ስፓርት
19ኛው የኢትዮጵያ ማራቶን ሪሌ ውድድር ነገ በመቐለ ይካሄዳል
አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 14 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 19ኛው የኢትዮጵያ ማራቶን ሪሌ ውድድር በነገው እለት በትግራይ ክልል መቐለ ይካሄዳል።
በውድድሩ ከስምንት ክለቦች፣ አምስት ክልሎችና ከከተማ መስተዳደሮች የተውጣጡ 84 አትሌቶች ይካፈላሉ።
የማራቶን ሪሌ ውድድር ስድስት አትሌቶች ከአንድ ክለብ ወይም ክልል የሚሳተፉበት የውድድር ዓይነት ሲሆን ከ150 በላይ ልዑካን በውድድሩ ለመሳተፍ መቐለ ገብተዋል።
በሁለቱም ፆታዎች አንደኛ ለሚወጡ አትሌቶች ለእያንዳንዳቸው የ40 ሺህ ብር፣ ሁለተኛ 20…
Read More...
አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ በ5 ሺህ ሜትር ሴቶች ሩጫ የሰበረችው ክብረወሰን ፀደቀ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ በ5 ሺህ ሜትር ሴቶች ሩጫ የሰበረችው ክብረወሰን መጽደቁ ተነገረ፡፡
በአሜሪካ ኢውጅን በተካሄደው የዳይመንድ ሊግ ውድድር ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ የዓለምን ክብረ ወሰን በመስበር ማሸነፏ ይታወሳል።
አትሌቷ በ5 ሺህ ሜትር ሴቶች ሩጫ 14 ደቂቃ ከ00 ሴኮንድ ከ21 ማይክሮ ሴኮንድ በመግባት…
ሀድያ ሆሳዕና የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ አሸናፊ ሆነ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀድያ ሆሳዕና ኢትዮጵያ ቡናን በመለያ ምት በማሸነፍ የ17ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ አሸናፊ ሆኗል፡፡
ሀድያ ሆሳዕናን እና ኢትዮጵያ ቡናን ያገናኘው የ17ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ጨዋታ መደበኛው ሰዓት 2 አቻ የተጠናቀቀ ሲሆን በተሰጠው መለያ ምት ነብሮቹ 5 ለ 4 አሸንፈዋል፡፡
በዚህም 17ኛው የአዲስ አበባ…
ኢትዮጵያ ማሊን በደርሶ መልስ 6 ለ 0 አሸነፈች
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን የማሊ አቻውን በደርሶ መልስ ጨዋታ 6 ለ 0 አሸንፏል፡፡
የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ 3ኛ ዙር የመልስ ጨዋታውን ዛሬ በአዲስ አበባ አበበ ቢቂላ ስታዲየም አካሂዷል፡፡
9 ሠዓት ላይ በተከናወነው የመልስ ጨዋታም የኢትዮጵያ ከ20…
23ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 23ኛው ታላቁ ሩጫ ውድድር በኢትዮጵያ በአዲስ አበባ ተካሂዷል፡፡
በውድድሩ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ላይ ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ እና ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት÷ታላቁ ሩጫ የመዲናዋ ተጨማሪ ድምቀት፣የአብሮነትና የፍቅር መገለጫ ነው፡፡…
አቶ ኢያሱ ወሰን የአፍሪካ ቦክስ ኮንፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ኢያሱ ወሰን የአፍሪካ ቦክስ ኮንፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ሆነው ተመርጠዋል።
47ኛው የአፍሪካ ቦክስ ኮንፌዴሬሽን መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ በአዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት መሰብሰቢያ አዳራሽ ዛሬ ተካሄዷል።
በዚህም የኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ኢያሱ የአፍሪካ ቦክስ ኮንፌዴሬሽን…
በፓሪስ ኦሊምፒክ ለሚሳተፈው የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ቡድን የመለማመጃ ስታዲየም ፈቃድ የመግባቢያ ሥምምነት ተፈረመ
አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 8 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በፓሪስ የኦሊምፒክ ውድድር ለሚሳተፈው የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ቡድን የመለማመጃ ስታዲየም ፈቃድ የመግባቢያ ሥምምነት ተፈረመ።
ሥምምነቱ የተፈረመው በፓሪሱ አንቶኒ ክፍለከተማ ከሚገኝ ስታዲየም ጋር ነው።
ሥምምነቱን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ደራርቱ ቱሉ እና የአንቶኒ ክፍለከተማ ከንቲባ ዣን-ኢቭ ሶናሌ ናቸው።…