ስፓርት
ማንቼስተር ዩናይትድ ፓትሪክ ዶርጉን አስፈረመ
አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ማንቼስተር ዩናይትድ ወጣቱን ተከላካይ ፓትሪክ ዶርጉን ከጣሊያኑ ክለብ ሊቼ በ35 ሚሊየን ዩሮ ማስፈረሙን ይፋ አድርጓል፡፡
የ20 ዓመቱ ዴንማርካዊ ተከላካይ በዩናይትድ እስከ ፈረንጆቹ 2030 የሚያቆየውን ውል ፈርሟል።
በሌላ የዝውውር መረጃ የማንቼስተር ዩናይትዱ ተጫዋች ማርከስ ራሽፎርድ አስቶን ቪላን በውሰት ለመቀላቀል መስማማቱ ተገልጿል።
በኃይለ ማርያም ተገኝ
Read More...
በፕሪሚየር ሊጉ አርሰናል ከማንቼስተር ሲቲ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል
አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ24ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ዛሬ ምሽት 1፡30 አርሰናል ከማንቼስተር ሲቲ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡
በሊጉ ጨዋታዎች 47 ነጥቦችን በመሰብሰብ 2ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው አርሰናል ከመሪው ሊቨርፑል ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ለማጥበብ ይፋለማል፡፡
በተመሳሳይ ከአርሰናል…
ቅዱስ ጊዮርጊስ ከኢትዮጵያ ቡና የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል
አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ18ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐግብር ከቀኑ 9 ሰዓት ቅዱስ ጊዮርጊስ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡
በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በሚደረገው በዚህ ጨዋታ 28 ነጥቦችን በመሰብሰብ በደረጃ ሰንጠረዡ ሁለተኛ ላይ የተቀመጡት ፈረሰኞቹ 22 ነጥቦችን በመሰብሰብ 7ኛ ደረጃ…
በራስ አል ኬማህ ግማሽ ማራቶን አትሌት እጅጋየሁ ታየ አሸነፈች
አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በተባበሩት አረብ ኢሜሬቶች በተካሄደው የራስ አል ኬማህ የሴቶች ግማሽ ማራቶን አትሌት እጅጋየሁ ታየ ድል ቀንቷታል፡፡
እጅጋየሁ ግማሽ ማራቶኑን 1 ሰዓት ከአምስት ደቂቃ ከ52 ሴኮንድ በመጨረስ ነው ማሸነፍ የቻለችው፡፡
ኬኒያዊያኖቹ ጁዲ ኬምቦ እና ጀሲካ ቼላንጋት ሁለተኛ እና ሶስተኛ በመሆን ውድድሩን ማጠናቀቃቸውን ከአዘጋጅ…
በቻምፒዮንስ ሊግ ጥሎ ማለፍ ምድብ ሪያል ማድሪድ ከማንቼስተር ሲቲ ተደለደለ
አዲስ አበባ፣ ጥር 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ድልድል የስፔኑ ሪያል ማድሪድ እና የእንግሊዙ ማንቼስተር ሲቲ ተገናኝተዋል።
የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ድልድል በዛሬው ዕለት ወጥቷል።
የሁለቱ ሃያላን እግር ኳስ ቡድኖች ፍልሚያ የመጀመሪያው ዙር ጨዋታ በኢትሃድ የሚካሄድ…
ቅዱስ ጊዮርጊስ ወላይታ ድቻን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 17ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ ወላይታ ድቻን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
ቀን 9 ሰዓት በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደ ጨዋታ አብዱ ሳሚዮ እና አማኑኤ ኤርቦ የቅዱስ ጊዮርጊስ ግቦችን አስቆጥረዋል፡፡
ውጤቱን ተከትሎም ፈረሰኞቹ ነጥባቸውን ወደ 28 ከፍ…
የሻምፒየንስ ሊግ የመጀመሪያው ዙር የምድብ ጨዋታዎች ዛሬ ፍጻሜያቸውን ያገኛሉ
አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሻምፒየንስ ሊግ የመጀመሪያው ዙር የመጨረሻ የምድበ ጨዋታዎች ዛሬ ፍጻሚያቸውን ሲያገኙ ማንቼስተር ሲቲ ከውድድሩ ላለመሰናበት የሚያደርገው ፍልሚያ ይጠበቃል፡፡
ምሽት 5 ሰዓት ላይ ማንቼስተር ሲቲ በኢቲሃድ ስታዲዬም ክለብ ብሩጅን የሚያስተናግድ ሲሆን ከውድድሩ ላለመሰናበት እና የደርሶ መልስ የማጣሪያ ጨዋታን እድል ለማግኘት…