Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

በማንዴላ መታሰቢያ ዋንጫ የቦክስ ውድድር ም/ሳጅን ሮማን አሰፋ ተጋጣሚዋን በበቃኝ አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ አፍሪካ ደርባን ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው የማንዴላ መታሰቢያ ዋንጫ የቦክስ ውድድር ምክትል ሳጅን ሮማን አሰፋ ተጋጣሚዋን በበቃኝ አሸነፈች፡፡ ትናንት ምሽት ሀገሯን የወከለችው የአዲስ አበባ ፖሊሷ ምክትል ሳጅን ሮማን አሰፋ በ54 ኪሎ ግራም የናሚቢያ ተጋጣሚዋን በመጀመሪያው ዙር በበቃኝ አሸንፋለች፡፡ ውድድሩ እስከ ሚያዝያ 13 ቀን 2016 ዓ.ም የሚቀጥል መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ መረጃ ያመላክታል፡፡
Read More...

ቤተልሔም ወልዴ በማንዴላ አፍሪካን ቦክሲንግ ሻምፒዮና ተጋጣሚዋን በበቃኝ አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በማንዴላ አፍሪካን ቦክሲንግ ካፕ ሻምፒዮና ከደቡብ አፍሪካ አቻዋ ጋር የተጋጠመችው ቤተልሄም ወልዴ በበቃኝ አሸንፋለች፡፡ የመላው አፍሪካ ሻምፒዮኗ ቤተልሄም ወልዴ በሁለተኛ ዙር ላይ ተጋጣሚዋ ላይ ሀይለኛ ቡጢ በማሳረፍ ነው በዳኛ ውሳኔ ያሸነፈችው፡፡ በወንዶች ምድብ ኢትዮጵያን የወከሉት አቡዱሰላም አቡበከር፣ አቡበከር…

በደቡብ አፍሪካ እየተካሄደ በሚገኘው የቦክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ከደቡብ አፍሪካና ከሞሪሽየስ ጋር ትጋጠማለች

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ አፍሪካ እየተካሄደ በሚገኘው የማንዴላ አፍሪካን ቦክሲንግ ካፕ ሻምፒዮና ኢትዮጵያውያን ቦክሰኞች በሁለቱም ፆታ ከደቡብ አፍሪካ እና ከሞሪሽየስ አቻቸው ጋር ይፋለማሉ፡፡ ምሽት 1 ሰዓት በደርባን ከተማ በሚደረገው ውድድር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ቦክሰኞች የመጀመሪያ ውድድር በሁለቱም ፆታዎች ያደርጋሉ፡፡ በወንዶች 57…

የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የሩብ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት ይደረጋሉ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የሩብ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታ አርሰናል ከባየርንሙኒክ እንዲሁም ማንቸስተር ሲቲ ከሪያል ማድሪድ ዛሬ ምሽት 4:00 ላይ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል። ባየርንሙኒክ ከአርሰናል በአሊያንዝ አሬና ስታዲየም በሚያደርጉት ጨዋታ በአርሰናል በኩል ማርቲን ኦዲጋርድ እና ቡካዮ ሳካ በጉዳት ምክንያት መሰለፋቸው…

ፕሪሚየር ሊጉ ከ23ኛ ሣምንት ጀምሮ በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም እንደሚካሄድ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ‘በኢትዮጵያ ዋንጫ’ ጨዋታዎች ምክንያት ከተቋረጠ በኋላ ሲመለስ ከ23ኛ ሣምንት ጀምሮ በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡ የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከ16ኛ እስከ 22ኛ ሣምንት በድሬዳዋ ከተማ - ድሬዳዋ ስታዲየም እየተካሄደ መሆኑ ይታወቃል። ይሁን እንጂ ‘በኢትዮጵያ…

የሻምፒዮንስ ሊጉ የሩብ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታዎች ዛሬ ይደረጋሉ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የሩብ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት ይደረጋሉ፡፡ ዛሬ ምሽት ከሚደረጉት መርሐ ግብሮች ባርሴሎና በሜዳው ኑ ካምፕ የፈረንሳዩን ፓሪስ ሴንት ዠርሜይንን የሚያስተናግድበት ጨዋታ ይጠበቃሉ፡፡ ባለፈው ሳምንት ሁለቱ ቡድኖች በፓሪስ ፓርክ ዴስ ፕሪንስ ባደረጉት ጨዋታ ባርሴሎና 3ለ2…

አትሌት ሲሳይ ለማ በቦስተን ማራቶን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ ቦስተን ማራቶን አትሌት ሲሳይ ለማ አሸንፏል፡፡ አትሌት ሲሳይ ርቀቱን 2 ሰዓት 6 ደቂቃ ከ17 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ ነው ያሸነፈው፡፡ ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት መሃመድ ኢሳ ደግሞ ውድድሩን ሁለተኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቅቋል፡፡