ስፓርት
በፕሪሚየር ሊጉ ቫር ተግባራዊ እንዳይደረግ የሚያስችል ድምጽ ሊሰጥ ነው
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች በሚቀጥለው የውድድር ዓመት በተንቀሳቃሽ ምስል የታገዘ ዳኝነት (ቫር) ተግባራዊ እንዳይደረግ የሚያስችል ድምጽ ሊሰጡ መሆኑን ፕሪሚየር ሊጉ አስታውቋል፡፡
ቫር በፕሪሚየር ሊጉ ከፈረንጆቹ 2019 ጀምሮ ተግባራዊ የተደረገ ሲሆን÷የተወሰኑ ክለቦች በቫር ውሳኔ ደስተኛ አለመሆናቸውን እና እግር ኳሱን እየረበሸው እንደሚገኝ ሲገልጹ ቆይተዋል፡፡
በቫር ቅሬታ ካለባቸው ክለቦች አንዱ የሆነው ወልቨርሃምፕተን ቫር ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ ተግባራዊ እንዳይደረግ የሚያስችል ውሳኔ ሃሳብ…
Read More...
ኢትዮጵያ ቡና ወላይታ ድቻን 2 ለ 1 አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 24ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ቡና ወላይታ ድቻን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
የኢትዮጵያ ቡናን የማሸነፊያ ግቦች መስፍን ታፈሰ እና መሃመድ ኑር ናስር አስቆጥረዋል፡፡
ወላይታ ድቻን ከሽንፈት ያላደነችዋን ብቸኛ ግብ ደግሞ ብዙአየሁ ሰይፉ ከመረብ አሳርፏል፡፡
በሌላ በኩል ሀዋሳ ከተማ…
በርንሌይ ከእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መውረዱ ተረጋገጠ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በርንሌይ ሁለተኛው ወራጅ ክለብ መሆኑ ተረጋግጧል።
ዛሬ በተደረገ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ቶተንሃም ሆትስፐርስ በርንሌይን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
ውጤቱን ተከትሎም በርንሌይ በ24 ነጥብ ወደ ሻምፒየን ሺፑ መውረዱን አረጋግጧል።
በሌሎች ጨዋታዎች ኢቨርተን ሼፍልድ ዩናይትድን 1…
ማንቼስተር ሲቲ ፉልሃምን በማሸነፍ የዋንጫ ግስጋሴውን አጠናክሯል
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማንቼስተር ሲቲ ፉልሃምን 4 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
የማንቼስተር ሲቲን የማሸነፊያ ግቦች ግቫርዲዮል (2)፣ ፎደን እና አልቫሬዝ አስቆጥረዋል፡፡
ውጤቱን ተከትሎም ማንቼስተር ሲቲ 85 ነጥቦችን በመሰብሰብ የሊጉን መሪነት ማጠናከር ችሏል፡፡
የ2024 የፓሪስ ኦሎምፒክ የችቦ ማብራት ፕሮግራም በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) "ኢትዮጵያ ትወዳዳር፣ ተወዳድራም ታሸንፍ'' በሚል መሪ ሀሳብ የ2024 የፓሪስ ኦሎምፒክ የችቦ ማብራት ፕሮግራም በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
በስነ ስርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት አሸብር ወልደጊዮርጊስ (ዶ/ር)፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ እና የደቡብ…
ኪሊያን ምባፔ በውድድር ዓመቱ መጨረሻ ከፒኤስጂ ጋር እንደሚለያይ ይፋ አደረገ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኪሊያን ምባፔ በውድድር ዓመቱ መጨረሻ ከፒኤስጂ ጋር እንደሚለያይ ይፋ አድርጓል፡፡
ፈረንሳያዊው አጥቂ ምባፔ ሪያል ማድሪድን ይቀላቀላል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በዶሃ የዳይመንድ ሊግ 3 ሺህ መሰናክል የሩጫ ውድድር አትሌት ሳሙኤል ፍሬው በቀዳሚነት አጠናቀቀ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኳታር ዶሃ በተካሄደ የዳይመንድ ሊግ 3 ሺህ መሰናክል የሩጫ ውድድር አትሌት ሳሙኤል ፍሬው በቀዳሚነት አጠናቀቀ።
አትሌቱ ውድድሩን 8:07.25 በሆነ ጊዜ በመግባት ነው ውድድሩን ያሸነፈ ሲሆን፤ ኬንያዊው አትሌት ኪበብዎት አብራሃም 8:07.38 እንዲሁም አትሌት ጌትነት ዋለ 8:09.69 በሆነ ጊዜ በመግባት ሁለተኛ እና ሶስተኛ…