Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ማንቼስተር ሲቲ በሜዳው በቶተንሃም ሆትስፐር 4 ለ 0 ተሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 14፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትሃድ ስታዲየም ቶተንሃም ሆትስፐርን ያስተናገደው ማንቼስተር ሲቲ 4 ለ 0 ተሸንፏል፡፡ የቶተንሃም ሆትስፐርን ግቦች ጀምስ ማዲሰን በ13ኛው እና 20ኛው (2) እንዲሁም ፔድሮ ፖሮ በ52ኛው ደቂቃ አስቆጥረዋል፡፡ በተጨማሪም አራተኛዋን ጎል ጆንሰን በ93ኛው ደቂቃ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል፡፡ በተከታታይ ሽንፈት እያስተናገዱ ያሉት ውኃ ሰማያዊዮቹ ተስተካካይ ጨዋታ እየቀረው ፕሪሚየር ሊጉን በ28 ነጥብ ከሚመራው ሊቨርፑል በአምሥት ነጥብ ዝቅ ብለው ሁለተኛ ላይ ይገኛሉ፡፡
Read More...

አርሰናል፣ ዎልቭስ እና ብራይተን ተጋጣሚዎቻቸውን አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 14፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በ12ኛ ሣምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በተመሳሳይ 12 ሠዓት ላይ አምሥት ጨዋታዎች ተደርገዋል፡፡ በዚህም በሜዳው አርሰናል ኖቲንግሃም ፎረስትን 3 ለ 0 በረታበት ጨዋታ÷ ሳካ፣ ፓርቴ እና ንዋንሪ ግቦችን አስቆጥረዋል፡፡ እንዲሁም ዎልቭስ ፉልሃምን 4 ለ1 ሲረታ÷ ብራይተን በርንማውዝን 2 ለ 1 አሸንፏል፡፡ በሌላ…

አርባ ምንጭ ከተማ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 14፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በድሬዳዋ ስታዲየም እየተካሄደ በሚገኘው 8ኛ ሣምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አርባምንጭ ከተማ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡ የአርባ ምንጭ ከተማን ግቦችም በፍቅር ግዛው በ22ኛው እና አሕመድ ሁሴን በ48ኛው ደቂቃ ከመረብ አሳርፈዋል፡፡ በተመሳሳይ ምሽት 1 ሠዓት ላይ በተካሄደ ጨዋታ ድሬዳዋ ከተማ…

ቼልሲ ሌስተር ሲቲን በሜዳው አሸንፏል

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 14፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በ12ኛ ሣምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ቼልሲን በሜዳው ያስተናገደው ሌስተር ሲቲ 2 ለ 1 ተሸንፏል፡፡ የቼልሲን ግቦች ኒኮላስ ጃክሰን በ15ኛው እንዲሁም ኤንዞ ፈርናንዴዝ በ75ኛው ደቂቃ ከመረብ አሳርፈዋል፡፡ እንዲሁም የሌስተር ሲቲን ብቸኛ ጎል ጆርዳን አየው በ95ኛው ደቂቃ በፍጹም ቅጣት ምት ማስቆጠር ችሏል፡፡…

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ከኢንተርናሽናል ጨዋታዎች መልስ ዛሬ ተጠባቂ ጨዋታዎችን ያስተናግዳል

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 14፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ከኢንተርናሽናል ጨዋታዎች መልስ በዛሬው ዕለት በደጋፊዎች ዘንድ ከፍተኛ ግምት የተሰጣቸው ጨዋታዎች ይካሄዳሉ። በዚህም መሠረት ማንቼስተር ሲቲ በሜዳው ኤቲሃድ የሰሜን ለንደኑን ቶተንም ሆትስፐርስ ከምሽቱ 2:30 ጀምሮ የሚያስተናግድበት ግጥሚያ በጉጉት ይጠበቃል። የዛሬው ጨዋታ ለፔፕ ጓርዲዮላው…

ሊዮኔል ሜሲ በዓለም አቀፍ ጨዋታዎች የግብ እድሎችን አመቻችቶ የማቀብል ክብረወሰንን ተጋራ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) አርጅንቲናዊው አጥቂ ሊዮኔል ሜሲ በዓለም አቀፍ ጨዋታዎች 58 የግብ እድሎችን አመቻችቶ የማቀብል ክብረወሰንን ከቀድሞው አሜሪካዊ አጥቂ ላንደን ዶንቫን ጋር ተጋርቷል፡፡ ሜሲ ትላንት ምሽት በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ አርጀንቲና ፔሩን 1 ለ 0 ባሸነፈችበት ምሽት ለቡድን አጋሩ ላውታሮ ማርቲኔዝ ግብ የሆነችዋን ኳስ አመቻችቶ…

ፔፕ ጓርዲዮላ በማቺስተር ሲቲ ለመቆየት ተስማማ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የማንቼስተር ሲቲ አሰልጣኝ ጆሴፍ ፔፕ ጓርዲዮላ በክለቡ ለቀጣይ አንድ ዓመት የሚያቆየውን የውል ማራዘሚያ ለመፈረም መስማማቱ ተነገረ፡፡ የ53 ዓመቱ ስፔናዊ አሰልጣኝ በፈረንጆቹ 2016 ማንቼስተር ሲቲን ከተቀላቀል ወዲህ ስድስት የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫዎችን ጨምሮ 18 ዋንጫዎችን አሳክቷል፡፡ በእንግሊዝ እግር ኳስ አዲስ…