Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

የጃፓኗ ካሳማ ከተማ ከንቲባ ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የስፖርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጃፓኗ ካሳማ ከተማ ከንቲባ ሺንጁ ያማጉቺ ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የተለያዩ የስፖርት ቁሳቁስ ድጋፍ አድርገዋል። በጃፓን ካሳማ ከተማ ላለፋት ተከታታይ አምስት ዓመታት በታሕሳስ ወር በጀግናው አትሌት ሻምበል አበበ በቂላ ለመዘከር የግማሽ ማራቶን ውድድር ይዘጋጃል ተብሏል፡፡ ከንቲባ ሺንጁ ያማጉቺ ዛሬ ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የተለያዩ የስፖርት ትጥቅ ድጋፎችን ያስረከቡ ሲሆን ፥ ለአትሌቶች ለስልጠና የሚሆናቸውን ትጥቆች በማምጣታቸው ደስ መሰኘታቸውን ገልጸዋል፡፡ ትጥቆቹ…
Read More...

የፊፋ ቴክኒካል ልዑክ ድሬዳዋ ገባ

አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም አቀፉ እግር ኳስ ማኅበር (ፊፋ) ቴክኒካል ልዑክ ድሬዳዋ ከተማ ገብቷል፡፡ ልዑኩ ድሬዳዋ ከተማ የገባው የድሬዳዋ ስታዲየም የአርቴፊሻል ሳር ንጣፍ እድሳት መጠናቀቅን ተከትሎ ሙያዊ ምልከታ ለማድረግ መሆኑ ተገልጿል፡፡ በምልከታውም ስታዲየሙ የፊፋን መስፈርት የሚያሟላ መሆኑን የማረጋገጥ ሥራ እንደሚያከናውን ይጠበቃል…

አሰልጣኝ ፍሬው ሀይለገብርኤል ከብሔራዊ ቡድኑ ጋር ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን እና ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ፍሬው ኃይለገብርኤል ከብሔራዊ ቡድኑ ጋር በይፋ ተለያይተዋል። የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሆነው በ2013 ዓ.ም የተሾሙት አሰልጣኙ፤ በአራት ዓመት ቆይታቸው ቡድኑ በፈረንጆቹ 2022 እና 2024 የዓለም ዋንጫ…

በግማሽ ፍጻሜ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ናይጄሪያ ከደቡብ አፍሪካ እንዲሁም ኮትዲቯር ከዴሞክራቲክ ኮንጎ ይጫወታሉ

አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ በግማሽ ፍጻሜ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ናይጄሪያ ከደቡብ አፍሪካ እንዲሁም ኮትዲቯር ከዴሞክራቲክ ኮንጎ ዛሬ ምሽት ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡ ናይጄሪያ ከደቡብ አፍሪካ ለፍጻሜ ለማለፍ የሚያደርጉት ጨዋታ ምሽት 2 ሰዓት ላይ በአቢጃን ስታድ ዲ ላ ፔይክስ ይካሄዳል፡፡ ሁለቱ ቡድኖች በግማሽ ፍጻሜ በታሪክ ለ4ኛ…

በቶሩን የቤት ውስጥ ሩጫ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በፖላንድ ቶሩን የቤት ውስጥ ሩጫ ውድድር በተለያዩ ርቀቶች ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ አሸንፈዋል። በ1 ሺህ 500 ሜትር የሴቶች የቤት ውስጥ ሩጫ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከ1ኛ እስከ 4ኛ በመውጣት ታሪክ ሰርተዋል፡፡ በዚህም ፍሬወይኒ ሃይሉ በ1 ሺህ 500 ሜትር ሴቶች የቤት ውስጥ ሩጫ ታሪክ በርቀቱ…

ለወልቂጤ ከተማ እግርኳስ ቡድን  ከ43 ሚሊየን ብር  በላይ ተሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊ ለሆነው የወልቂጤ ከተማ እግርኳስ ቡድን  ከ43 ሚሊየን ብር በላይ መሰብሰቡ ተገለፀ፡፡ የወልቂጤ ከተማ እግር ኳስ ቡድን  የገቢ ማሰባሰቢያ መርኃ ግብር  በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል ተካሄዷል። በገቢ ማሰባሰቢያ መርኃ ገብሩ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው…

በቦስተን የኒው ባላንስ የቤት ውስጥ ውድድር ጉዳፍ ፀጋይና ለሜቻ ግርማ አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቦስተን የኒው ባላንስ የዓለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ውድድር ጉዳፍ ፀጋይ እና ለሜቻ ግርማ ውድድሩን በበላይነት አጠናቅቀዋል፡፡ በ1 ሺህ 500 ሜትር የተወዳደረችው ጉዳፍ ፀጋይ ርቀቱን በ3 ደቂቃ 58 ሰከንድ ከ11 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ ቀዳሚ ሆናለች፡፡ በዚሁ ርቀት የ18 ዓመቷ አትሌት ብርቄ ሀየሎም 3…