ስፓርት
ኢትዮጵያ መድን አዳማ ከተማን 4 ለ 1 አሸነፈ
አዲሰ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ መድን አዳማ ከተማን 4 ለ 1 በሆነ ሰፊ ልዩነት አሸንፏል፡፡
በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው 26ኛ ሣምንት የፕሪሚየር ሊጉ መርሐ ግብር የኢትዮጵያ መድንን የማሸነፊያ ግቦች ሐይደር ሸረፋ፣ አለን ካይዋ፣ አብዲሳ ጀማል እና አቡበከር ሳኒ አስቆጥረዋል፡፡
የአዳማ ከተማን ብቸኛ ግብ ደግሞ ጀሚል ያዕቆብ ከመረብ አሳርፏል፡፡
በተመሳሳይ ቀድም ሲል በተካሄደ ጨዋታ ድሬዳዋ ከተማ ወልቂጤ ከተማን 3 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
Read More...
አትሌት ትዕግስት አሰፋ በበርሊን ማራቶን ያስመዘገበችው ክብረወሰን ጸደቀ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ትዕግስት አሰፋ በበርሊን ማራቶን ያስመዘገበችው ሰዓት የዓለም የሴቶች የማራቶን ክብረወሰን ሆኖ ጸድቋል፡፡
አትሌት ትዕግስት አሰፋ የበርሊን ማራቶን ውድድርን 2:11:53 በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ ክብረ ወሰን መስበሯ ይታወሳል፡
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ27ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ላልተወሰነ ጊዜ ተራዘመ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ27ኛ ሳምንት መርሐ ግብር በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን የሊጉ አክሲዮን ማህበር አስታወቀ።
የ27ኛ ሳምንት የሊጉ ጨዋታዎች በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ከግንቦት 22 እስከ 25 ቀን 2016 ዓ.ም እንዲካሄዱ የጨዋታ መርሃ ግብር…
በፓሪስ ኦሊምፒክ ዳያስፖራዎች በውድድሩ ቦታ ተገኝተው አትሌቶችን እንዲያበረታቱ ተጠየቀ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በፓሪስ ኦሊምፒክ ከ200 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ዳያስፖራዎች በውድድር ስፍራ ተገኝተው አትሌቶችን እንዲያበረታቱ እየተሰራ መሆኑ ተመላከተ።
በፓሪስ ኦሊምፒክ ውጤታማ ለመሆን የሚያስችል ጠንካራ ስራ እየተሰራ እንደሆነ የፓሪስ ኦሎምፒክ የብሔራዊ ዝግጅት ኮሚቴ አስታውቋል።
ኮሚቴው በተሰጠ መግለጫ፤ ኢትዮጵያን የሚመጥን…
ቼልሲ ከአሰልጣኙ ጋር ተለያየ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ አሰልጣኝ ማውሪስዮ ፖቸቲኖን በጋራ ስምምነት ከአሰልጣኝነት አሰናበተ፡፡
የ52 ዓመቱ ፖቸቲኖን እንደ አውሮፕያኑ አቆጣጠር ሐምሌ 1 ቀን 2023 ነበር ቼልሲን ለማሰልጠን የሁለት ዓመት ኮንትራት የተፈራረሙት፡፡
ቼልሲ የዘንድሮውን የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በ6ኛ ደረጃ ማጠናቀቁ ይታወሳል፡፡
ቶኒ ክሩስ ከዩሮ 2024 በኋላ ጫማ እንደሚሰቅል አስታውቋል
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሪያል ማድሪድ እና የጀርመኑ አማካኝ ቶኒ ክሩስ በቀጣይ ወር ሀገሩ ከምታስተናግደው ዩሮ 2024 መጠናቀቅ በኋላ ጫማ እንደሚሰቅል አስታውቋል፡፡
በፈረንጆቹ ጥር 4/1990 በምስራቅ ጀርመን የተወለደው ክሩስ የፕሮፌሽናል እግርኳስ ህይወቱን የጀመረው በባየር ሙኒክ ሲሆን ሶስት የቡንደስሊጋ እና ሶስት የጀርመን ጥሎ ማለፍ…
ማንቼስተር ሲቲ የ2023/24 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን ሆነ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ማንቼስተር ሲቲ ብርቱ ፉክክር በታየበት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ2023/24 የውድድር ዘመን ሻምፒዮን ሆኗል፡፡
በዛሬው ዕለት ፍጻሜውን ባገኘው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በሜዳው ዌስትሃምን ያስተናገደው ማንቼስተር ሲቲ 3 ለ1 ማሸነፉን ተከትሎ ነው ሻምፒዮንነቱን ያረጋገጠው፡፡
በዚህም 91 ነጥቦችን በመሰብሰብ ፕሪሚየር…