ስፓርት
የካፍ ክለቦች ውድድር የምድብ ድልድል ይፋ ሆነ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2024/25 የውድድር ዘመን የካፍ ክለቦች ውድድር የምድብ ድልደል ይፋ ተደርጓል፡፡
በዚህም መሰረት በቻምፒየንስ ሊግ የሚሳተፈው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከዩጋንዳው ቪላ ጋር ሲመደብ በኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የሚሳተፈው ኢትዮጵያ ቡና ደግሞ ከኬንያው ኬንያ ፖሊስ ክለብ ጋር ተመድበዋል፡፡
Read More...
የተጫዋቾች የዝውውር ጊዜ የሚከፈትበት ቀን ላይ ማስተካከያ ተደረገ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2017 የውድድር ዘመን የተጫዋቾች የዝውውር ጊዜ የሚከፈትበት ቀን ላይ ማስተካከያ መደረጉን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን አስታወቀ፡፡
ፌደሬሽኑ ከዚህ በፊት የ2017 የውድድር ዘመን የዝውውር ጊዜ ሐምሌ 15 ቀን 2016 እንደሚከፈት ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።
ይሁን እንጂ ቀኑን ማስተካከል አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ አዲሱ…
የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ኦሊቪየ ዢሩ ከብሔራዊ ቡድኑ ራሱን አገለለ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪው ኦሊቪየ ዢሩ በ37 ዓመቱ ከብሔራዊ ቡድኑ ራሱን ማግለሉን አስታውቋል፡፡
ዢሩ በ17ኛው የአውሮፓ ዋንጫ ትናንት ምሽት ሀገሩ ፈረንሳይ ከስፔን ጋር ጨዋታዋን ስታደርግ ተቀይሮ በመግባት የተጫወተ ሲሆን በሽንፈት ከተጠናቀቀው ጨዋታ በኋላ በይፋ ራሱን ከብሔራዊ ቡድኑ አግልሏል፡፡…
ከስፔን ጋር ለፍጻሜ የሚፋለመው ብሔራዊ ቡድን ዛሬ ይለያል
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከስፔን ጋር ለፍጻሜ የሚፋለመው ብሔራዊ ቡድን የሚለይበት የእንግሊዝና ኔዘርላንድስ (ሆላንድ) ጨዋታ ተጠባቂ ነው፡፡
በ17ኛው የአውሮፓ ዋንጫ የግማሽ ፍጻሜ ሁለተኛ መርሐ-ግብር እንግሊዝ ከኔዘርላንድስ ዛሬ ምሽት 4 ሠዓት ላይ በሲግናል ኢዱና ፓርክ ስታዲየም የሚያደርጉት ብርቱ ፍልሚያ ይጠበቃል፡፡
በሩብ ፍጻሜው እንግሊዝ…
ስፔንና ፈረንሳይ ተጠባቂ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ያደርጋሉ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአውሮፓ ዋንጫ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ምሽት 4 ሠዓት ላይ ስፔን ከፈረንሳይ የሚያደርጉት ፍልሚያ ተጠባቂ ነው፡፡
17ኛው የአውሮፓ ዋንጫ በጀርመን አስተጋጅነት እየተካሄደ ሲሆን÷ ዛሬ ስፔን ከፈረንሳይ 75 ሺህ 24 ተመልካች በሚያስተናግደው አሊያንዝ አሬና ስታዲየም የሚያድርጉት ጨዋታ የስፖርት ቤተሰቡን ቀልብ ስቧል።
ከፍተኛ…
ኢትዮጵያ ቡና የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊ ሆነ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2016 ዓ.ም የኢትዮጵያ ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታ በወላይታ ድቻና ኢትዮጵያ ቡና መካከል ተካሂዷል፡፡
ከቀኑ 9 ሰዓት በአዲስ አበባ ስታዲየም በደመቀ ሁኔታ በተከናወነ ጨዋታ መደበኛው ክፍለ ጊዜ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት በመጠናቀቁ ተጨማሪ 30 ደቂቃ ተሰጥቷል፡፡
በዚህም ኢትዮጵያ ቡና ወላይታ ድቻን 2 ለ1 ረትቶ የ2016 ዓ.ም…
በፓሪስ በተካሄደው የዳይመንድ ሊግ ውድድር በ3ሺህ ሜትር የወንዶች መሰናክል አብርሃም ስሜ አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በፈረንሳይ ፓሪስ በተካሄደው በዳይመንድ ሊግ ውድድር በ3ሺህ ሜትር የወንዶች መሰናክል ኢትዮጵያዊው አትሌት አብርሃም ስሜ አሸንፏል፡፡
አትሌቱ 8:02.36 በመግባት ነው ውድድሩን በቀዳሚነት ያጠናቀቀው፡፡