Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ኒውካስል ዩናይትድ ከአርሰናል የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ አርሰናል ከኒውካስል ዩናይትድ ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል። በ6ኛ ሳምንት የሊጉ መርሐ ግብር ዛሬ መድፈኞቹ ምሽት 12፡30 ላይ ከኒውካስል ዩናይትድ ጋር ከባድ ፍልሚያ ያደርጋሉ። የሊጉ መሪ የሆነው ሊቨርፑል በትናንትናው ዕለት ሽንፈት ማስተናገዱን ተከትሎ አርሰናል በመካከላቸው ያለውን የአምስት ነጥብ ልዩነት ለማጥበብ ወደ ሜዳ ይገባል። አርሰናል ከዚህ በፊት በሴንት ጀምስ ፓርክ ባደረጋቸው ሁለት ጨዋታዎች ምንም ግብ ሳያስቆጥር የተሸነፈ ሲሆን÷ ዛሬም…
Read More...

ሪያል ማድሪድ በሰፊ የግብ ልዩነት በአትሌቲኮ ማድሪድ ተሸነፈ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በጉጉት ሲጠበቅ በነበረው የማድሪድ ደርቢ ሪያል ማድሪድ በአትሌቲኮ ማድሪድ 5 ለ 2 በሆነ ውጤት ተሸንፏል፡፡ የአትሌቲን የማሸነፊያ ግቦች ለኖርማንድ፣ ሶርሎት፣ ሁሊያን አልቫሬዝ (2) እና አንትዋን ግሪዝማን አስቆጥረዋል፡፡ የሪያል ማድሪድን ግቦች ደግሞ ኪሊያን ምባፔ እና አርዳ ጉለር ከመረብ አሳርፈዋል፡፡

ሊቨርፑል በክሪስታል ፓላስ ተሸነፈ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ6ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ሊቨርፑል በክሪስታል ፓላስ 2 ለ 1 ተሸንፏል፡፡ የክሪስታል ፓላስን የማሸነፊያ ግቦች ኢስማኤላ ሳር እና ኤዲ ንኬቲያህ ከመረብ አሳርፈዋል፡፡

ማንቼስተር ሲቲ ድል ሲቀናው ቼልሲ ተሸነፈ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ6ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ማንቼስተር ሲቲ በርንሌይን ሲያሸንፍ ቼልሲ በብራይተን ሽንፈት አስተናግዷል፡፡ ኢቲሃድ ስታዲየም ላይ በተደረገው ጨዋታ ሲትዝኖቹ በርንሌይን 5 ለ 1 ሲያሸንፍ ÷ ግቦቹን እስቲቭ በራሱ ግብ ላይ (2)፣ ሃላንድ (2) እና ማቲያስ ኑኔዝ አስቆጥረዋል፡፡…

ኑኖ እስፕሪቶ ሳንቶ የዌስትሃም ዩናይትድ አሰልጣኝ ሆኑ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ግራሃም ፖተርን ያሰናበተው የለንደኑ ክለብ ዌስትሃም ዩናይትድ ፖርቹጋላዊውን አሰልጣኝ ኑኖ እስፕሪቶ ሳንቶን ሾሟል፡፡ በቅርቡ ከኖቲንግሃም ፎረስት የተሰናበተው ኑኖ የሶስት ዓመት ኮንትራት ለዌስትሃም ዩናይትድ መፈረሙን ክለቡ አስታውቋል፡፡ በፕሪሚየር ሊጉ በሦስት ነጥብ 19ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ዌስትሃም ዩናይትድ ፥…

ማንቼስተር ዩናይትድ በብሬንትፎርድ ተሸነፈ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 6ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ወደ ለንደን ያቀናው ማንቼስተር ዩናይትድ በብሬንትፎርድ 3 ለ 1 ተሸንፏል፡፡ የብሬንትፎርድን የማሸነፊያ ግቦች ኢጎር ቲያጎ (2) እና ማቲያስ የንሰን ከመረብ አሳርፈዋል፡፡ የማንቼስተር ዩናይትድን የማስተዛዘኛ ግብ ደግሞ ቤንጃሚን ሼሽኮ አስቆጥሯል፡፡

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ሰባት ጨዋታዎች ይደረጋሉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ6ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ዛሬ ሰባት ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡ በዕለቱ የመጀመሪያ ጨዋታ ማንቼስተር ዩናይትድ ቀን 8፡30 ከሜዳው ውጭ ብሬንትፎርድን ይገጥማል፡፡ በውድድር ዓመቱ ሁሉንም ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው የሊጉ መሪ ሊቨርፑል ቀን 11 ሰዓት ላይ ከሜዳው ውጭ ከክሪስታል ፓላስ ጋር…