Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

በፓሪስ በተካሄደው የዳይመንድ ሊግ ውድድር በ3ሺህ ሜትር የወንዶች መሰናክል አብርሃም ስሜ አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በፈረንሳይ ፓሪስ በተካሄደው በዳይመንድ ሊግ ውድድር በ3ሺህ ሜትር የወንዶች መሰናክል ኢትዮጵያዊው አትሌት አብርሃም ስሜ አሸንፏል፡፡ አትሌቱ 8:02.36 በመግባት ነው ውድድሩን በቀዳሚነት ያጠናቀቀው፡፡
Read More...

40ኛው የሻምበል አበበ ቢቂላ ማራቶን በኦሮሚያ ፖሊስ አሸናፊነት ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐዋሳ ከተማ የተካሄደው 40ኛው የሻምበል አበበ ቢቂላ ማራቶን ውድድር በሁለቱም ጾታ የኦሮሚያ ፓሊስ አሸናፊ ሆኗል፡፡ በወንዶች የተካሄደውን ውድድር በወንዶች አትሌት ጎሳ አምበሱ ከኦሮሚያ ፖሊስ በቀዳሚነት አጠናቅቋል፡፡ በዚሁ ውድድር አትሌት ጊዜው አበጀ ከኢትዮ ኤልክትሪክ ሁለተኛ እንዲሁም አትሌት ሳኅለሥላሴ ንጉሴ…

የመቻል ስፖርት ክለብ የገቢ ማሰባሰቢያ በስካይ ላይት ሆቴል ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የመቻል ስፖርት ክለብ የገቢ ማሰባሰቢያ (ቴሌቶን) ዛሬ ከምሽቱ 12 ሠዓት ጀምሮ በስካይ ላይት ሆቴል እንደሚካሄድ ተገለጸ፡፡ መቻል ስፖርት ክለብን ወደ ቀደመ ገናና ስሙ የመመለስና ክለቡን የማጠናከር ሥራ እየተከናወነ ሲሆን÷ የገቢ ማሰባሰቢያውም የእዚሁ ሥራ አካል መሆኑ ተመላክቷል፡፡ ክለቡን ለማጠናከር እና በኢትዮጵያ…

የፌደራል ማረሚያ ቤቶች 3 ዋንጫዎችን በማንሣት የኢትዮጵያ ቦክስ ክለቦች ሻምፒዮን ሆነ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራል ማረሚያ ቤቶች በሦስት ዘርፎች የተካሄዱ ውድድሮችን በማሸነፍ የኢትዮጵያ ቦክስ ክለቦች ውድድር አሸናፊ ሆኗል፡፡ በኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽን  አዘጋጅነት ለአራት ቀናት ሲካሄድ የነበረው የክለቦች የቦክስ ውድድር ተጠናቅቋል፡፡ በውድድሩ ሰባት ክለቦች የተካፈሉ  ሲሆን÷ የሴቶቹ ውድድር በ “ኤ” ምድብ እንዲሁም የወንዶቹ…

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን ሆነ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የ2016 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን ሆነ፡፡ በፕሪሚየር ሊጉ 30ኛ ሳምንት መርሐ ግብር የዋንጫውን አሸናፊ የለዩ ሁለት ተጠባቂ ጨዋታዎች በተመሳሳይ ቀን 9 ሰዓት ላይ ተካሂደዋል፡፡ በዚህ መሰረትም በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኢትዮጵያ መድንን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት…

የፈረንሳይ ከዋክብት የጎል ድርቅ በአውሮፓ ዋንጫ አዲስ ታሪክ ሆኖ ተመዝግቧል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 29፣2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የላቀ ክህሎት ያላቸው ከዋክብትን የያዘው የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን በ17ኛው የአውሮፓ ዋንጫ በክፍት ጨዋታ አንድም ግብ ሳያስቆጥር ግማሽ ፍጻሜን በመቀላቀል አዲስ ታሪክ አስመዝግቧል፡፡ ትናንት ምሽት ከ120 ደቂቃ ፍልሚያ በኋላ ፈረንሳይ ፖርቹጋልን በመለያ ምት 5 ለ 3 በማሸነፍ ወደ ግማሽ ፍጻሜ ማለፏ ይታወሳል። የትናንት…

በአውሮፓ ዋንጫ እንግሊዝ ከስዊዘርላንድ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአውሮፓ ዋንጫ የሩብ ፍጻሜ መርሐ ግብር እንግሊዝና ስዊዘርላንድ የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው፡፡ የ17ኛው የአውሮፓ ዋንጫ የሩብ ፍጻሜ መርሐ ግብር ዛሬ ምሽት በሚደረጉ ሁለት ጨዋታዎች ይጠናቀቃል። በዚህም መሰረት እንግሊዝ ከስዊዘርላንድ ምሽት 1:00 ላይ በዱሴልዶርፍ ስታዲየም የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡ በጥሎ…