ስፓርት
በአውሮፓ ዋንጫ ስዊዘርላንድ ሀንጋሪን አሸነፈች
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ17ኛው የአውሮፓ ዋንጫ ጨዋታዎች ዛሬ በተካሄደው የምድብ አንድ ጨዋታ ስዊዘርላንድ ሀንጋሪን 3 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸነፈች።
የስዊዘርላንድን የማሸነፊያ ግቦች ክዋዶ ዱዋህ፣ ሚሸል ኤቢስቸር እና ብሪል ኢምቦሎ ሲያስቆጥሩ የሀንጋሪን ማስተዛዘኛ ግብ ደግሞ በርናባስ ቫርጋ ከመረብ አሳርፏል።
ትናንት በተካሄደው የምድቡ የመጀመሪያ ጨዋታ አስተናጋጇ ጀርመን ስኮትላንድን 3 ለ 1 በሆነ ሰፊ ውጤት ማሸነፏ ይታወቃል።
Read More...
አዳማ ከተማ ሀዋሳ ከተማን በሰፊ የጎል ልዩነት አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አዳማ ከተማ ሀዋሳ ከተማን 5 ለ 0 በሆነ ሰፊ የጎል ልዩነት አሸነፈ።
በፕሪሚየር ሊጉ 27ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ቀን 9 ሠዓት ላይ ሐዋሳ ከተማ እና አዳማ ከተማ ጨዋታቸውን አድርገዋል፡፡
የአዳማ ከተማ የማሸነፊያ ጎሎችን ነቢል ኑሪ፣ ዮሴፍ ታረቀኝ 2 ጎሎችን፣ ቢኒያም ዐይተን እና አህመድ ረሺድ…
መቻል ፋሲል ከነማን 1 ለ 0 አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 27ኛ ሳምንት መርሐ ግብር መቻል ፋሲል ከነማን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፋል፡፡
የመቻልን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ አብዱ ሙተለቡ በ86ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል፡፡
የፕሪሚየር ሊጉ መርሐ ግብር ሲቀጥል ምሽት 12 ሰዓት ላይ ድሬደዋ ከተማ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡
በተመሳሳይ 12…
17ኛው የአውሮፓ ዋንጫ ጨዋታዎች ዛሬ መካሄድ ይጀምራሉ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 24 ሀገራት የሚሳተፉበት የ2024 የአውሮፓ ዋንጫ ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት 4 ሠዓት ላይ አስተናጋጇ ጀርመን ከስኮትላንድ በሚያደርጉት የመክፈቻ ጨዋታ ይጀመራል፡፡
ጨዋታው ሲቀጥል ነገ ቀን 10 ሠዓት ላይ ሀንጋሪ ከስዊዘርላንድ፣ ምሽት 1 ሠዓት ላይ ስፔን ከክሮሽያ እንዲሁም ምሽት 4 ሠዓት ላይ ጣልያን ከአልባኒያ ይጫወታሉ፡፡…
ሊዮኔል ሜሲ የእግር ኳስ ህይወቱን በአሜሪካው ክለብ ማጠናቀቅ እንደሚፈልግ አስታወቀ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አርጀንቲናዊው ሊዮኔል ሜሲ የእግር ኳስ ህይወቱን በአሜሪካው ኢንተር ማያሚ ክለብ ማጠናቀቀቅ እንደሚፈልግ አስታወቀ፡፡
የ8 ጊዜ ባለንዶር አሸናፊው ሜሲ የፈረንሳዩን ክለብ ፓሪስ ሴንት ጀርሜን በመልቀቅ በክረምቱ የዝውውር መስኮት ወደ አሜሪካ ማቅናቱ ይታወሳል፡፡
“ኢንተር ማያሚ የመጨረሻው ክለቤ ይሆናል ብዬ አስባለሁ” ሲል…
ህር ዳር ከተማና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 27ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ባህር ዳር ከተማ እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 2 ለ 2 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል።
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም 9 ሰዓት ላይ በተካሄደው ጨዋታ የባህር ዳር ከተማን ግቦች ፀጋዬ አበራና ያብስራ ተስፋዬ አስቆጥረዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ግቦች ደግሞ አዲስ ግደይ…
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ27ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ዛሬ ይጀመራል
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በ27ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ዛሬ ወደ ውድድር ይመለሳል።
የሊጉ መሪ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከባህር ዳር ከተማ ከቀኑ 9 ሰዓት በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ይጫወታሉ።
በሌላኛው የ27ኛ ሳምንት ጨዋታ…