Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ጁለን ሎፔቴጉይ የዌስትሃም አሰልጣኝ ለመሆን ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ስፔናዊው አሰልጣኝ ጁለን ሎፔቴጉይ በውድድር ዓመቱ መጨረሻ የዌስትሃም ዩናይትድ አሰልጣኝ ለመሆን ተስማምተዋል፡፡ ስምምነቱ ተፈጻሚ ከሆነም የ57 ዓመቱ የቀድሞ የዎልቭስ አሰልጣኝ በድጋሚ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ እንደሚመለሱ ይጠበቃል፡፡ የመዶሻዎቹ አለቃ ዴቪድ ሞይስ ዌስትሃም ባለፉት 9 ጨዋታዎች አንድ ጊዜ ብቻ ማሸንፉ እና ከዩሮፓ ሊግ ውጪ መሆኑን ተከትሎ ጫና ውስጥ ገብተው ቆይተዋል፡፡ በዚህ ክረምት የኮንትራት ውላቸው የሚጠናቀቀው ዴቪድ ሞይስ የክለብ ቆይታቸውን በተመለከተ የፊታችን ግንቦት…
Read More...

በፕራግ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታ አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቼክ ሪፐብሊክ በተደረገ የፕራግ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታ አሸነፉ። በወንዶች አትሌት ለሚ ብርሃኑ 2፡08፡45 በሆነ ሰዓት በመግባት ውድድሩን በቀዳሚነት ሲያጠናቅቅ፤ በውድድሩ የተሳተፉት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ሄርጳሳ ነጋሳ እና አባይነህ ደጉ አምስተኛ እና ሰባተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን…

ፋሲል ከነማ ሀድያ ሆሳዕናን 2 ለ1 አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 23ኛ ሣምንት ፋሲል ከነማ ሀድያ ሆሳዕናን 2 ለ 1 አሸንፏል፡፡ ምሽት 12 ሠዓት ላይ በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው የፋሲል ከነማን ጎሎች ዣቪየር ሙሉ እና ምኞት ደበበ አስቆጥረዋል፡፡ እንዲሁም የሀድያ ሆሳዕናን ብቸኛ ጎል ደግሞ ዳዋ ሆጤሳ ከመረብ አሳርፏል፡፡

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ኒውካስልና ኖቲንግሃም ፎረስት ድል ቀናቸው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ36ኛ ሣምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ኒውካስል እና ኖቲንግሃም ፎረስት ተጋጣሚዎቻቸውን ሲያሸንፉ ብሬንትፎርድ ከፉልሃም አቻ ተለያይቷል፡፡ በዚህም ኒውካስል በርንሌይን 4 ለ1 እንዲሁም ኖቲንግሃም ፎረስት ሸፊልድ ዩናይትድን 3 ለ1 ረትተዋል፡፡ ብሬንትፎርድ እና ፉልሃም ደግሞ ያለምንም ጎል አቻ ተለያይተዋል፡፡

ሲዳማ ቡና ወላይታ ድቻን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 23ኛ ሣምንት ሲዳማ ቡና ወላይታ ድቻን 2 ለ 1 አሸነፈ፡፡ የሲዳማ ቡናን ጎሎች ይስሃቅ ካኖ እና ማይክል ኪፕሮቪ ሲያስቆጥሩ÷ የወላይታ ድቻን ጎል ዘላለም አባተ ማስቀጠር ችሏል፡፡ በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም እየተካሄደ የሚገኘው የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 23ኛ ሣምንት ጨዋታ…

አርሰናል የዋንጫ ተፋላሚነቱን አጠናከረ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አርሰናል በርንማውዝን 3 ለ 0 በማሸነፍ የዋንጫ ተፋላሚነቱን አጠናክሯል፡፡ በ36ኛ ሣምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አርሰናል በርንማውዝን በረታበት ጨዋታ ቡካዮ ሳካ፣ ትሮሳርድ እና ራይስ ጎሎቹን ማስቆጠር ችለዋል፡፡ መድፈኞቹ ዛሬ ማሸነፋቸውን ተከትሎም ነጥባቸውን 83 በማድረስ ፕሪሚየር ሊጉን እየመሩ ይገኛሉ፡፡

በፕሪሚየር ሊጉ ኢትየጵያ መድን ሲያሸንፍ መሪው ንግድ ባንክ ነጥብ ጥሏል

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 23ኛ ሳምንት ኢትዮጵያ መድን ሀምበሪቾን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸነፈ። በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም 9:00 ሰዓት ላይ በተካሄደው ጨዋታ አቡበከር ሳኒ በ68ኛው እና በ75ኛው ደቂቃ ባስቆጠራቸው ጎሎች ኢትዮጵያ መድን ተጋጣሚውን ሀምበሪቾን አሸንፎ ሶስት ነጥብ ይዞ ወጥቷል። በተመሳሳይ በዛሬው…