Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

አትሌት ሱቱሜ ከበደ በኮልካታ የ25 ኪሎ ሜትር ውድድር አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ሱቱሜ ከበደ በህንድ የተካሄደውን የኮልኮታ የ25 ኪሎ ሜትር  ውድድር በበላይነት አጠናቀቀች። አትሌቷ ውድድሩን 1፡19፡17 በሆነ ሰዓት በመግባት ቀዳሚ ሆናለች። አትሌት ሱቱሜን በመከተል ኬንያዊቷ አትሌት ቼፕንግኖ በ1፡19፡44 በሆነ ሰዓት ሁለተኛ ሆና ስታጠናቅቅ፤ ባህሬናዊቷ አትሌት ጂሳ ድሞ በ1፡21፡29 በሆነ ሰዓት ሶስተኛ ሆና ማጠናቀቅ ችላልች። ውድድሩ ሊካሄድ ሁለት ሳምንት ሲቀረው እንደምትሳተፍ ያረጋገጠችው…
Read More...

አትሌት ንብረት መላክ የባንግሴን ግማሽ ማራቶን ውድድርን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አትሌት ንብረት መላክ በታይላንድ ቾን ቡሪ የተካሄደውን የባንግሴን ግማሽ ማራቶን ውድድር አሸንፏል፡፡ አትሌት ንብረት ርቀቱን 1 ሰዓት 2 ደቂቃ ከ32 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ ነው ቀዳሚ መሆን የቻለው፡፡

የማንቼስተር ደርቢ ዛሬ ምሽት ይደረጋል

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ16ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ-ግብር የማንቼስተር ከተማ ክለቦች የሆኑት ማንቼስተር ሲቲ እና ማንቼስተር ዩናይትድ ምሽት ላይ የሚያድረጉት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡ ጨዋታው ምሽት 1 ሰዓት ከ30 በኢቲሃድ ስታዲየም የሚከናወን ሲሆን÷ በማንቼስተር ሲቲ በኩል ባለፈው ሳምንት በቀይ ካርድ ከሜዳ…

ማህበረሰብ አቀፍ ስፖርትን ባህል ማድረግ ይገባል-ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ማህበረሰብ አቀፍ ስፖርትን ባህል ማድረግ ይገባል-ከንቲባ አዳነች አቤቤ አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ)የከተማው ነዋሪ በአካልና በአዕምሮ የዳበረ እንዲሁም ጤናው የተጠበቀ እንዲሆን ማህበረሰብ አቀፍ ስፖርትን ባህል ማድረግ ይገባል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ፡፡ “ጤናማ የአኗኗር ዘይቤ ለሁሉአቀፍ የማህበረሰብ ጤንነት!” በሚል…

ሊቨርፑል እና አርሰናል ከተጋጣሚዎቻቸው ጋር አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ16ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ-ግብር መሪው ሊቨርፑል እና አርሰናል ከተጋጣሚዎቻቸው ጋር አቻ ተለያይተዋል፡፡ ምሽት 12 ሰዓት ላይ በአንፊልድ ፉልሃምን ያስተናገደው ሊቨርፑል 2 አቻ ሲለያይ፤ ኮዲ ጋክፖ እና ዲያጎ ጆታ ለሊቨርፑል እንዲሁም አንደሪያስ ፔሬራ እና ሮቤርቶ ሙኒዝ የፉልሃም ግቦች አስቆጥረዋል፡፡…

ዛሬ በእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ 5 ጨዋታዎች ይካሄዳሉ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 5፣2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ዛሬ በ16ኛው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ መርሐ ግብር አምስት ጨዋታዎች ይካሄዳሉ። በዕለቱ አርሰናል ከኤቨርተን እንዲሁም ሊቨርፑል ከፉልሃም ምሽት 12 ሰዓት ላይ የሚያድረጓቸው ጨዋታዎች ተጠባቂ ናቸው። በተመሳሳይ ኒውካስትል ከሌስተር ሰቲ፣ ዎልቭስ ከኤፕስዊች ምሽት 12 ሰዓት የሚጋጠሙ ሲሆን ፥ ምሽት 2፡30 ላይ…

የ2024 የአፍሪካ ምርጥ ተጫዋች የመጨረሻ እጩዎች ይፋ ሆኑ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የ2024 የአፍሪካ ምርጥ ተጫዋች የመጨረሻ አምስት እጩዎች ዝርዝር ይፋ ተደርጓል፡፡ የብራይተን ሆቭ አልቢዮን እና የኮትዲቯር ብሄራዊ ቡድን የፊት መስመር ተጫዋች ሲሞን አዲንግራ ከእጩዎቹ መካከል አንዱ ነው፡፡ ተጫዋቹ ኮትዲቯር አዘጋጅታ ባሸነፈችው የ2023 የአፍሪካ ዋንጫ ድንቅ ብቃቱን ማሳየቱ ተመላክቷል፡፡ ሲሞን…