ስፓርት
ኮል ፓልመር የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ምርጥ ወጣት ተጫዋች ሽልማትን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቼልሲው የአማካይ ስፍራ ተጫዋች ኮል ፓልመር የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ2023/24 የዓመቱ ምርጥ ወጣት ተጫዋች ሽልማትን አሸንፏል፡፡
ፓልመር የዓመቱ ምርጥ ወጣት ተጫዋች የመጨረሻ እጩ የነበሩትን ኧርሊንግ ሃላንድ እና ቡካዮ ሳካን በመበልጥ ነው ማሸነፍ የቻለው፡፡
በ42 ሚሊየን ዩሮ ከማንቼስተር ሲቲ ቼልሲን የተቀላቀለ ሲሆን ፥ በውድድር ዓመቱ ደካማ አቋምን ባሳየው ቼልሲ 22 ጎሎችን በማስቆጠር 10 ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን ደግሞ አመቻችቶ አቀብሏል፡፡
የ22 ዓመቱ እንግሊዛዊ ቀደም ሲል…
Read More...
በፕሪሚየር ሊጉ ባሕርዳር ከተማ ሀምበሪቾን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ25ኛ ሣምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ባሕርዳር ከተማ ሀምበሪቾን 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡
ባሕርዳር ከተማ ሀምበሪቾን በረታበት ጨዋታ ፍፁም ጥላሁን ሁለቱንም ጎሎች ከመረብ ማሳረፍ ችሏል፡፡
ውጤቱን ተከትሎም የጣና ሞገዶቹ ነጥባቸውን 44 በማድረስ ባሉበት 3ኛ ደረጃን ማስጠበቅ ሲችሉ÷ ሀምበሪቾ 8 ነጥቦችን በመያዝ የሊጉ…
አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በፓሪሱ ኦሎምፒክ የስፖርት ቤተሰቡ የተለመደውን ድጋፍ እንዲሰጠው ጠየቀ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)አንጋፋው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በ2024ቱ የፓሪስ ኦሎምፒክ የመጨረሻ ድሉን ለማስመዘገብ በሚያደረገው ጥረት የስፖርት ቤተሰቡ የተለመደውን ድጋፍ እንዲሰጠው ጠየቀ፡፡
አትሌቱ በ2024 የፓሪስ ኦሊምፒክ ኢትዮጵያን በመወከል እንዲሳተፍ ያደረገው ጥረት በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተቀባይነት ማግኘቱን ተከትሎ በማኅበራዊ ትስስር…
በፓሪስ ኦሊምፒክ ማራቶን ቀነኒሳ በቀለን ጨምሮ ተሳታፊ አትሌቶች ተለዩ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌቲክስ ፌደሬሽን በፓሪስ ኦሊምፒክ 2024 ማራቶን አትሌት ቀነኒሳ በቀለን ጨምሮ በሁለቱም ጾታ የሚሳተፉ እና ተጠባባቂ አትሌቶችን ይፋ አድርጓል፡፡
በዚህም በወንዶች አትሌት ቀነኒሳ በቀለ፣ ሲሳይ ለማ እና ዴሬሳ ገለታ ተካትተዋል፡፡
በዚሁ ቡድን አትሌት ታምራት ቶላ እና ኡሰዲን መሐመድ በተጠባባቂነት መካተታቸውን…
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወላይታ ድቻን በሰፊ የጎል ልዩነት አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ መሪው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወላይታ ድቻን 5 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸንፏል፡፡
ቀን 9 ሰዓት ላይ በተደረገው ጨዋታ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፍፁም ግርማይ (በራሱ ላይ)፣ ባሲሩ ኡመር፣ሳይመን ፒተር፣አፍሬም ታምራት እና ኪቲካ ጀማ ጎሎችን አስቆጥረዋል፡፡
ውጤቱን ተከትሎም ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ…
በፕሪሚየር ሊጉ ቫር ተግባራዊ እንዳይደረግ የሚያስችል ድምጽ ሊሰጥ ነው
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች በሚቀጥለው የውድድር ዓመት በተንቀሳቃሽ ምስል የታገዘ ዳኝነት (ቫር) ተግባራዊ እንዳይደረግ የሚያስችል ድምጽ ሊሰጡ መሆኑን ፕሪሚየር ሊጉ አስታውቋል፡፡
ቫር በፕሪሚየር ሊጉ ከፈረንጆቹ 2019 ጀምሮ ተግባራዊ የተደረገ ሲሆን÷የተወሰኑ ክለቦች በቫር ውሳኔ ደስተኛ አለመሆናቸውን እና እግር ኳሱን እየረበሸው…
ኢትዮጵያ ቡና ወላይታ ድቻን 2 ለ 1 አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 24ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ቡና ወላይታ ድቻን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
የኢትዮጵያ ቡናን የማሸነፊያ ግቦች መስፍን ታፈሰ እና መሃመድ ኑር ናስር አስቆጥረዋል፡፡
ወላይታ ድቻን ከሽንፈት ያላደነችዋን ብቸኛ ግብ ደግሞ ብዙአየሁ ሰይፉ ከመረብ አሳርፏል፡፡
በሌላ በኩል ሀዋሳ ከተማ…