Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

በኤሲሚላን ራሱን ለዓለም ያሳየው አንድሪያ ፒርሎ…

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጣሊያናዊው የኤሲሚላን የቀድሞ ኮከብ አንድሪያ ፒርሎ ከምንጊዜም ምርጥ የመሐል ሜዳ ተጫዋቾች መካከል አንዱ ነው፡፡ በፈረንጆቹ 1979 በዛሬዋ ዕለት የተወለደው አንድሪያ ፒርሎ የእግር ኳስ ሕይወቱን የጀመረው በሀገሩ ክለብ ብሬሺያ ነው፡፡ ከምንጊዜም ታላላቅ የመሐል ሜዳ ተጫዋች መካከል አንዱ የሆነው ፒርሎ በእይታው፣ በፈጠራ ብቃቱ፣ በሚያቀብላቸው ኳሶች እና በፍፁም ቅጣት ምት ችሎታው ይታወቃል። ፒርሎ ከብሬሺያ በኋላ ወደ ኢንተርሚላን ቢያቀናም መቆየት የቻለው ለሁለት የውድድር ዓመት ብቻ…
Read More...

ዳኒ ካርቫሃል ከሪያል ማድሪድ ጋር ተለያየ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ስፔናዊው የቀኝ መስመር የተከላካይ ስፍራ ተጫዋች ዳኒ ካርቫሃል ከሪያል ማድሪድ ጋር ተለያይቷል፡፡ የ34 ዓመቱ ተጫዋች በሪያል ማድሪድ ቆይታው 4 የስፔን ላሊጋ፣ 6 የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ እና 2 የኮፓ ዴል ሬይ ዋንጫዎችን ጨምሮ 27 ዋንጫዎችን አሳክቷል፡፡ በፈረንጆቹ 2013 ከጀርመኑ ክለብ ባየር ሊቨርኩሰን…

በዓለም የኤምኤምኤ ከባድ ሚዛን ውድድር ካሜሩናዊው ፍራንሲስ ንጋኑ በዝረራ አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአሜሪካ ካሊፎርኒያ በተካሄደው በዓለም የድብልቅ ማርሻል አርት (ኤምኤምኤ) ከባድ ሚዛን ውድድር ካሜሩናዊው ፍራንሲስ ንጋኑ ብራዚላዊውን ፍሊፕ ሊንስ በመጀመሪያው ዙር ግጥሚያ በዝረራ አሸንፏል፡፡ ትናንት ምሽት በተካሄደው ውድድር ንጋኑ ከብራዚላዊው የኤምኤምኤ ኮከብ ፍሊፕ ሊንስ ከባድ ፉክክር ቢገጥመውም በሰነዘረው ቡጢ…

ሰንደርላንድ እና ሊድስ ዩናይትድ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ37ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ሰንደርላንድ እና ሊድስ ዩናይትድ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል። አመሻሽ 11 ሰዓት ላይ የተካሄደው የሰንደርላንድ እና ኤቨርተን ጨዋታ በሰንደርላንድ 3 ለ 1 አሸናፊነት ተጠናቅቋል። በጨዋታው የሰንደር ላንድ ግቦችን ኢንዞ ለፌ፣ ብራያን ብሮቤይ እና ዊልሰን ኢሲዶር…

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን ሆነ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኢትዮ ኤሌክትሪክን 2 ለ 0 በማሸነፍ የ2018 የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን ሆኗል። የ2018 የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተደረገ ጨዋታ ፍፃሜውን አግኝቷል። ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ እስከ ሊጉ መጨረሻ ጨዋታ በነጥብ እኩል ሆነው ዛሬ…

ማንቼስተር ዩናይትድ ኖቲንግሃም ፎረስትን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ37ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ማንቼስተር ዩናይትድ ኖቲንግሃም ፎረስትን 3 ለ 2 አሸንፏል። ቀን 8:30 ላይ በኦልድ ትራፎርድ በተደረገው ጨዋታ የዩናይትድን ግቦች ሉክ ሻው፣ ማቲዎስ ኩንሃ እና ብራያን ምቤሞ አስቆጥረዋል። የኖቲንግሃም ፎረስትን ከመሸነፍ ያልታደጋቸውን ግቦች ደግሞ ሞራቶ እና ጊብስ…

24ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ በሚደረጉ ውድድሮች ፍፃሜውን ያገኛል

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) 24ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ በሚደረጉ ውድድሮች ይጠናቀቃል። በውድድሩ የመጨረሻ ቀን ላይ ኢትዮጵያን የወከሉ አትሌቶች የሚካፈሉባቸው 8 የፍፃሜ ውድድሮች ምሽት ላይ ይደረጋሉ። በዚህም አመሻሽ 12:30 ላይ በከፍታ ዝላይ አትሌት ገመዶ አባተ እንዲሁም አመሻሽ 12:40 አትሌት ኦታጌ ኦባንግ በወንዶች የጦር…