ስፓርት
ፖርቹጋል ዛሬ ተጠባቂ ጨዋታዋን ታደርጋለች
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ17ኛው የአውሮፓ ዋንጫ ዛሬ ምሽት ቱርክ ከፖርቹጋል የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡
በ2024 የአውሮፓ ዋንጫ 10 ሠዓት ላይ በምድብ 6 የሚገኙት ጆርጂያ እና ቼክ ሪፐብሊክ ይጫወታሉ፡፡
በመጀመሪያው የምድብ ማጣሪያ ጨዋታ ጆርጂያ በቱርክ 3 ለ 1 እንዲሁም ቼክ ሪፐብሊክ በፖርቹጋል 2 ለ 1 መሸነፋቸው ይታወሳል፡፡
ይህን ተከትሎም ሁለቱም ብሔራዊ ቡድኖች ያለምንም ነጥብ በምድቡ ግርጌ ላይ ይገኛሉ፡፡
በዚሁ ምድብ የሚገኙት እና እኩል 3 ነጥብ ያላቸው ቱርክ እና ፖርቹጋል ምሽት 1 ሠዓት…
Read More...
ኦስትሪያ ፖላንድን በማሸነፍ ወደ ጥሎ ማለፍ የመግባት ዕድሏን አለመለመች
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ17ኛው የአውሮፓ ዋንጫ በምድብ አራት የተደለደሉት ኦስትሪያና ፖላንድ ባደረጉት የምድቡ ሁለተኛ ጨዋታ ኦስትሪያ 3 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፋለች።
በዚህም ኦስትሪያ ወደ ጥሎ ማለፍ የመግባት ዕድሏን አለምልማለች።
በምድቡ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ ኦስትሪያ በፈረንሳይ 1 ለ 0፤ እንዲሁም ፖላንድ በኔዘርላንድስ 2 ለ 1…
በአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በሴቶች 5 ሺህ ሜትር ኢትዮጵያ የወርቅና የብር ሜዳሊያ አገኘች
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በካሜሩን ዱዋላ ዛሬ በጀመረው 23ኛ የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በሴቶች 5 ሺህ ሜትር ሩጫ ኢትዮጵያ የወርቅና የብር ሜዳሊያ አግኝታለች።
በውድድሩ አትሌት ፋንታዬ በላይነህ እና አትሌት ውብርስት አስቻለ ተከታትለው በመግባት ለሀገራቸው የወርቅና የብር ሜዳሊያ አምጥተዋል።
ዩክሬን ስሎቫኪያን አሸነፈች
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ17ኛው የአውሮፓ ዋንጫ ሁለተኛው ዙር የምድብ ማጣሪያ መርሐ ግብር ዛሬ ቀጥሎ ሲካሄድ ዩክሬን ስሎቫኪያን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፋለች።
ቀን 10 ሰዓት ላይ በተካሄደው ጨዋታ ስሎቫኪያ 17ኛው ደቂቃ ላይ ባስቆጠረችው ጎል ስትመራ ቆይታ፤ ዩክሬን በ54ኛው እና በ80ኛው ደቂቃ ላይ ባስቆጠረቻቸው ጎሎች ወሳኝ ሶስት ነጥብ ይዛ…
በፕሪሚየር ሊጉ ባሕርዳር ከተማ አዳማ ከተማን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ28ኛ ሣምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ባሕርዳር ከተማ ከመመራት ተነስቶ አዳማ ከተማን 3 ለ 2 ማሸነፍ ችሏል፡፡
ኤልያስ ለገሠ እና ዮሴፍ ታረቀኝ ለአዳማ ከተማ እንዲሁም የአብሥራ ተስፋዬ፣ ወንድወሰን በለጠ እና ፍቅሩ ዓለማየሁ (በራስ ላይ) ለጣና ሞገዶቹ ጎሎቹን አስቆጥረዋል፡፡
በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም እየተካሄደ…
ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ፍሬወይኒ የ1500 ሜትር የሴቶች ሩጫ ውድድር አሸነፈች
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ፍሬወይኒ ሐይሉ በፖላንድ በተካሄደው የ1500 ሜትር የቤት ውስጥ የሴቶች ሩጫ ውድድር አሸንፋለች፡፡
አትሌቷ በፖላንድ ባይድጎሽ ከተማ በተካሄደው የ1500 የሴቶች ሩጫ ውድድር 3፡58.59 በሆነ ሰዓት በመግባት ማሸነፏን ከዎርልድ አትሌቲክስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከዚህ በፊት አትሌቷ በፖላንድ…
በአውሮፓ ዋንጫ ስሎቬኒያና ሰርቢያ አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአውሮፓ ዋንጫ የምድብ 3 ጨዋታ ስሎቬኒያና ሰርቢያ 1 አቻ ተለያዩ፡፡
የስሎቬኒያን ጎል ዛን ካርኒቺኒክ (69') ሲያስቆጥር ሰርቢያን አቻ ያደረገችውን ደግሞ ሉካ ጆቪች (90'+5) ከመረብ አገናኝቷል፡፡