ስፓርት
አሰልጣኝ ኢጎር ቱዶር ከቶተንሃም ሆትስፐር ጋር ተለያየ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተንሃም ከአሰልጣኝ ኢጎር ቱዶር ጋር መለያየቱን አስታውቋል፡፡
ከሊጉ የመውረድ ስጋት ያለበት ቶተንሃም ቶማስ ፍራንክን በማሰናበት የኢጎር ቱዶርን ቅጥር መፈጸሙ ይታወሳል፡፡
ይሁን እንጂ የ47 ዓመቱ አሰልጣኝ ኢጎር ቱዶር ባስመዘገበው ደካማ ውጤት ከ44 ቀናት ቆይታ በኋላ ከክለቡ ጋር
ተለያይቷል፡፡
ቶተንሃም ሆትስፐር ከአሰልጣኝ ኢጎር ቱዶር ጋር በስምምነት እንደተለያየ መግለጹን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
Read More...
የኢትዮጵያ የባህል ስፖርቶች ውድድርና ፌስቲቫል በሐረር ከተማ ተጀመረ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) 23ኛው የኢትዮጵያ የባህል ስፖርቶች ውድድርና 19ኛው የባህል ስፖርቶች ፌስቲቫል በዛሬው ዕለት በሐረር ከተማ መካሄድ ጀምሯል፡፡
በውድድርና ፌስቲቫሉ መክፈቻ ላይ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴዔታ መኪዩ መሀመድ፣ የኢትዮጵያ ባህል ስፖርቶች ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ህይወት መሀመድን…
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ የመጀመሪያ ጨዋታ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔን 3 ለ 0 አሸንፏል።
በሞሮኮ ኤል አብዲ ስታዲየም ምሽት 1 ሰዓት ላይ በተደረገው ጨዋታ የዋልያዎቹን የማሸነፊያ ግቦች አቤል ያለው (2) እና ከነዓን ማርክነህ አስቆጥረዋል።
መልሱ ጨዋታ በቀጣይ ሳምንት ማክሰኞ…
ከልጅነቱ የአርሰናል ወዳጅ ሆኖ ያደገው ዊሊያም ሳሊባ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በዚህ ወቅት ዓለም ላይ ካሉ ምርጥ የመሐል ተከላካይ ሥፍራ ተጫዋቾች መካከል አንዱ ነው ፈረንሳዊው ዊሊያም ሳሊባ፡፡
መካከለኛ የኑሮ ደረጃ ካላቸው ቤተሰቦች የተወለደው ሳሊባ እንደ ማንኛውም ታዳጊ በፓሪስ በምትገኝ ቦንዲ መንደር ውስጥ መንገድ ላይ ኳስ እየተጫወተ ነው ያደገው፡፡
በሳሊባ የእግር ኳስ ሕይወት ላይ ትልቅ…
የአፍሪካ ዋንጫን ከሴኔጋል የነጠቀው አወዛጋቢው የካፍ ውሳኔ…
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ከወራት በፊት ሴኔጋል አሸንፋው የነበረውን የአፍሪካ ዋንጫ ለሞሮኮ እንዲመለስ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
በቅርቡ በሰሜን አፍሪካዊቷ ሀገር በተደረገው 2025 የቶታል ኢነርጂ የአፍሪካ ዋንጫ ፍጻሜ ሴኔጋል ሞሮኮን አሸንፋ ዋንጫውን ማንሳቷ ይታወሳል፡፡
ይሁን እንጂ በፍጻሜው ጨዋታ በተፈጠረው…
የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ተጠባቂ የመልስ ጨዋታዎች…
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የ16ቱ ጥሎ ማለፍ የመልስ ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት መደረግ ይጀምራሉ፡፡
ምሽት 2 ሰዓት ከ45 ላይ የፖርቹጋሉ ክለብ ስፖርቲንግ ሊዝበን በሜዳው ቦዶ ግሊምትን ያስተናግዳል፡፡
ሁለቱ ቡድኖች ባለፈው ሳምንት በመጀመሪያ ዙር ያደረጉትን ጨዋታ የኖርዌዩ ክለብ ቦዶ ግሊምት 3 ለ 0 በማሸነፍ ወደ ሩብ ፍጻሜ…
የማንቼስተር ሲቲ ቀጣይ አምስት ፈታኝ ጨዋታዎች
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ለአራትዮሽ ዋንጫ እየተፎካከረ የሚገኘው ማንቼስተር ሲቲ በቀጣይ በተለያዩ ውድድሮች በሚያደርጋቸው አምስት ተከታታይ ጨዋታዎች ይፈተናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የማንቼስተር ሲቲ ቀጣይ አምስት ተከታታይ ጨዋታዎች የቡድኑ የዋንጫ ጉዞ ላይ የሚወስኑ ሲሆን ከአምስቱ ጨዋታዎች መካከል ሁለት ጊዜ ከአርሰናል ጋር ይገናኛል፡፡
በአሰልጣኝ…