Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክና ወልቂጤ ከተማ ድል ቀናቸው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክና ወልቂጤ ከተማ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል። በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 29ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ቀን 9 ሰዓት ላይ ሁለት ጨዋታዎች ተደርገዋል። በዚህ መሰረትም ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሻሸመኔ ከተማን 2 ለ 0 በማሸነፍ የሊጉን መሪነት አጠናክሯል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን የማሸነፊያ ግቦች አዲስ ግደይ እና ሱሌማን ሃሚድ ከመረብ አሳርፈዋል። ውጤቱን ተከትሎ ሻሸመኔ ከተማ ከኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ወደ ከፍተኛ ሊግ መውረዱ ተረጋግጧል።…
Read More...

ስዊዘርላንድ ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቀለች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ17ኛው የአውሮፓ ዋንጫ ስዊዘርላንድ የ2020 ሻምፒዮናዋን ጣልያንን 2 ለ 0 በመርታት ሩብ ፍጻሜውን የተቀላቀለች የመጀመሪያዋ ሀገር ሆናለች፡፡ ጎሎቹንም ፍሩለር እና ቫርጋስ በመጀመሪያው እና በሁለተኛው አጋማሽ አስቆጥረዋል፡፡ ውጤቱን ተከትሎም ስዊዘርላንድ በሩብ ፍጻሜው ከእንግሊዝና ስሎቫኪያ አሸናፊ ጋር የምትፋለም…

ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ29ኛ ሣምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ያለምንም ጎል አቻ ተለያይተዋል፡፡ ውጤቱን ተከትሎ ፋሲል ከነማ ነጥቡን ወደ 44 ከፍ በማድረግ ከአዳማ ከተማ እኩል 6ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡ እንዲሁም ወላይታ ድቻ በ34 ነጥብ 12ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ በተመሳሳይ 12 ሠዓት ላይ በተከናወነ…

“መቻል ለ ኢትዮጵያ” የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ነገ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) "መቻል ለ ኢትዮጵያ" የተሰኘ የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ በነገው ዕለት ሰኔ 23 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡ የጎዳ ላይ ሩጫው የመቻል ስፖርት ክለብን 80ኛው ዓመት የምስረታ በዓል ምክንያት በማድረግ ነው የሚካሄደው፡፡ መነሻና መድረሻውን መስቀል አደባባይ በሚያደርገው የሩጫ ውድድር በርካቶች…

የአውሮፓ ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ከዛሬ ጀምሮ ይካሄዳሉ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ17ኛው የአውሮፓ ዋንጫ የጥሎ ማለፍ መርሐ ግብር ከዛሬ ሰኔ 22 ጀምሮ እስከ ሰኔ 25 ቀን 2016 ዓ.ም ይከናወናሉ። በጀርመን አስተናጋጅነት እየተካሄደ ባለው ውድድር ጥሎ ማለፉን የተቀላቀሉ ብሔራዊ ቡድኖች ብርቱ ፉክክር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል። በዚህም ዛሬ ምሽት አንድ ሰዓት ላይ ስዊዘርላንድ ከዩሮ 2020 ሻምፒዮኗ…

ኢትዮጵያ መድን ሀድያ ሆሳዕናን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2016 (ኤፍቢ ሲ) በ29ኛ ሣምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ መድን ሀድያ ሆሳዕናን 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡ የመድንን ብቸኛ የማሸነፊያ ጎልም ወገኔ ገዛኸኝ በሁለተኛው አጋማሽ ከመረብ አሳርፏል፡፡

ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ አባላት ከ1 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር በላይ ሽልማት ተበረከተ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ23ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለተካፈለው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑካን ቡድን አባላት ከ1 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር በላይ የማበረታቻ ሽልማት ተበረከተላቸው፡፡ በካሜሩን ዱዋላ በተካሄደው 23ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ተካፍሎ ትናንት አዲስ አበባ ለገባው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ዛሬ በግዮን ሆቴል ዕውቅናና…