ስፓርት
ኢትዮጵያ በ3 ሺህ ሜትር መሠናክል የሴቶች ውድድር የብር ሜዳሊያ አገኘች
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በካሜሩን ዱዋላ በተካሄደው 3 ሺህ ሜትር መሠናክል የሴቶች ውድድር አትሌት ዓለምናት ዋለ ሁለተኛ ሆና አጠናቀቀች፡፡
በዚሁ ውድድር የተሳተፈችው አትሌት መሠረት የሻነህ አራተኛ በመሆን ውድድሩን ማጠናቀቅ ችላለች፡፡
ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ ሀገራት የሚጠበቁባቸው የ23ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የማጠቃለያ ውድድሮች እየተካሄዱ ነው፡፡
እስከ አሁን በተካሄዱ ውድድሮችም ኢትዮጵያ በሁለቱም ጾታዎች የእርምጃ ውድድሮች 2 ወርቅ፣ በ10 ሺህ ሜትር ወንዶች 1 ወርቅና 1 ብር፣ በ5 ሺህ ሜትር…
Read More...
ረዳት አሰልጣኟ በተመለከቱት የቢጫ ካርድ ምክንያት ከምድቧ 2ኛ ደረጃን ያጣችው ስሎቬኒያ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጀርመን አስተናጋጅነት እየተካሔደ የሚገኘው 17ኛው የአውሮፓ ዋንጫ ዴንማርክ እና ስሎቪኒያ ተመሳሳይ ነጥብ እና ሪከርዶች እያሏቸው ደረጃ የተለያዩበት መንገድ በዓለም የእግርኳስ ቤተሰብ ዘንድ አግራሞትን ፈጥሯል፡፡
በምድብ ሶስት የተደለደሉት ሁለቱ ሀገራት ሶስት ጨዋታዎችን አድርገው በሶስቱም አቻ ወጥተው ሶስት ነጥቦችን መያዝ…
አቡበከር ናስር ከማሜሎዲ ሰንዳውንስ ጋር ተለያየ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አጥቂ መስመር ተጫዋቹ አቡበከር ናስር ከደቡብ አፍሪካው ክለብ ማሜሎዲ ሰንዳውንስ ጋር በይፋ ተለያይቷል፡፡
አቡበከር ቀጣይ ማረፊያው የጋናው ክለብ ሊሆን እንደሚችልም ተጠቁሟል፡፡
የ24 ዓመቱ አጥቂ በሰንዳውንስ ያንሰራራል ተብሎ ቢጠበቅም ባጋጠመው የቁርጭምጭሚት ጉዳት ምክንያት በውድድር ዓመቱ መሰለፍ…
በአውሮፓ ዋንጫ ቤልጂየም ከዩክሬን የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአውሮፓ ዋንጫ ቤልጂየም እና ከዩክሬን ዛሬ ምሽት የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡
በ17ኛው የአውሮፓ ዋንጫ ዛሬ ምሽት አራት ወሳኝ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታዎች ይደረጋሉ።
በዚህም ቤልጂየም ከዩክሬን እንዲሁም ፖርቹጋል ከጆርጂያ የሚያደርጓቸው ጨዋታዎች ተጠባቂ ናቸው፡፡
በምድብ አምስት ምሽት 1 ሰዓት ላይ ቤልጂየም…
በአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የእርምጃ ውድድር ኢትዮጵያ በሁለቱም ጾታ ወርቅ አገኘች
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በካሜሩን ዱዋላ እየተካሄደ በሚገኘው 23ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የእርምጃ ውድድር ኢትዮጵያ በሁለቱም ጾታዎች የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ ሆናለች፡፡
ዛሬ ረፋድ የተካሄደው የ20 ኪሎ ሜትር የእርምጃ ውድድር በአትሌት ስንታየሁ ማስሬ እና ምስጋና ዋቁማ አሸናፊነት ተጠናቅቋል።
እስከ አሁን በተካሄዱ ውድድሮች ኢትዮጵያ…
ፈረንሳይ፣ እንግሊዝና ኔዘርላንድስ ጥሎ ማለፉን ለመቀላቀል ብርቱ ፍልሚያ ይጠብቃቸዋል
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ17ኛው የአውሮፓ ዋንጫ የዛሬ መርሐ-ግብሮች ጥሎ ማለፉን ለመቀላቀል የሚያስችሉ ጠንካራ ፉክክር የሚጠብቃቸው አራት ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡
በዚህ መሠረትም ምሽት 1 ሠዓት ላይ በቡድን አራት የተደለደሉት ፈረንሳይ ከፖላንድ እንዲሁም ኔዘርላንድስ (ሆላንድ) ከኦስትሪያ በተመሳሳይ ሠዓት ይጫወታሉ፡፡
ምድብ አራትን የምትመራው…
በቦስተን የሴቶች 10ሺህ ሜትር የሩጫ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸነፉ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)በቦስተን በተካሄደው የሴቶች 10ሺህ ሜትር የሩጫ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከ1 እሰከ 3 ደረጃ በመያዝ አሸንፈዋል፡፡
ውድድሩን መልክናት ዉዱ በ31 ደቂቃ ከ15 ሴኮንድ በመጨረስ አንደኛ ደረጃን ስትይዝ ፣ቦሰና ሙላት በ31 ደቂቃ ከ16 ሴኮንድ፣ሰናይት ጌታቸው በ31 ደቂቃ ከ17 ሴኮንድ በመግበት 2ኛ እና 3ኛ ደረጃን በመያዝ…