፓልመር የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ምርጥ ወጣት ተጫዋች ሽልማትን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቼልሲው የአማካይ ስፍራ ተጫዋች ኮል ፓልመር የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ2023/24 የዓመቱ ምርጥ ወጣት ተጫዋች ሽልማትን አሸንፏል፡፡
ፓልመር የዓመቱ ምርጥ ወጣት ተጫዋች የመጨረሻ እጩ የነበሩትን ኧርሊንግ ሃላንድ እና ቡካዮ ሳካን በመበልጥ ነው ማሸነፍ የቻለው፡፡
በ42 ሚሊየን ዩሮ ከማንቼስተር ሲቲ ቼልሲን የተቀላቀለ…
በፕሪሚየር ሊጉ ባሕርዳር ከተማ ሀምበሪቾን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ25ኛ ሣምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ባሕርዳር ከተማ ሀምበሪቾን 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡
ባሕርዳር ከተማ ሀምበሪቾን በረታበት ጨዋታ ፍፁም ጥላሁን ሁለቱንም ጎሎች ከመረብ ማሳረፍ ችሏል፡፡
ውጤቱን ተከትሎም የጣና ሞገዶቹ ነጥባቸውን 44 በማድረስ ባሉበት 3ኛ ደረጃን ማስጠበቅ ሲችሉ÷ ሀምበሪቾ 8 ነጥቦችን በመያዝ የሊጉ…
አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በፓሪሱ ኦሎምፒክ የስፖርት ቤተሰቡ የተለመደውን ድጋፍ እንዲሰጠው ጠየቀ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)አንጋፋው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በ2024ቱ የፓሪስ ኦሎምፒክ የመጨረሻ ድሉን ለማስመዘገብ በሚያደረገው ጥረት የስፖርት ቤተሰቡ የተለመደውን ድጋፍ እንዲሰጠው ጠየቀ፡፡
አትሌቱ በ2024 የፓሪስ ኦሊምፒክ ኢትዮጵያን በመወከል እንዲሳተፍ ያደረገው ጥረት በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተቀባይነት ማግኘቱን ተከትሎ በማኅበራዊ ትስስር…
በፓሪስ ኦሊምፒክ ማራቶን ቀነኒሳ በቀለን ጨምሮ ተሳታፊ አትሌቶች ተለዩ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌቲክስ ፌደሬሽን በፓሪስ ኦሊምፒክ 2024 ማራቶን አትሌት ቀነኒሳ በቀለን ጨምሮ በሁለቱም ጾታ የሚሳተፉ እና ተጠባባቂ አትሌቶችን ይፋ አድርጓል፡፡
በዚህም በወንዶች አትሌት ቀነኒሳ በቀለ፣ ሲሳይ ለማ እና ዴሬሳ ገለታ ተካትተዋል፡፡
በዚሁ ቡድን አትሌት ታምራት ቶላ እና ኡሰዲን መሐመድ በተጠባባቂነት መካተታቸውን…